Connect with us
Express news


Football

እሁድ ቶተንሃም ከቼልሲ ፍጥጫ!

Tottenham v Chelsea Showdown on Sunday!
eurosport.com

ቶተንሃም በሰሜን ለንደን ቼልሲን በሚያስተናግድበት በእሁዱ ጨዋታ ሃሪ ኬን ከሮሜሉ ሉካኩ የሚፋጠጡ ይሆናል። የቶተንሃሞቹ ተጫዋቾች ሉካስ ሙራ እና ስቲቨን በርግዋይን በጉዳት ላይ ናቸው።

ይህ የለንደን ደርቢ በተለያዩ አቅጣጫዎች እየሄዱ ያሉ ሁለት ክለቦችን ያገናኛል። ቼልሲ በሻምፒዮንስ ሊጉ የመክፈቻ ዙር ካሸነፈ በኋላ ጥሩ ስሜት ላይ ይገኛሉ ፣ ሮሜሉ ሉካኩም በከፍተኛ ምርጥ አቋም ላይ ነው እና በአሁኑ ጊዜ በዓለም እግር ኳስ ውስጥ ካሉ ምርጥ ብቃት እያሳዩ ያሉ አጥቂዎች አንዱ ተብሏል። አርሰናልን ካሸነፈ በኋላ እና እና ጠንካራ ከሆነው ሊቨርፑል ጋር በ 10 ተጫዋቾች 1-1 በሆነ አቻ በመለያየት ቼልሲ አሁን የሊጉ አናት ላይ ሆኗል።

futbolprotez.cz

ቶተንሃሞች ብሩህ ተስፋን የሚሰጥ ነገር የላቸውም። በውድድር ዘመኑ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲን ካሸነፉበት ጊዜ አንስቶ ዋትፎርድ እና ቮልቭስ ላይ ድሎችን አስመዝግበዋል ፤ በቅርቡ ግን ያሸንፏቸዋል ተብለው በተጠበቁት የክሪስታል ፓላስ ቡድን 3-0 ተሸንፈዋል እና በኮንፈረንስ ሊግ ከሬኔስ ጋር 2 አቻ ወጥተዋል።

የሃሪ ኬን አጥጋቢ ያልሆነ እንቅስቃሴ ከሉካስ ሙራ እና ስቲቨን በርግዊን ጉዳት ጋር ተደምሮ የቶተንሃሙን አሰልጣኝ ኑኖ እስፒሪቶ ሳንቶን ሃሳብ ውስጥ መክተቱ አይቀርም።

ይህ ሁሉ ጨዋታው በቼልሲ ድል ይጠናቀቃል ብሎ ለማመን ምክንያት ሊሆን ይችላል ፣ ግን ይህ የሰሜን ለንደን ደርቢ እንደመሆኑ ቶተንሃምም ቀላል አይሆንም ፣ ያንንም ሻምፒዮኖቹ ማንችስተር ሲቲ ላይ አረጋግጠዋል።

የንጎሎ ካንቴ ከቁርጭምጭሚት ጉዳት መመለስም የቼልሲው አሰልጣኝ ቶማስ ቱቸልን ያስደስታቸዋል። ይህ ለሰማያዊዎቹ ጥሩ ማበረታቻ ይሆናል።

thetimes.com

ግምት

ቶማስ ቱቸል በሚታወቅበት ሃይለኛ እና አላማ ያለው ጨዋታ ቼልሲ ጠንካራ አጀማመር እንደሚያደርግ ይጠብቁ። ሆኖም ሳንቶ የመጀመሪያ ምርጫ የተከላካይ መስመሩን ካስገባ ቼልሲ ብዙ ግቦችን ሲያስቆጥር ይችላል ማለት ከባድ ነው። ሉካኩ ለሰማያዊዎቹ አንድ አስቆጥሮ የሚያሸንፉበት የቸልሲን የማጥቃት የበላይነት የምናይበትን ጨዋታ ይጠብቁ።

ቶተንሃም 0 – 1 ቼልሲ

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football