Connect with us
Express news


Football

ቀዮቹ በአንፊልድ በቀላሉ አሸንፈዋል!

An Easy Win for the Reds at Anfield!
liverpooloffside.sbnation.com

ሳዲዮ ማኔ ለክለቡ 100 ኛ ጎሉን አስቆጥሯል። እስካሁን ያልተሸነፈው ሊቨርፑል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ደረጃ አናት ላይ ይገኛል።

የየርገን ክሎፕ ሊቨርፑል ቡድን ሳዲዮ ማኔ ክሪስታል ፓላስን ለማሸነፍ 100 ኛ ጎሉን ለክለቡ ካስቆጠረ በኋላ በፕሪሚየር ሊጉ እስካሁን አልተሸነፈም።

ክሪስታል ፓላስ ጨዋታውን በጥሩ ሁኔታ ጀምረው ነበር። ሊቨርፑል ኳሱን ከራሱ ሳጥን ለማውጣት ሲታገል የፓትሪክ ቪዬራው የለንደን ቡድን በሁለት ደቂቃዎች ውስጥ ማእዘኑን ሁለት ጊዜ መተዋል። ሆኖም ሊቨርፑል ቆይቶ ምላሽ ሰጠ ግን በመጀመሪያው አጋማሽ ቀዮቹ አባካኝ ነበሩ። በመጀመሪያ ፣ ዲዮጎ ጆታ በሚያስደንቅ ሁኔታ ከጥቂት ሜትሮች ርቀት ከማእዘን በላይ ጠለዘ ፣ ከዚያ ቲያጎ እና ጆርዳን ሄንደርሰን እንዲሁ በፓላስ ግብ ጠባቂ ቪሴንቴ ጓአይታ ተመልሶባቸዋል።

heraldsun.com.au

ሆኖም ፓላስ ለረጅም ጊዜ እነሱን ማስቆም አልቻሉም። ለመጀመሪያው ግብ በ 43ኛው ደቂቃ ኮንስታንቲኖስ ፂሚካስ ከግራ በኩል ያሻማውን ኳስ ሳላህ በጭንቅላቱ ወደ ጎል ሞከረው ፣ ጓአይታ ግን አድኖታል ፣ ሆኖም ኳሱን ወደ ማኔ እግር በመትፋቱ እሱ በፍጥነት በማስቆጠር 1-0 ማድረግ ችሏል እናም በዛው 100 ኛው የሊቨርፑል ግቡን አግኝቷል!

ከዚያ ሞሃመድ ሳላ በ 78ኛው ደቂቃ ቨርጂል ቫን ዲይክን ከማእዘን ተሻምቶ የጨረፋትን ኳስ በማስቆጠር 2-0 አድርጎታል። ከዛም የሙሉ ሰአት ፊሽካ ከመነፋቱ ትንሽ ቀደም ብሎ ናቢ ኬታ ከሳጥኑ ውጪ ውብ ኳስ በግራ እግሩ አስቆጥሮ 3-0 ሆኗል።

thisisanfield.com

በመጨረሻም በአንፊልድ ለሊቨርፑል ጥሩ ሳምንት ነበር በተለይ በሳምንቱ አጋማሽ በቻምፒየንስ ሊጉ ኤሲ ሚላን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ካሸነፈ በኋላ።

ውጤቱ ሊቨርፑል ከ 5 ጨዋታዎች 4 አሸንፎ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ እንዲሆን አድርጓል ፣ ፓላስ ደግሞ በኢ.ፒ.ኤል ሰንጠረዥ ወደ 14 ኛ ዝቅ ብሏል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football