Connect with us
Express news


EFL Cup

ቼልሲ በፍፁም ቅጣት ምት አስቶንቪላን አሸነፈ!

Chelsea Edge Past Aston Villa on Penalties!
si.com

የካራባኦ ዋንጫ መደበኛ ጨዋታ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ከተጠናቀቀ በኋላ ቼልሲዎች በፍፁም ቅጣት ምት 4-3 አሸንፈዋል!

የቶማስ ቱቸሉ ቼልሲ ፣ ሬይስ ጄምስ የማሸነፍያውን ፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሮ ፣ አስቶን ቪላን ከውድድሩ ወጪ በማድረግ ወደ ምርጥ 16 ማለፍ ችለዋል። ተከላካዩ የሰማያዊዎቹን የመጨረሻ ቅጣት ምት በማስቆጠር 4-3 አሸንፈዋል።

የቼልሲው ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ ፣ አሽሊ ያንግ ለቪላ የግቡ አግዳሚ ከመለሰለት በኋላ የዚምባብዌውን የመሀል ተከላካይ ማርቨስ ናካምባን ፍፁም ቅጣት ምት በማዳን የምዕራብ ለንደኑ ቡድን ጀግና ሆኖ አምሽቷል።

ቲሞ ወርነር ፣ ጄምስ በ54ኛ ደቂቃ ያሻማዉን ኳስ ወደ ግብ በመቀየር ሰማያዊዎቹን ቀዳሚ አድርጓል። በዚያን ሰአት ጀርመናዊው በ 11 የቡድን ግጥሚያዎች ያስቆጠራት የመጀመርያ ግቡ ጨዋታውን በመደበኛ ጊዜ የሚያሸንፉ ይመስል ነበር እና ብዙም ሳይቆይ እንደገና ማስቆጠር ነበረበት ፣ ነገር ግን ከቅርብ ርቀት የመታዉን ኳስ ኢላማውን ያልጠበቀ ነበር።

skysports.com

በአስደናቂ ሁኔታ የተጫወተው የዲን ስሚዝ አስቶን ቪላ በ 64 ደቂቃዎች ላይ ካሜሮን አርቸር አየር ላይ ጥሩ ቴክኒክ አሳይቶ ባስቆጠረው የጭንቅላት ግብ የሚገባውን አቻ ውጤት አስመዝግቦ ነበር።

ባሮውን 6-0 ባሸነፉበት ጨዋታ ሃትሪክ የሰራው የ 19 ዓመቱ አጥቂ በዚህ የውድድር ዘመን በ 2 የኢ.ኤፍ.ኤል. ዋንጫ ጨዋታዎች 4 ግቦችን አስቆጥሯል። ሆኖም የመጨረሻው የፍፁም ቅጣት ምት ጨዋታ ለቪላ ልብ የሚሰብር ነበር።

knutsfordguardian.co.uk

ቱቼል ከጨዋታው በኋላ “ከባዱ ጨዋታ በማሸነፋችን ደስተኛ ነኝ ፣ እናም ለሌሎች ተጫዋቾች የመሰለፍ እድል ሰጥተናል” ብለዋል።

የረቡዕ ውጤት የቼልሲን የውድድር ዘመኑ ያለመሸነፍ ጉዞ ያስቀጠለ ነበር ፣ ይህም ከ 5 ጨዋታዎች 13 ነጥቦችን በመያዝ በፕሪሚየር ሊጉ 1 ኛ ደረጃን እንዲይዝ አስችሎታል። ሰማያዊዎቹ በስታምፎርድ ብሪጅ በ ምርጥ 16 ውስጥ ሳውዝሃምፕተንን ይገጥማሉ። ቼልሲ ከ 2014-15 የውድድር ዘመን በኋላ የኢ.ኤፍ.ኤል. ዋንጫ አላነሳም ፣ ነገር ግን በዚህ ዓመት ጥሩ ዕድል ያላቸው ይመስላል!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in EFL Cup