Connect with us
Express news


EFL Cup

አርሰናል በካራባኦ ዋንጫ ዊምብሌዶንን አሸንፎ አልፏል!

Arsenal Smash Wimbledon to Advance in the Carabao Cup!
goal.com

አርሰናል በካራባኦ ዋንጫ ዊምብሌዶንን 3-0 ማሸነፍ ችሏል።

አርሰናሎች ዊምብሌዶንን በአሌክሳንደር ላካዜት (11)) ፣ ኤሚል ስሚዝ-ሮው (77)) እና ኤዲ ንኬቲያ (80)) ጎሎች በሜዳቸው 3-0 አሸንፈው ወደ ጥሩ አቋም የመመለስ ተስፋ አሳይተዋል።

ጋብርኤል ማርቲኔሊ በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ከተጠለፈ በኋላ አሌክሳንደር ላካዜት በጣም ለተለወጠው እና ለ አዳዲስ ተጫዋቾች እድል ለሰጠው የመድፈኞቹ ቡድን የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥሯል።

ሆኖም መድፈኞቹ ሁለተኛ ግብ ቆይተው ነው ያስቆጠሩት ፤ የሊግ አንዱ ቡድን አጥብቆ ተከላክሏል። ተቀይሮ የገባው ኤሚል ስሚዝ-ሮው በመጨረሻ የተተፋፋ ኳስ በ77 ኛው ደቂቃ አስቆጠረ ከዚያ ኒኬቲያ በተረከዙ በማስቆጠር ድሉን አረጋገጠ።

arseblog.com

ድሉ በሁሉም ውድድሮች ለአርሰናል በተከታታይ ለሦስተኛ ጊዜ ሲሆን በሳምንቱ መጨረሻ ቶተንሃምን በሰሜን ለንደን ደርቢ ለመግጠም የሚያደርጉት ዝግጅት ያጠናክራል።

ከጨዋታው በኋላ የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በበኩላቸው “1-0 እስከሆንን ድረስ እነሱ አሁንም በጨዋታው ውስጥ ነበሩ እና እንደ ሁኔታው ግብ ሊያስቆጥሩ ይችላሉ ፣ ስለዚህ እኛ መዝጋት እንዳለብን አውቀን ነበር። እኛም ያንን አድርገናል እናም ቀለል ያለን ይመስል ነበር ፣ ግን ከባድ ጨዋታ ነበር።”

“በረቡዕ ምሽት በካራባኦ ዋንጫ 50,000 ደጋፊዎች መኖራቸው በጣም ልዩ ነው እና በብዙ ቦታዎች ላይ አይከሰትም። ተጫዋቾቹ ያንን አስተውለዋል እናም ይህ በግልጽ አበረታቷቸዋል። ምሽቱን የበለጠ ልዩ አድርገውታል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in EFL Cup