Connect with us
Express news


Football

ብሬንትፎርድ ከሊቨርፑል ጋር 6 ግቦችን ተጋርተዋል!

Brentford Share 6 Goals with Liverpool!
football365.com

ለቀዮቹ 3 ነጥቦችን ከብሬንትፎርድ ለመውሰድ የሞሐመድ ሳላህ 100 ኛ የፕሪሚየር ሊግ ግብ ብቻውን በቂ አልነበረም። ዮአን ዊሳ ለባለ ሜዳዎቹ ዘግይቶ የአቻነት ግብ አስቆጥሯል!

ብሬንትፎርድ ሊቨርፑልን በብሪንትፎርድ ኮሚኒቲ ስታዲየም ፣ ድንቅ በሆነ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ 3 ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት ገተው ይዘዋል ፣ ዮአን ዊሳ ሰዓቱ 82 ደቂቃ ሲል የአቻነት ጎል አስቆጥሯል።

ዊሳ አሊሰን ላይ በሚያምር ሁኔታ በመጨረስ ለአስተናጋጆቹ አንድ ነጥብ አስገኝቷል ፣ ሆኖም ከየርገን ክሎፕ የሊቨርፑል ቡድን ጋር ለረጅም ጊዜ በጥሩ ሁኔታ ተወዳድረው እና ሁሉንም 3 ነጥቦች ለመውሰድ የሚያስችላቸውን በቂ ዕድሎችን ፈጥረው ነበር።

የቶማስ ፍራንክ ቡድን የሚገባውን መሪነት ፣ ኢቫን ቱኒ የሰርጊ ካኖስ መሬት ለመሬት ያሻማውን ኳስ ወደ ኢታን ፒኖክ ከጨረፈው በኋላ ከቅርብ ርቀት ሲያስቆጥር አግኝቷል ። ፒኖክ ኳሷ ሰው ባልነበረበት የግብ መስመር ላይ ሲንከባለል በቀላሉ ለመጨረስ በትክክለኛው ቦታ ላይ የነበረ ሰው ነበር።

brentfordfc.com

ከዚያ ዲዮጎ ጆታ ከስድስት ያርድ ሳጥኑ ጠርዝ ጆርዳን ሄንደርሰን ያሻማውን ኳስ ወደ ጥግ በሃይል አስቆጥሯል። ያ ጎል በ 31ኛው ደቂቃ ላይ ውጤቱን 1-1 አድርጎታል።

በ 2 ኛው አጋማሽ 9 ደቂቃዎች ካለፉ በኋላ መሀመድ ሳላህ ለሊቨርፑል 100 ኛ የፕሪምየር ሊግ ግቡን በማስቆጠር ቀዮቹን በጨዋታው ለመጀመሪያ ጊዜ ቀዳሚ አድርጓል። ሆኖም ፖንቱስ ያንሰን የመታው ኳስ ከማእዘኑ ጋር ተጋጭቶ ከወረደ በኋላ ቪታሊ ጃኔልት በተፈጠረው ሽኩቻ ውስጥ እንደገና ማስቆጠር ችሏል።

ከርቲስ ጆንስ ከዚያ ከርቀት የመታው ኳስ በብሬንትፎርዱ ተከላካይ ክሪስቶፈር አጀር ተጨርፎ በመግባት የሊቨፑልን መሪነት ወደነበረበት መልሷል ፣ ግን የመጨረሻው የጨዋታው ግብ የብሬንትፎርድ ነበር!

standard.co.uk

አቻው ውጤት ሊቨርፑልን በፕሪሚየር ሊጉ አናት ላይ አንድ ነጥብ ከፍ አድርጎታል። በዚህ አመት በኢ.ፒ.ኤል. እስካሁን አልተሸነፉም። ብሬንትፎርድ ለትንሽ ለንደን ክለብ አጥጋቢ ከሆነ እንቅስቃሴ እና ውጤት በኋላ በ 9 ኛ ደረጃ ላይ ይቆያል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football