Connect with us
Express news


Football

ቅድመ -እይታ: የትልቅ ገንዘብ አውጪ ቡድኖች ፍጥጫ!

Preview: Battle of the Big Spenders!
marca.com

ማክሰኞ ምሽት ፓሪስ ሴንት ጀርሜን በቻምፒየንስ ሊጉ ማንችስተር ሲቲን ያስተናግዳል። መመልከት ያለብንን ነገሮች እነሆ!

ማክሰኞ ምሽት በምድብ አንድ ፒ.ኤስ.ጂ. የሻምፒዮንስ ሊግ ሽንፈቱን ለመበቀል በሚያደርገው ጨዋታ ፣ የማንቸስተር ሲቲ የሳምንቱ ሁለተኛ ፈታኝ ጨዋታ በ ፓርክ ዴስ ፕሪንሰስ ይደረጋል። ባለፈው የውድድር ዘመን የፔፔ ጋርዲዮላ ቡድን በቻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ በሁለቱም ደርሶ መልስ ጨዋታ ፒ.ኤስ.ጂን አሸንፈዋል ፣ ይህም የፒ.ኤስ.ጂ. የአውሮፓ ዋንጫ የማሸነፍ ህልም ቢያንስ በአንድ አመት አራዝሟል!

አንጄል ዲ ማሪያ ከጨዋታው በመታገዱ ምክንያት ፣ የፒኤስጂው አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ሊዮኔል ሜሲ ከ ሲቲ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ከአጥንት ጉዳት አገግሞ እንደሚሰለፍ ተስፋ አድርጓል። ሆኖም ፣ ይህ ጽሑፍ በሚፃፍበት ጊዜ ፣ የ 6 ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊ አሁንም ለዚህ ጨዋታ መሰለፉ በጣም አጠራጣሪ ነው።

ሰርጂዮ ራሞስ እና ማርኮ ቬራቲ እንዲሁ ለጊዜው እንደማይሰለፉ ይጠበቃል ፣ ነገር ግን ሁዋን በርናት ፣ ላይቪን ኩርዛዋ እና ኮሊን ዳግባ ሁሉም ወደ ልምምድ የተመለሱ ሲሆን ኢድሪሳ ጉዬ ከአውሮፓ እገዳ ተመልሷል።

sportingnews.com

ሜሲ ጨዋታዉን ለመጀመር ብቁ ካልሆነ ፣ ጁሊያን ድራክለር በቀኝ በኩል ሊመረጥ ይችላል ፣ ጂያንሉጂ ዶናሩማም በኪሎር ናቫስ ሊቀየር ይችላል።

ናታን አኬ አርቢ ሌፕዚግ ላይ ግብ በማስቆጠሩ ፣ በቦታው የመሰለፍ ፍልላጎት ይኖረዋል። ኢካይ ጉንዶጋን እና ኦለክሳንደር ዚንቼንኮ ለዚህ አስፈላጊ ጨዋታ በጊዜ ከትንሽ ጉዳቶች ማገገም ይችሉ እንደሆነ የምናየው ይሆናል።

marca.com

ባለፈው የውድድር ዘመን ከፒ.ኤስ.ጂ. ጋር ባሳየው እንቅስቃሴ ብዙ አድናቆት ያገኘው ፈርናንዲንሆ የሮድሪን የቅርብ ጊዜ የአካል ብቃት ስጋቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት በምርጥ 11 ሊገባ ይችላል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፌራን ቶረስ እና ራሄም ስተርሊንግ የፊት መስመርን ለመመራት ተስፋ አድርጓል።

በዓለም ላይ ትልቅ ወጪ የሚያደርጉ ቡድኖች ሲገናኙ ፣ የጨዋታዉን ውጤት መገመት ቀላል አደለም። ሆኖም ፒኤስጂ በሜዳው እየተጫወተ ከመሆኑ አንፃር ፓሪሲየኖች 2-1 ያሸንፋሉ ብለን እናስባለን።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football