Connect with us
Express news


Football

ቅድመ -እይታ: ፖርቶ በሜዳው ሊቨርፑልን ያስተናግዳል!

Preview: Porto Play Host to Liverpool!
mirror.co.uk

ሊቨርፑሎች ማክሰኞ ወደ ፖርቹጋል ይጓዛሉ። ይህንን አስደናቂ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ማን ያሸንፋል?

ሊቨርፑል ማክሰኞ ምሽት ከፖርቹጋሉ ቡድን ፖርቶ ጋር ለሚያደርገው የምድብ ሁለት ፍልሚያ ወደ ኢስታዲዮ ዶ ድራጋኦ ሲጓዝ ፣ ከ 2 ቱ የ 2021-22 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታው 2ቱን አሸንፎ መውጣት ይፈልጋል። የሴሪዮ ኮንሲዮ ቡድን ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር 0-0 በሆነ አቻ ውጤት የአውሮፓ ዘመቻውን የጀመረ ሲሆን ቀዮቹ በአንፊልድ ኤሲ ሚላንን አሸንፈዋል!

ቻንሴል ምቤምባ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር በነበራቸው ጨዋት ቀይ ካርድ አይቶ ከሜዳ መሰናበቱ ተከትሎ ፖርቶ ተከላክሎ እንዲጫወት አስገድዶታል። ከአትሌቲኮ በነበራቸው ጨዋታ በፔፔ ተቀይሮ ከሜዳ የወጣው ተጫዋች ፣ አርብ ከሞሪሬንስ ጋር ባደረገጉት የሊጉ ድልም መሰለፍ አልቻለም ነበር። የጡንቻው እብጠት ከዚህ ጨዋታም ሊያስቀረው ይችላል።

ስለዚህ ፋቢዮ ካርዶሶ እና ኢቫን ማርካኖ በመሃል ተከላካካይ ቦታ ሲጫወቱ ፣ ዌንዴል በግራ ተመላላሽ ቦታ ላይ ተሰልፎ ከቀዮቹ ጋር ይፋለማሉ። የፖርቶ 1 ኛ ምርጫ ግብ ጠባቂ አጉስቲን ማርቼሲን የውድድር ዘመኑን የመጀመርያ ጨዋታ የማድረግ እድል ይኖረዋል ተብሎ ይታሰባል።

ማርኮ ግሩጂች ከአትሌቲኮ ጋር ሙሉ 90 ደቂቃውን ከተጫወተ በኋላ ከቀድሞው ቡድኑ ጋር ይጫወታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፤ ሴሪዮ ኦሊቬራ ፣ በኮንቺያኦ የመሃል መስመር ላይ ለመሰለፍ ከማቴዎስ ኡሪቤ ጋር የሚፎካከር ይመስላል።

tivela.fr

የሊቨርፑል ጥንድ ናቢ ኬታ እና ቲያጎ አልኮንታራ ምናልባት ከዓለም አቀፉ ዕረፍት በኋላ ከ ሃርቪ ኤሊዮትን ጋር በሕክምና ክፍል ውስጥ ይቆያሉ ፣ ኒኮ ዊሊያምስ ደግሞ በቁርጭምጭሚት ጉዳት ምክንያት የመሰለፉ ነገር አጠራጣሪ ነው።

ጀርገን ክሎፕ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ከሚደረገው ጨዋታ በፊት ቢያንስ 2 ለውጦችን እንደሚያደርግ ይጠበቃል ፣ ታኪሚ ሚናሚኖ እና ኮስታስ ሲሚካስ ሁለቱም በግራ በኩል ቦታቸውን ለማስጠበቅ ተስፋ አድርገዋል።

ሮቤርቶ ፊርሚኖ ወደ ሙሉ አቋሙ በመመለሱ ምክንያት በአጥቂ ክፍሉ ዲያጎ ጆታን ሊተካ ይችላል ፣ ኩርቲስ ጆንስ እና ጄምስ ሚልነር በአማካይ መስመር ለመሰለፍ ይፎካከራሉ።

ሊቨርፑል 3-1 ያሸንፋል ብለን እናስብባለን! ፖርቶዎች የሊቨርፑል የአጥቂ መስመር መስመር መቋቋም የሚከብዳቸው ይመስለናል!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football