Connect with us
Express news


Boxing

ኦሌክሳንደር ዩሲክ ፣ አንቶኒ ጆሽዋን በማሸነፍ አዲሱ የዓለም የከባድ ሚዛን ሻምፒዮን ሆነ።

New World Heavyweight Champion as Oleksandr Usyk Defeats Anthony Joshua!
CBSsports.com

ኦሌክሳንድር ዩሲክ በለንደን 67,000 ተመልካቾች በታደሙበት ጨዋታ አድካሚ ፍልሚያ ካደረገ በኋላ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አሸንፏል።

ለዚህ የቦክስ ውድድር መቀመጫዎች እስከ 10 ሺህ የእንግሊዝ ፓውንድ ይሸጡ ነበር ፣ እናም ጨዋታውን የሚመጥን ወጪ ነበር።

ኦሌክሳንድር ዩሲክ ግልፅ እና በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አንቶኒ ጆሽዋን በማሸነፉ እና ለዓለም እጅግ አስደናቂ የሆነ ክህሎት በማሳየት ፣ የዓለማችን አዲሱ የ ደብሊው.ቢ.ኤ ፣ የ ደብሊው.ቢ.ኦ እና የ አይ.ቢ.ኤፍ የከባድ ሚዛን ሻምፒዮን መሆን ችሏል። የቀድሞው የዓለም የ ክሩሰር ሚዛን ሻምፒዮን ፣ ምንም ሽንፈት ያላስተናገደው እና ከጆሽዋ የበለጠ ተፈጥሯዊ ተጫዋች እና የበለጠ ተሰጥኦ አለው ተብሎ የሚታሰበው ዩክሬናዊው ተፋላሚ ፣ የዓለም ሻምፒዮኑን በመፋለም አቋሙን ማስመስከር ነበረበት።

sportsillustrated.com

ዩሲክ በመክፈቻው ዙር ፤ በጥሩ የግራ እጅ ማጥቃት ፣ በእግሮቹ ጥሩ ምት በመሰንዘር ፣ እና ምንም የማጥቃት ክፍተት ባለመስጠት አሪፍ አጀማመር አሳይቷል። ዩክሬናዊው ወደ ኋላ ከመመለስ እና በርቀት ከመፋለም ይልቅ በሜዳው መሃል ላይ ቆሞ ሲፋለም ነበር ፣ የበለጠ ሰውነት ያለዉን አንቶኒዮ ጆሽዋ የሚያደናግር እንቅስቃሴ በማሳየት ይህንን ፍልሚያ ጀምሯል። እንቅስቃሴው በሦስተኛው ዙር ነበር የጀመረው እናም ጆሽዋን በግራ ምት በመደብደብ ፣ ጭንቅላቱ እንዲያብጥ እና የተደናገጠ እይታ በዓይኖቹ ውስጥ እንዲታይ አደረገው።

ጆሽዋ ፣ የዩሴክ በሚያሳያቸው ጥሩ የፍልሚያ ስልት አጠቃቀም እና አስገራሚ እንቅስቃሴዎች መረጋጋት አልቻለም ነበር ፣ እናም ፍልሚያው በቀጠለ ሰኣት ሻምፒዮኑ እየከበደው መሆኑ ግልፅ ነበር። በግራ ዐይኑ ዙሪያ እብጠት ተፈጥሯል እናም ራሱን ለማበረታታት አሰልጣኙ ሮበርት ማክራከን ያስፈልገው ነበር።

በመጨረሻዎቹ ዙሮች ላይ ጆሽዋ ቀላል ድብደባዎች ብቻ ነበር ማድረስ የቻለው ፣ ነገር ግን ዩሲክ ማጥቃቱን ሲቀጥል በጣም ተዳክሞ ነበር። በአደገኛ ድብደባ እና በአሰቃቂ የቀኝ እጅ ጉዳት፣ ዩሲክ ጆሽዋን ወደ ኋላ እንዲሸሽ አስገደደው ፣ እናም ሻምፒዮናው ወደ ፊቱ የሚሰነዘሩ ጥቃት ማየት እስከማይችልበት ደረጃ በጣም ተዳክሞ ነበር።

በ 12 ኛው ዙር ፣ ጆሽዋ በገመዱ ሲደገፍ ነበር ፣ ተስፋ በመቁረጥም ከ 220 ፓውንድ ዩክሬናዊው ያነሰ ኃይል እና ጠበኝነት ነበረው።

በመጨረሻው ሰከንዶች ውስጥ ጆሽዋ ፣ ዩሲክን ለመደብደብ ሙከራ ቢያደርግም ሊሳካለት አልቻለም እናም ዳኞቹ ዩሲክ 117-112 ፣ 116-112 እና 115-113 በሆነ ውቴት አሸነፏል በማለት ወሰኑ። ዓለምም ከአዲስ የከባድ ሚዛን ሻምፒዮና ጋር ተዋወቀች።

ምንም እንኳን ጆሽዋ ወደ ሆስፒታል ባይሄድም በአሰቃቂው ሽንፈት በዓይኑ አከባቢ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል።

guardian.org

የዩሲክ አስደናቂ ድል የህይወት ዘመኑ ትልቅ ስኬት ነበር። የጆሽዋ ቡድን ዩሲክን በማሽሸነፍ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው በሁለቱ የብሪታንያ ተፋላሚዎች መካከል ፣ ከታይሰን ፉሪ ጋር መፋለም ያስከትላል ብለው ያምኑ ነበር ፣ ነገር ግን በዚህ ሰአት ‹አንቶኒ ጆሽዋ› የዓለም ሻምፒዮን አይደለም ፣ እናም ዩሲክ ይህንን አስደናቂ ድል ካስመዘገበ በኋላ የከባድ ሚዛን ቦክሲንግ በተጨዋቹ በጣም ተደንቀዋል።

ለሁለቱም ተፋላሚዎች ብዙ ገንዘብን የሚያስገኝላቸው የመልስ ጨዋታ እየታሰበ ነው ፣ ነገር ግን ጆሽዋ እንደገና ለመፋለም በቂ የአካል እና የአዕምሮ ብቃት እስኪያገኝ ድረስ ትንሽ ጊዜ ሊወስድ ይችላል!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Boxing