Connect with us
Express news


Football

በማድሪድ ውስጥ የሞልዶቫውያኑ አስገራሚ ድል!

Moldovan Madness in Madrid!
marca.com

ሪያል ማድሪድ በሜዳው በትንሹ የሞልዶቫ ቡድን የ 1-2 ሽንፈት ደርሶበታል። ቤንዜማ ያስቆጠራት ፍፁም ቅጣት ምት ፣ በሜዳቸው በ ሞልዶቫ ሻምፒዮናዎች የደረሳቸውን የ 1-2 አሳፋሪ ሽንፈት ለመቀልበስ በቂ አልነበረችም!

በውድድሩ አነስተኛ ልምድ ያለው ቡድን ሸሪፍ ቲራስፖል ፣ የ13 ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮን ሪያል ማድሪድ በበርናባው ውስጥ በማሸነፍ እጅግ የላቀውን የ ዩኤፋ ቻምፒየንስ ሊግ (ዩሲኤል) ፣ የምን ጊዜም ያልተጠበቀ ውጤት አስመዝግበዋል።

ሴባስቲያን ቲል ፣ በመጨረሻው ደቂቃ አስደናቂ ግብ አስቆጥሮ የ ዩሪ ቨርኒዱብ ቡድን እንዲያሸንፍ አድርጓል ፣ ይህንን ተከትሎም የሞልዶቫ ሻምፒዮናዎች ደስታቸው በሚያስደንቅ ሁኔታ ገልፀዋል ።

ቀደም ሲል የጃሱርቤክ ያክሺቦቭ የመጀመሪያ አጋማሽ ግብ መሪነቱን እንዲይዙ አስችሏቸዋል። ክሪስቲያን ዳ ሲልቫ ውብ ኳስ ካሻማለት በኋላ በአስደናቂ ሁኔታ በጭንቅላቱ ወደ ታች በመምታት ፣ በማድሪዱ ግብ ጠባቂ ቲባው ኩርቱኦ ላይ ግብ አስቆጥሯል።

ከዚያም ካሪም ቤንዜማ ለ ካርሎ አንቸሎቲው ቡድን ፍፁም ቅጣት ምት በማስቆጠር ውጤቱ 1 ለ 1 አድርጎታል። ፍፁም ቅጣቱ ምናልባት ትንሽ አጠራጣሪ ነበር። በቪኒሺየስ ጁኒየር ላይ በአዶ እና በፔይሶቶ ኮስታዛ ጥፋት የተሰራ ብዙ አይመስልም ነበር ፣ ነገር ግን በ ቫር ከታየ በኋላ በማድሪዱ የፊት መስመር ላይ ፍፁም ቅጣት ምት የሚያሰጥ ጥፋት እንደተፈፀመ ተወስኗል።

managingmadrid.com

ሆኖም የቲል ግብ አስደናቂውን ድል ለማስመዝገብ በቂ ነበረች። የሉክሰምቡርግ ተጫዋች በ 89 ደቂቃ የአየር ላይ ኳስ በማስቆጠር የባለ ኤዳዎቹ ደጋፊ አፍ አስይዟል።

ቲል ከጨዋታው በኋላ “የህይወት ዘመኔ ምርጥ እና በጣም አስፈላጊ ግብ ነበር። ተጋጣሚያችን ቡድን በጣም ከባድ ነበር እና እንደ እድል ሆኖ አስገራሚ ግብ ማስቆጠር ችያለው። ከዚህ ግጥሚያ በኋላ ሁላችንም አብደናል። በቡድኑ ውስጥ ብዙ የውጭ ተጫዋቾች አሉ ፣ ከሁሉም ሀገሮች የተውጣጣን ነን። ይህ የእኛ ጥንካሬ ነው ” ብሏል።

ከ 580 ቀናት በኋላ በርናባው ለመጀመርያ ጊዜ የ ዩሲኤል ጨዋታ ያስተናገደው ሪያል ማድሪድ የጠበቀው ውጤት አልነበረም። ሪል በተለምዶ ከእግር ኳስ ብቃት ጋር ባልተዛመደ የአንድ ሀገር ሻምፒዮናዎች ተዋርደዋል እናም የ ሸሪፍ ደጋፊዎች ጩኸት ለዚህ የማይታመን ሽንፈት የድምፅ ማጀቢያ ነበር!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football