Connect with us
Express news


Basketball

በስፖርት አለም ውስጥ ከፍተኛ ተከፋይ ጀግኖች!

The Most Highly-Paid Heroes in Sport!
thesun.co.uk

ሜሲ እና ሮናልዶ ከመሳሰሉት እግር ኳስ ተጫዋቾች ውጪ ፣ በዓለም ላይ ከፍተኛ ደመወዝ ተከፋይ አትሌቶች እነማን ናቸው?

ሮጀር ፌዴሬር – (ቴኒስ ፣ የ 2020 ገቢ – 90 ሚሊዮን ዶላር)

ሮጀር ፌዴሬር በ 2020 አብዛኛው ጊዜ በጉልበት ጉዳት ምክንያት ቢርቅም እንደ ሮሌክስ ፣ ክሬዲት ሱይሴ እና ዩኒክሎ ካሉ ብራንዶች በስፖንሰር 90 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቷል። የስዊሱ የቴኒስ ተጫዋች ትልቁ የገቢ ምንጭ ፣ በ 2021 የመጀመሪያ የአክሲዮን ሽያጭ በቅርቡ የሚያስተዋውቀው የስዊስ የአትሌቲክስ አልባሳት ኩባንያ ላይ ካለው ድርሻ ፣ ሊመጣ ይችላል!

ሌብሮን ጄምስ – (የቅርጫት ኳስ ፣ የ 2020 ገቢ – 96.5 ሚሊዮን ዶላር)

skysports.com

2020 ለሌሊሮን ጄምስ የስኬት ዓመት ነበር። በጥቅምት ወር 4 ኛ የ ኤን.ቢ.ኤ. ዋንጫዉን አሸንፏል እናም የ 36 ዓመቱ ተጫውች በሜዳው ምርጥ አቋም በማሳየት በሳምንት 1.8 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት ችሏል። ከቅርጫት ኳስ ውጪ የረጅም ጊዜ አጋሩ የነበረውን ኮካኮላን ለቆ  ከ ፔፕሲኮ ጋር አዲስ ውል ፈርሟል። እንዲሁም የቦስተን ሬድ ሶክስ ፣ የሊቨርፑል እግር ኳስ ቡድን እና የሮሽ ፌንዌይ ውድድር ያካተተ የ ፌንዌይ ስፖርት ግሩፕ ውስጥ አነስተኛ ድርሻ ገዝቷል።

ዳክ ፕሬስኮት – (የአሜሪካ እግር ኳስ ፣ የ 2020 ገቢ – 107.5 ሚሊዮን ዶላር)

ከዳክ ፕሬስኮት የ 4 ዓመት በ 160 ሚሊዮን ዶላር የኮንትራት ማራዘሚያ ጋር ተያይዞ የመጣው የ 66 ሚሊዮን ዶላር የመፈረም ጉርሻ ፣ የዳላስ ካውቦይሱ ተጫዋች ከ 100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሀብት የሰበሰበ ተጫዋች ያደርገዋል። ከ ቴክሳስሱ ቡድን በሳምንት በግምት 604,000 ዶላር ያገኛል። ስፖንሰሮቹ ደግሞ ስሊፕ ነምበር ፣ 7/11 እና ዲሬክ ቲቪ የመሳሰሉ ናቸው። ፕሬስኮት መጠነ-ሰፊ የስፖርት ምግብ ቤት ኢንቨስትመንት አለው።

ኮነር ማክግሪጎር – (ኤም.ኤም.ኤ. ፣ የ 2020 ገቢ- 180 ሚሊዮን ዶላር)

ኮነር ማክግሪጎር በጥር ወር በ ዩ.ኤፍ.ሲ. 257 መሳተፉ ምናልባት ያሰበውን ድል ማሳካት አልቻለም ነበር። ማክግሪጎር ከጥር 2020 በኋላ የመጀመራ የዩ.ኤፍ.ሲ. ፍልሚያውን በደስቲን ፖሪየር ቢሸነፍም በግምት ወደ 22 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ሰብስቧል! ሆኖም ብዙ ሀብት ያካበተው ፤ ድራፍትኪንግስ ፣ ዲስቶፒያ ቪዲዮ ጨዋታውን የሚያካትት ፕሮፐር ቁ. አስራ ሁለት የዊስኪ ምርት መሸጡ ነበር። ይህም የዓለማችን ሀብታም አትሌት ያደርገዋል!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Basketball