Connect with us
Express news


Football

የቻምፒዮንስ ሊግ ቻምፒዮን? -ክፍል ሁለት

Champion of the Champions League? – Part II
fotbalportal.cz

በዚህ መደምደሚያ ክፍል በዚህ አመት ለአውሮፓ ክብር የሚጠበቁትን ቡድኖች ትንተና ላይ ፣ ሁለቱን ዋና ተጠባቂዎች እንመለከታለን!

ማንችስተር ሲቲ

በአውሮፓ ውስጥ ለበርካታ አመታት ተስፋ አስቆራጭ እንቅስቃዎችን ካደረገ በኋላ ማንቸስተር ሲቲ በ 2021 ለቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ጨዋታ ደርሷል ፣ ቢሆንም በፕሪሚየር ሊግ ተቀናቃኙ ቼልሲ አናዳጅ ሽንፈት ደርሶበታል። በዚህ አመትም የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን ለዩሲኤል ስኬት ከግንባር ቀደም ተፎካካሪዎች መካከል አንዱ ነው። እንዲሁም ከአስቶንቪላ ጃክ ግሪልሽን በ 100 ሚሊዮን ሪከርድ በማስፈረማቸው አማራጮቻቸውን ጨምረዋል። የሚታወቅ አጥቂ አለመኖር አንዳንድ የጥያቄ ምልክቶችን ቢያነሳም ፣ ግን በአውሮፓ እግር ኳስ ውስጥ ከጋርዲዮላ ማንቸስተር ሲቲ ጋር የሚስተካከል ተሰጥኦ እና ጥልቀት ያላቸው ቡድኖች ጥቂት ናቸው!

eurosport.com

ሆኖም ሲቲዎች ከውድድሩ የመጀመሪያ ደረጃዎች ጀምሮ ምርጥ አቋም ላይ መሆን አለባቸው ፣ ሆኖም ግን ከ ፒኤስጂ ፣ ከ ሌፕዚግ እና ከክለብ ብሩጅ ጋር በውድድሩ የሞት ምድብ ውስጥ ይገኛሉ። አርቢ ሊፕዚግን ካሸነፉ በኋላ የመጀመሪያዎቹ ምልክቶች ጥሩ ናቸው ፣ ግን ሲቲ አሁን ትልቁን የምድብ ፈተና ከፒኤስጂ ጋር ዛሬ ምሽት በፓርክ ዴ ፕሪንስ ያደርጋል!

ፓሪስ ሴንት ጀርሜን

የፒኤስጂ አስገራሚ የዝውውር መስኮት ፓርሲያውያኑን ዩሲኤል አሸናፊ ለመሆን ተመራጭ አድርጓቸዋል ፣ ሊዮኔል ሜሲን ማስፈረማቸው ከክረምቱ ትልቅ ዜናዎች መካከል አንዱ ነበር። የ 6 ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊውን ወደ ፈረንሣይ ሲዘዋወር ከቀድሞው የባርሴሎና አጋሩ ኔይማር ጋር ያገናኘዋል ፣ እና ኪሊያን ምባፔ ይሄን የፊት መስመርን ያሟላል። አንድ ላይ ሆነው በዓለም እግርኳስ ውስጥ እጅግ በጣም አስገራሚ የአጥቂ መስመር ሊፈጥሩ ይችላሉ!

cbarcelonanoticias.com

ሰርጂዮ ራሞስም በነፃ ዝውውር ፈርሟል እናም ተከላካዩ በአውሮፓ ተከታታይ አሸናፊ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የጆርጂንዮ ዋንያልደም ፣ ጂያንሉጂ ዶናሩማ እና አችራፍ ሀኪሚ መምጣት በቡድኑ ቁልፍ ቦታዎች ላይ ጥራትን ጨምሯል። የሞሪሺዮ ፖቼቲኖ ፒኤስጂ ተጠባቂ የሆኑት በምክንያት ነው። ፓሪሲያውያኑ በሁሉም የሜዳ አከባቢዎች አስደናቂ ተሰጥኦዎች አሏቸው እናም በእርግጠኝነት በውድድሩ የመጨረሻ ደረጃዎች ላይ ተፈታታኝ ይሆናሉ!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football