Connect with us
Express news


Football

ማንችስተር ዩናይትድ በቻምፒየንስ ሊግ ቪላሪያልን ባሸነፉበት ጨዋታ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሽርፍራፊ ሴኮንድ የማሸነፊያዉን ግብ አስቆጥሯል!

Cristiano Ronaldo Scores Injury-Time Winner as Manchester United beat Villarreal in Champions League!
standard.com

ሮናልዶ በ 95 ኛው ደቂቃ ግብ በማስቆጠር ማንችስተር ዩናይትድን በአስደናቂ ሁኔታ በሜዳው 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ቪላሪያል በፍፁም ቅጣት ምት ያሸነፈው ያለፈው የውድድር ዘመን የኢሮፓ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በተደገመበት ምሽት ፣ ዩናይትድ ሌላ ደካማ አቋም ያሳየብርትን ግጥሚያ በአቻ ውጤት የሚጠናቀቅ ይመስል ነበር። በጣም ቀርፋፋ ነበሩ ፣ እና ደካማ የመከላከል አቅማቸው የዩናይትድ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴሃ ብዙ ሥራ እንዲሠራ አስገድዶታል። ነገር ግን የክረምት ፈራሚው ሮናልዶ ከጄሴ ሊንጋርድ የተቀበለውን ኳስ በማስቆጠር በ ኦልድትራፎርድ ውስጥ አስደሳች ትዕይንቶችን አምጥቷል!

ደጋፊዎች በስታዲየሙ ዙሪያ ጩከታቸውን አሰሙ ፣ እናም ሮናልዶ የኢከር ካሲላስን ሪከርድ በመስበር በ 178 ኛው የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታው ማሊያውን በማውለቅ ደስታዉን ገልጿል።

sportindia.com

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በ 95 ኛው ደቂቃ በቪላሪያል ላይ አስቆጥሮ ያስገኘውን ድል ፣ በአራት ግጥሚያዎች ሶስት ሽንፈቶችን በማስተናገዳቸው ምክንያት በአሰልጣኙ ላይ የነበረዉን ጫና ቀንሷል ፣ ኦሌ ጉናር ሶልሻየር ለማንችስተር ዩናይትዱ “ትልቅ ክስተት” አስመዝግቧል።

ዩናይትዶች ፣ በመክፈቻው ሰባት ደቂቃዎች ውስጥ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ወደ ላይ ያሻማዉን ኳስ ሮናልዶም ኢላማዉን ያልጠበቀ ኳስ በጭንቅላቱ በመግጨት ፣ጥሩ አጀማመር አሳይተዋል።

ቪላሪያል ከዚያ በኃላ የበላይነቱን ወስዷል ነገር ግን በመጀመሪያው አጋማሽ ብዙ እድል ከፈጠሩ በኋላ ግብ ማስቆጠር አልቻሉም። የዩናይትዱ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴሃ የ አርኖትን ዳንጁማ ፣ ፓኮ አልካሰርን እና የዬረሚ ፒኖንም ሙከራዎች በአስደናቂ ሁኔታ አክሽፏል።

theathletic.com

ራፋኤል ቫራን የ ኳሱን መነሳት በተሳሳተ መንገድ ለመመለስ በሚሞክርበት ጊዜ የቪላሪያሉ አጥቂ አልካሰር ግብ ማስቆጠር ነበረበት እና አልቤርቶ ሞሪኖ እና ፒኖ ሁለቱም ተስፋ ሰጭ ከሆኑት አሪፍ ሙከራ አድርገው ነበር።

ነገር ግን በሁለተኛው አጋማሽ የመጀመርያዎቹ ደቂቃ ላይ ዳንጁማ ኳሱን ወደ ኋላ መልሶ ያሻማዉን ኳስ አልካሰርን ከቅርብ ርቀት ግብ ማስቆጠር ችሏል።

ዩናይትድ የ ቪላርያል ተከላካዮችን አልፎ መግባት ተቸግሮ በነበረበት ሰአት ፣ አሌክስ ቴሌስ ከ 20 ያርድ ርቀት ላይ የተሻማለትን የአየር ኳስ ወደ ታችኛው የግቡ ጥግ በማስቆጠር አቻ እንዲሆኑ አድርጓል።

የሮናልዶ የማሸነፊያ ግብ ፣ የኦሌ ጉናር ሶልሻየር ቡድን በምድቡ ውስጥ የመጀመሪያውን ድል እንዲያሳካ አድርጋለች ፣ በሌላኛው የምድቡ ጨዋታ ደግሞ አትላንታ ያንግ ቦይስን 1 ለ 0 በማሸነፍ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ተቀምጠዋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football