Connect with us
Express news


Football

ባርሴሎና በቻምፒዮንስ ሊጉ በቤኒፊካ ተሸነፈ!

Barcelona Dominated by Benfica in the Champions League!
UEFA.com

የጆርጅ ጀሱስ ቡድን ፣ ከ 60 ዓመት በኋላ ረቡዕ ምሽት በተደረገው የቻምፒየንስ ሊግ ግጥሚያ ፣ የካታላኑን ግዙፍ ቡድን ባርሴሎናን 0-3 አሸንፈዋል።

ከ 1961 ጀምሮ ባርሴሎናን በጭራሽ አሸንፎ የማያውቀው ቤንፊካ ይህንን ስታቲስቲክስ እና የሮናልድ ኮማን ተጫዎቾችን እንደሚያሸንፉ አውቀው ወደ ኢስታዲዮ ዳ ሉዝ ገብተዋል።

የእነሱ በራስ መተማመን በስታዲየሙ ዙሪያ ታይቷል ፣ እናም ዳርዊን ኑኔዝ የ ፖርቹጋሉ ቡድን ግብ ለማስቆጠር ሶስት ደቂቃዎችን ብቻ ወስዶበታል።

ከዚያ በኋላ ራፋ ሲልቫ ሁለተኛዉን ግብ ካስቆጠረ በኋላ ፣ ኑኔዝ የሁለተኛው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 11 ደቂቃዎች ሲቀሩት 3ኛዉን አክሏል ፣ ይህም ባርሴሎና በምድብ አምስት የመክፈቻ ጨዋታ በባየር ሙኒክ የተሸነፈበትን የውጤት ልዩነት ጋር እኩል ነበር።

FCbarcelona.cz

ባርሳ 0-3 ብቻ በመሸነፍ እድለኛ ነበር። ምንም የግብ ጫና ሳይፈጥሩ ኳሱን ያለማቋረጥ ሲቀባበሉ ነበር ፣ እናም ኦፕታ የመዘገበውን ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ በጣም አስገራሚ እና የሚረሳ ነበር።

እ.ኤ.አ. በ 1992 የአውሮፓ ዋንጫን ያነሳው የባርሴሎና ቡድን አካል የነበረው የባርሴሎና አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን “ስለ ቡድኔ ደረጃ አልከራከርም” ብለዋል።

“ይህ ስብስብ ካለፉት የባርሴሎና ቡድኖች ጋር ማወዳደር ምንም ፋይዳ የለውም። ምክንያቱም ይህ ግልፅ ነው። እኔ በቡድኔ ውስጥ ስላለው ሥራ ያለኝን አስተያየት ብቻ ልሰጥዎት እችላለሁ – በተጫዋቾቼ እና በአመለካከታቸው ድጋፍ እንደሰጡኝ ይሰማኛል።

ከ ሁለት ግቦቹ በተጨማሪ ፣ ኑኔዝ ከቦታው ለመውጣት በችኮላ ውሳኔ የወሰደውን የባርሴሎናውን ግብ ጠባቂ ማርክ-አንድሬ ቴር ስቴገንን አጥፎ ካለፈ በኋላ የግቡ ጠርዝ የመለሰለትን አስደናቂ ሙከራ አድርጓል።

ሉክ ዲ ጆንግ በመጀመሪያው አጋማሽ የመጀመርያው ደቂቃ ውስጥ ክፍት የሆነ ግብ የማስቆጠር እድል አባክኗል።

https://www.onmanorama.com/

ነገር ግን ባርሳ አንድ ዒላማው የጠበቀ ሙከራ ብቻ አስመዝግቦ ኤሪክ ጋርሺያ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሶስት ደቂቃዎች ሲቀሩት በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

ኮማን “ቤንፊካ ጠንካራ የ አካል ብቃት ነበራቸው እናም በጣም ፈጣን ናቸው። ለመጀመሪያው እና ለሁለተኛ ግብ እንዳይቆጠሩ በደንብ መከላከል የነበረብን ይመስለኛል” ብሏል።

“በእውነቱ ጥሩ ግብ የማስቆጠር እድሎች ነበሩን እና የጨዋታውን አቅጣጫ እንዲህ ነው መቀየር የሚቻለው። ቤኔፊካ በእውነቱ የፈጠሯቸውን ጥቂት ዕድሎች ወደ ግብ መቀየር መቻላቸው በ ሁለቱ ቡድኖች መካከል የነበረውን ትልቅ ልዩነት ያሳየ ነበር።”

ባርሴሎናዎች ፣ ሁለቱንም የመክፈቻ ጨዋታዎች በሰፊ የግብ ልዩነት በመሸነፍ በሻምፒዮንስ ሊግ ታሪካቸው በጣም መጥፎ ጅማሮ አድርገዋል ።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football