Connect with us
Express news


Bundesliga

የቡንደስሊጋ ደርቢዎች! – ክፍል ሁለት

Bundesliga Battles! – Part II
bavarianfootballworks.com

በዚህ የመጨረሻ ክፍል የቡንደስሊጋ ደርቢዎች ተከታታይ ፅሁፋችን ፣ በጀርመን ከፍተኛ-ሊግ ውስጥ በጣም ከፍተኛ ተፎካካሪ ቡድኖችን እንመለከታለን!

ዴር ክላሲከር – ባየር ሙኒክ ከ ቦሩሲያ ዶርትመንድ

በእነዚህ ቡድኖች መካከል ለመጀመርያ ጊዜ እርስ በእርስ በሚጫወቱበት ጊዜ ብዙም ፉክክር አልነበረም። ነገር ግን በአሁኑ ሰአት ዴ ክላሲከር በጀርመን እግር ኳስ ውስጥ በጣም ተጠባቂ ጨዋታ ሊሆን ይችላል። ሁለቱ ቡድኖች በ 2010 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ከፍተኛ ፉክክር አሳይተዋል። በዚህ ወቅት ከተደረጉ ጨዋታዎች መካከል በጀርመን ካፕ የዋንጫ ጨዋታ ቦርሲያ ዶርትመንድ 5-2 ድል ያስመዘገበበት ጨዋት አንዱ ነበር!

ሆኖም ፣ በጣም የማይረሳው ጨዋታ በዌምብሌይ የተድደረገው የ 2013 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ መሆን አለበት ፣ ይህም በታሪክ የጀርመን ቡድኖች ለመጀመርያ ጊዜ በቻፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የተፋጠጡበት ጨዋታ ነበር። በ 1-1 አቻ ውጤት ሊጠናቀቅ የተቃረበዉን ጨዋታ ፣ አርያን ሮበን በሽርፍራፊ ሴኮንድ ውስጥ ግብ በማስቆጠር ከ የካቲት 2010 በኋላ ሙኒኮች የመጀመርያ የ ደር ክላሲኬር ደርቢ ድል እንዲያስመዘግቡ አድርጓል!

ለመጨረሻ ጊዜ በዶርትመንድ ሜዳ በተገናኙበት ጨዋታ ባየርን 3-1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል!

ዘ ሪቨር ደርቢ  – ሻልክ 04 እግር ኳስ ቡድን ከ ቦርሲያ ዶርትሙንድ

kurzovesazeni.com

ይህ በጀርመን እግር ኳስ ውስጥ በጣም የጦፈ ግጥሚያ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም! ከጌልሰንኪርቼን እና ከዶርትሙንድ በተገኙት ቡድኖች መካከል የተደረጉት ጨዋታዎች ሁል ጊዜ ከባድ ፉክክር አላቸው። ሁለቱ ስታዲየሞች ከ 40 ኪሜ ባነሰ ርቀት ላይ ይገኛሉ ፣ ሻልከ እና ዶርትሙንድ በጀርመን የእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ የማይረሱ አንዳንድ ጨዋታዎችን አስተናግደዋል። ሁለቱም ቡድኖች እርስ በእርሳቸው ዋንጫ የማንሳት እድል አበላሽተዋል ፣ እናም ሁለቱም ከመመራት ተነስተው የማይረሱ ድል አስመዝግበዋል።

በመስከረም 2008 ዶርትሙንድ ከ 0-3 መመራት ተነስተው በ 21 ደቂቃ ውስጥ 3 ግቦችን አስቆጥረው የ 3-3 አቻ ውጤት አስጠብቀዋል። ሻልከ በህዳር 2017 በበለጠ አስገራሚ ሁኔታ አፀፋዉን መለሰ! ሻልክ በ 25 ደቂቃዎች ውስጥ 4 ግቦችን ከተቆጠሩባቸው በኋላ በሁለተኛው አጋማሽ በልበ ሙልነት እና በወኔ ተጫውተው በሽርፍራፊ ሴኮንድ ባስቆጠሩት ግብ ከዶርትመንድ 2 ነጥቦችን በመውሰብ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል!

ባለፈው ግጥሚያቸው ዶርትሙንድ በሜዳቸው 3-0 አሸንፈዋል!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Must See

More in Bundesliga