Connect with us
Express news


Football

የአውሮፓ ሊግ ማጠቃለያ!

Europa League Round-Up!
getfootballnewsfrance.com

ሐሙስ ምሽት የተደረጉ የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ሁሉም ውጤቶች እና መነጋገሪያ ነጥቦች እንመለከታለን!

ምድብ አንድ

ሊዮን 3 – ብሮንድባይ አዪኤፍ 0

የ ካርል ቶኮ ኤካምቢ ሁለት ግብ እና ሆሴም ኦውር አንድ ግብ አስቆጥረው በሊዮን ውስጥ የፈረንሣዩ ቡድን የ ዴንማርኩ ቡድንን አሸንፈዋል። ለስ ጎነቹ አሁን 6 ነጥቦችን በመያዝ ምድብ አንድን በቀዳሚነት ይመሩታል። ብሩንድቢ በ 1 ነጥብ 3 ኛ ላይ ተቀምጠዋል።

ስፓርታ ፕራግ 1 – ሬንጀርስ 0

ግላስጎው ሬንጀርስ በዴቪድ ሃንኮ ግብ በፕራግ ውስጥ ተሸንፈዋል። ስፓርታ ሁሉንም 3 ነጥቦች በወሰደበት ጨዋታ የሬንጀርሱ ግሌን ካማራ በ 74 ኛው ደቂቃ  በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብታል። ውጤቱም ሬንጀርስ በምድብ አንድን በ 0 ነጥብ መጨረሻ ላይ ሲያስቀምጣቸው ፣ ስፓርታ በ 4 ነጥብ 2 ኛ ደረጃ እንድዪዙ አስችላቸዋል።

ምድብ ሁለት

ሪያል ሶሲዳድ 1 – ሞናኮ 1

games4you.me

የአክሰል ዲሲ ግብ በሚኬል ሜሪኖ በመሰረዙ ምክንያት ቡድኖቹ ነጥቦቹን በስፔን ተጋርተው ወጥተዋል። ሞናኮ በምድብ ሁለት በ 4 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ሲይዙ ሶሲዳድ በ 2 ነጥብ 3 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ኤስኬ ስትሩም ግሬዝ 1 – ፒኤስቪ ኢንድሆቨን 4

የኔዘርላንዱ ቡድን ኦስትሪያኖችን በግሬዝ ውስጥ አሸነፈ። ኤስኬ ከጆን ጎረንክ ስታንኮቪች የማስተዛዘኛ ግብ አግኝቷል ፣ ነገር ግን የ ኢብራሂም ሳንጋሬ ፣ ኤራን ዛሃቪ ፣ ፊሊፕ ማክስ እና ዮርቤ ቬርቴሰን ግቦች ፒኤስቪ እንዲያሸንፍ አድርገዋል። የደቡባዊ ኔዘርላንድስ ቡድን በ 4 ነጥብ ምድቡን ይመራል። ግራዝ በ 0 ነጥብ ታች ላይ ተቀምጠዋል።

ምድብ ሶስት

ሌጊያ ዋርሶ 1 – ሌስተር ሲቲ 0

የፖላንድ ዋና ከተማ የሆነው ቡድን ሌስተር ሲቲን ሲያሸንፍ በጨዋታው ውስጥ ብቸኛዋን ግብ ማሂር ኤምሬሊ አስቆጥሯል። ሊጊያ አሁን በ 6 ነጥብ በ ምድቡ አናት ላይ ሲሆን ሌስተር በ 1 ነጥብ ብቻ በመጨረሻ ላይ ተቀምጠዋል።

ናፖሊ 2 – ስፓርታክ ሞስኮ 3

በ ምድብ ሶስት የሩሲያው ቡድን የመጀመርያ 3 ነጥባቸውን በጣሊያን ውስጥ አግኝተዋል። የናፖሊው ተጫዋቾች ኤሊፍ ኤልማስ እና ቪክቶር ኦሲሜን የተሳካ ውጤት ቢያስመዘግቡም ስፓርታ ሞስኮው በ ኩዊኒ ፕሮሜስ ሁለት ግቦች እና በ ሚካሂል ኢግናቶቭ አንድ ግብ ጨዋታውን አሸንፈዋል። ስፓርታክ አሁን በምድቡ በ 3 ነጥብ 2 ኛ ፣ ናፖሊ በ 1 ነጥብበ 3 ኛ ደረጃ ላይ የቀምጠዋል።

ምድብ አራት

ፌነርባቼ 0 – ኦሊምፒያኮስ 3

livik.net

የ ጊዮርጎስ ማሱራስ ሁለት ግቦች እና ፍራንሲስኮ ሶሬርስ ባስቆጠራት ግብ ግሪኮች በቱርክ ፌነርባቸን በቀላሉ እንዲያሸንፉ አስችሏቸዋል። አሁን ኦሊምፒያኮስ በ 6 ነጥብ የምድቡን የበላይ ሲሆን የቱርክ ቡድን በአንድ ነጥብ 3 ኛ ላይ ነው።

ሮያል አንትወርፕ 0 – ኢንትራክት ፍራንክፈርት 1

በ 91 ኛው ደቂቃ የአይንትራች ጎንኮሎ ፓሲያንሲያ ፍፁም ቅጣት ምት የጀርመኑ ቡድን በዓለም የአልማዝ ዋና ከተማ ውስጥ ድል እንዲያስመዘግቡ አስችላለች። ሮያል አንትወርፕ አሁን በ ምድብ አራት መጨረሻ ላይ ሲቀመጡ አይንትራክት ፍራንክፈርት በ 4 ነጥብ 2 ኛ ላይ ይገኛል።

ምድብ አምስት

ላዚዮ 2 – ሎኮሞቲቭ ሞስኮ 0

breakingnewslatest.com

ይህንን የአውሮፓ ዋና ከተሞች ውጊያ ለማሸነፍ ከቶማ ቤዚክ እና ፓትሪክ የመጀመሪያ አጋማሽ ግቦች ለላዚዮ በቂ ነበሩ። ላዚዮ አሁን በምድቡ በ 4 ነጥብ 2 ኛ ሲሆን ሎኮሞቲቭ በ 1 ነጥብ ግርጌ ላይ ነው።

ማርሴ 0 – ጋላታሳራይ 0

በፈረንሳይ በ አሰልቺ ሁኔታ 0-0 በተጠናቀቀው ጨዋታ ፣ የደጋፊዎች አመፅ ጨዋታዉን አቋርጦት ነበር። ጋላታሳራይ በ 4 ነጥብ ከምድቡ አንደኛ ሆኖ ይቆያል ፣ ማርሴ በ 2 ነጥብ 3 ኛ ላይ ነው።

ምድብ ስድስት

ሉዶጎሬትስ ራዝግራድ 0 – ሬድ ስታር ቤልግሬድ 1

ሬድ ስታር ከዚህ ሁሉ የባልካን ገጠመኝ 3 ነጥቦችን ሲወስድ ሲሲንሆ ከ ሉዶጎሬትስ በቀይ ካርድ ከሜድ ወጥታል። ጉሬለር ካንጋ ለ ሰርቢያው ቡድን ግብ አስቆጥራል። ሬድ ስታር ቡድኑን በ 6 ነጥብ ይመራል እና ሉዶጎሬትስ 1 ነጥብ ብቻ በመያዝ 3 ኛ ላይ ናቸው።

ስፖርቲንግ ብራጋ 3 – ሚድትጅላንድ 1

በ 2 ኛው አጋማሽ ብራጋ ሁለት ግብ ከ ጋሌኖ እና አንድ ግብ ከ ሪካርዶ ሆርታ አግኝተው ፣ ከእረፍት በፊት ከ ኢቫንደር አንድ ግብ ላገኘው ሚድትጅላንድን ለማሸነፍ በቂ ነበር። ብራጋ አሁን በ 3 ነጥብ በቡድኑ 2 ኛ ሲሆን ፣ ኤፍ..ሲ ሚድትጅላንድ በ 1 ነጥብ መጨረሻ ላይ ይገኛል።

ምድብ ሰባት

ሴልቲክ 0 – ባየር ሊቨርኩሰን 4

bundesliga.com

ሊቨርኩሰን በሉካስ አላርዮ ፍፁም ቅጣት ምት እና በፒሮ ሂንካፒ ፣ ፍሎሪያን ዊርትዝ እና አሚን አድሊ ግቦች ፣ ግላስጎው ውስጥ ሴልቲክን አሸንፈዋል። የጀርመን ቡድን አሁን ምድቡን በ 6 ነጥብ ሲመራ ሴልቲክ ደግሞ በ 0 ነጥብ መጨረሻ ላይ ናቸው።

ፌረንስቫሮሺ 1 – ሪያል ቤቲስ 3

በ ሃንጋሪ ውስጥ ቤቲስ ከሜዳቸው ውጪ ድል አስመዘገቡ። የነቢል ፈኪር እና የክሪስቲያን ቴሎ ግቦች እንዲሁም የሄንሪ ዊንጎ የግል ጎል ለስፔኑ ቡድን ከበቂ በላይ ነበሩ። ፌረንክቫሮሺን ሚርቶ ኡዙኒ ከእረፍት በፊት አቻ አድርጎ ነበር ፣ ነገር ግን ቤቲስ በ 2 ኛው አጋማሽ በጣም ተጠናክሮ ነበር። ፌረንክቫሮሺ በ 0 ነጥብ 3 ኛ ደረጃ ላይ ነው። ሪያል ቤቲስ በ 6 ነጥብ 2 ኛ ነው።

ምድብ ስምንት

ጌንክ 0 – ዲናሞ ዛግሬብ 3

አንድ ግብ በሉካ ኢቫኑሴክ እና በብሩኖ ፔትኮቪች ሁለት ቅጣት ምቶች የ ቤልጄሙ ቡድን በጄንክ ተሸንፈዋል። ዲናሞ እና ጀንክ ሁለቱም 3 ነጥብ ያላቸው ሲሆን በምድብ ስምንት በተከታታይ 2 ኛ እና 3 ኛ ናቸው።

ዌስትሃም ዩናይትድ 2 – ራፒድ ቪየና 0

የ ዴክላን ራይስ እና የ ሴይድ ቤንራህማ ግቦች በለንደን 3 ቱን ነጥቦች ለዌስትሃም አስገኝተዋል። ዌስትሃም አሁን ምድብ ስምንትን በ 6 ነጥብ ሲመራ ፣ ራፒድ ቪየና በ 0 ነጥብ ግርጌ ላይ ነው።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football