Connect with us
Express news


Football

በሊቨርፑል አራት ግብ የተቆጠረበት ጨዋታ!

Four Goal Thriller in Liverpool!
skysports.com

በዚህ 2-2 አቻ ውጤት መሀመድ ሳላህ ድንቅ ጎል ካስቆጠረ በኋላ ኬቪን ዲ ብሩይን ለማንችስተር ሲቲ የመጨረሻውን የእኩልነት ግብ አስቆጥሯል።

በዚህ በአንፊልድ በተደረገ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ (ኢፒኤል) ጨዋታ ሊቨርፑል ድል ያደረገ ይመስል የነበረ ቢሆንም ኬቨን ዴ ብሩይን ዘግይቶ ያስቆጠራት ጎል ለማንቸስተር ሲቲ የሚገባውን ነጥብ አስገኝታለች።

የኢ.ፒ.ኤል. ሻምፒዮን ሲቲ እና የየርገን ክሎፕ ሊቨርፑል በኤ.ፒ.ኤል. ሰንጠረዥ ላይ የአንደኛነቱን ቦታ ከቼልሲ ለመረከብ ተስፋ አድርገው ነበር ፣ ግን በውጤቱ መሰረት የቶማስ ቱቸል ቡድን የበላይ ሆኖ ይቆያል ማለት ነው።

ሲቲ በመጀመሪያው አጋማሽ ምርጥ ቡድን ነበር ነገር ግን ብዙ የግብ እድሎችን አምክነዋል። የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድንም ሳዲዮ ማኔ የሳላህን ምርጥ ኳስ አስቆጥሮ ተቀጡ። ሳላህ የሜሲን የሚመስል ሩጫ አድርጎ ካቀበለው በኋላ በቀላሉ በማስቆጠር ከ 59 ደቂቃዎች በኋላ ሊቨርፑልን ቀዳሚ አድርጓል።

የሊቨርፑል 1-0 መሪነት ለ 10 ደቂቃዎች ብቻ የቆየ ሲሆን ፣ ሙሉ ምሽቱን ሲቸገር የነበረውን ጀምስ ሚልነርን ያሰቃየው ፊል ፎደን ከጋብርኤል ጄሱስ ኳስ ተቀብሎ አሊሶንን አሳልፎ በኮፕ ኤንድ በኩል አስቆጥሯል።

marca.com

ሚልነር በርናርዶ ሲልቫ ላይ ክፉኛ ጥፋት ሰርቶ ከሁለተኛው ቢጫ ካርድ በማምለጡ የሲቲ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተቃውሞውን ሲገልፅ ነበር።

ከዚያ ሰዓቱ 76 ደቂቃ ሲል ሳላህ በርካታ የሲቲ ተከላካዮችን አልፎ ከጠባብ አንግል አስደናቂ ግብ ሲያስቆጥር አንፊልድ በደስታ ተናወጠ።

skysports.com

የሲቲ እንቅስቃሴ ቢያንስ አንድ ነጥብ የሚገባው ነበር እናም ዴብረይን ጨዋታው ዘጠኝ ደቂቃ ብቻ ሲቀረው የመታው ኳስ በጆኤል ማቲፕ ተጨርፎ አሊሶንን አልፎ በመግባት ያንን ነጥብ አስገኝቶላቸዋል።

ቀዮቹ በ 85 ኛው ደቂቃ ማሸነፍ ነበረባቸው ፣ ነገር ግን ፋቢንሆ ወደ ባዶ ግብ የመታው ኳስ በሮድሪ ድንቅ ብሎክ ሊድን ችሏል።

በውጤቱ መሰረት ሁለቱም ክለቦች በኢ.ፒ.ኤል. ሰንጠረዡ ዝቅ ይላሉ። ሊቨርፑል በ 15 ነጥብ ሁለተኛ ነው። ማንቸስተር ሲቲ በ 14 ነጥብ 3 ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football