Connect with us
Express news


Bundesliga

የወደቁ ግዙፎች! ሪያል ማድሪድ ፣ ፒኤስጂ እና ባየርን በትናንሽ ቡድኖች ተሸነፉ!

Fallen Giants! Real Madrid and PSG Lose To Outsiders!
https://isport.blesk.cz/

በእለተ እሁድ ፤ የሊግ 1 መሪዎች ፣ ፒኤስጂ ፣ የላሊጋው መሪዎች ፣ ሪያል ማድሪድ እና ሌላው ቀርቶ የቡድንስሊጋው መሪዎች ባየርን በየሊጎቻቸው የውድድር ዘመኑ የመጀመሪያ ሽንፈታቸውን ቀምሰዋል።

ፒኤስጂ በሊግ 1 ውስጥ የኢያስደንቅ ሪከርድ ነበረው። እሁድ ከ ሬኒስ ጋር ከመፋለማቸው በፊት 8 ግጥሚያዎችን አድርገው ሁሉንም ጨዋታዎች አሸንፈዋል። ምንም እንኳን ፒኤስጂ በምርጥ 11 ውስጥ ምርጡ የማጥቃት ሶስትዮሽ ይዘው ቢገቡም ፣ ምንም ጎል ሳያስቆጥሩ ቡድናቸው በመካከለኛው የደረጃ ሰንጠረዥ የሚገኘው ሬኔስ ሲሸነፍ ማየቱ ለደጋፊዎቻቸው የበለጠ አስደንጋጭ ነበር። ምባፔ ፣ ሜሲ እና ኔይማር ሁሉም እየተጫወቱ ነበር!

ግብ ማስቆጠር አለመቻላቸው ብቻ ሳይሆን ፣ ኢላማዉን የጠበቀ አንድ ሙከራ እንኳን ማድረግ አልቻሉም! ሜሲ አንድ ጊዜ የፍፁም ቅጣት ምት የግቡ መአዝን መልሶለት ነበር ፣ እናም ምባፔ ከጨዋታ ውጪ የሆነ ግብ አስቆጥሯል። ይህ ብቻ ነበር ማድረግ የቻሉት። ፒኤስጂ በጨዋታው አብዛኛው ጊዜ ኳሱን ይዘውት ሊሆን ይችላል ፣ ነገር ግን ምን ማድረግ እንዳለባቸው የማያውቁ ይመስሉ ነበር።

https://psgtalk.com/

የሬኔስ አጥቂ እና የአሁኑ የሊግ 1 ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ጋታን ላበርዴ አንድ ግብ በማስቆጠር እና ለግብ የኢሆን ኳስ በማመቻቸት ፒኤስጂ እንዲሸነፍ ትልቅ ሚና የተጫወተው። ጨዋታው 2-0 ተጠናቀቀ ፣ እና ፒኤስጂ አሁን ዓለም አቀፉ ዕረፍት ካለቀ በኋላ በአንገርስ ላይ ወደ አሸናፊነት የሚመለስበትን መንገድ ይፈልጋል።

የሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች ቡድናቸው በላሊጋው በ 13 ኛ ደረጃ ላይ በሚገኘው ኤስፓኒዮል ሲሸነፍ ማየት አስደንጋጭ ነበር ። ማክሰኞ በሸሪፍ ቲራፖል የተሸነፈው የ ሎስ ብላንኮዎች ቡድን ይህ ሁለተኛው አሳፋሪ ውጤት ነበር።

ሪያል ማድሪድ በርካታ የግብ ዕድሎችን ፈጥረዋል ፣ ነገር ግን የእስፓኒዮሉ አጥቂ ራውል ዲ ቶማስ በ 17 ኛው ደቂቃ ከሚያምር ዝቅተኛ ኳስ ግብ ካስቆጠረ በኋላ የማጥቃት ሙከራውን እንዲቆም አድርጓል።

https://www.marca.com/

ሎስ ብላንኮዎች ግብ ማስቆጠር አልቻሉም እናም የእስፓኒዮሉ የክንፍ ተጫዋች አሌክስ ቪዳል በ 60 ኛው ደቂቃ ውስጥ የሪያል ተከላካዮችን ጥሩ እንቅስቃሴ ካለፈ በኋላ ሌላ ግብ ጨመረ። ኤስፓኒዮል ከ 3 ደቂቃዎች በኋላ እንደገና ለግብ የቀረበ ሙከራ ማድረግ ችለዋል ነገር ግን ሰርጊ ዳርደር ከሪያል ግብ ጠባቂ ቲባው ኩርቱዋ ጋር ፊት ለፊት ከተገናኘ በኋላ መረቡን ማግኘት አልቻለም።

ከዚያም በ 68 ኛው ደቂቃ ቤንዜማ ቡድኑን በጀርባው ተሸክሞ አቻ ለማድረግ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ፣ ከጨዋታ ውጪ በመሆኑ ግቡ ተሽሯል። በፍጥነት ሁኔታውን በማስተካከል በ 70 ኛው ደቂቃ ግብ አስቆጥሯል። ይህ በሚያሳዝን ሁኔታ ሪያል ያስቆጠረው ብቸኛው ግብ ነበር። ውጤቱም በኢስፓኒዮል መሪነት 2-1 አለቀ።

ሪያል ማድሪድ አሁንም በግብ ልዩነት በልጦ በላሊጋው በ 17 ነጥብ አንደኛ ደረጃ ላይ ነው ፣ ነገር ግን አትሌቲኮ ማድሪድ እና ሪያል ሶሲዳድ እንዲሁ 17 ነጥብ አላቸው።

መርሳት የሌለብን ፣ የቡንደስሊጋ ሻምፒዮናዎች እና የአሁኑ የቡንደስሊጋ መሪዎች ባየር ሙኒክም በዚህ የውድድር ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ በትንሹ ቡድን ፍራንክፈርት 1-2 የተሸነፉት ትናንትና ነበር። ለሁሉም አነስተኛ ግምት የተሰጣቸው ቡድኖች አስደሳች ቀን ነበር!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Bundesliga