Connect with us
Express news


Football

አስደናቂ ቅጣት ምቶች! – ክፍል 1

Fantastic Free Kicks! – Part I
skysports.com

በ ቅጣት ምት ከተገኙ ግቦች በላይ የእግር ኳስ ጨዋታ የሚያሳምር ምንም ነገር የለም! የምንጊዜም በጣም አስደናቂ የሆኑትን ቅጣት ምቶች እንመልከት!

ዲሚትሪ ፓየት – ዌስትሃም ከ ክሪስታል ፓላስ (2016)

ዲሚትሪ ፓየት ከፈረንሣይ ወደ እንግሊዝ ከተጓዘ በኃላ በፕሪሚየር ሊጉ በሁለት ዓመታት ውስጥ የሚያስደንቅ አቋም አሳይቷል ፣ ከዚያ እንደገና ሊጉን ለቆ ወጥቷል። ፈረንሳዊው ተጫዋች በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ ለአጭር ጊዜ የቆየ ቢሆንም በጣም አስደሳች ነበር።

በክሪስታል ፓላስ ላይ ያስቆጠራት ቅጣት ምት በጣም አስደናቂ ግቡ ነበረች። አጥቂው ረጃጅም ተጫዋቾች በተሞላበት ግድግዳ ዙሪያ ኳሱን አጠማዞ በመምታት ባልተጠበቀ ሁኔታ ወደ ላይኛው የግቡ ጥግ አስቆጥራል። በእውነቱ ፣ በጥሩ ሁኔታ የተመታ ከመሆኑ አንፃር የፓላስ ግብ ጠባቂ በግቡ አካባቢ ከመቆም ውጪ ኳሱን ሊያድነው አልቻለም!

ዴቪድ ቤካም – እንግሊዝ ከ ግሪክ (2001)

eurosport.com

ይህ የእግር ካስ ህይወቱ በሚያስደንቅ የቅጣት ምት ስታቲስቲክሶች የተሞላ ተጫዋች ይቺ ቅጣት ምቱ በጣም አስደናቂዋ ቅጣት ምት ልትሆን ትችላለች። የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች በሚያስደንቅ ተሰጥኦው በቀኝ እግሩ በ 2001 እንግሊዝን ታድጋል።

በኦልድትራፎርድ በባከነ ሰአት ውስጥ ግሪኮች 1-2 እየመሩ በነበሩበት ጨዋታ ፣ ቴዲ ሸሪንግሃም ጥፋት ሰርቷል ፣ ጥፋት የተሰራበት ቦታም በቀጥታ ግብ ለማስቆጠር በጣም ሩቅ ነበር። ነገር ግን ይህ ለ ዴቪድ ቤካም በጣም ሩቅ አልነበረም። የመቆሚያ እግሩ ቁርጭምጭሚቱ አካባቢ በማጠፍ እና ኳስ የሚመታበትን እግሩ በኳሱ ዙርያ በማዞር በሚያስደንቅ ሁኔታ ኳሱን አጠማዞ በቀኝ  በኩል ወደ ላይኛው የግቡ ጥግ በማስቆጠር ፣ እንግሊዝ ወደ የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ እንድታልፍ አድርጋል!

ሚይክል ኒልሰን – አይኤፍኬ ጎተርበርግ ከ ፒኤስቪ ኢንድሆቨን (1993)

እ.ኤ.አ. በ 1992/93 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ ፣ የስዊድን ተጫዋች ሚካኤል ኒልሰን እስካሁን ከተመዘገቡት ምርጥ ቅጣት ምቶች አንዱ ሆኖ የሚታወስ በማስቆጠር ታሪክ ሰርቷል!

መጀመሪያ ፣ ግብ ጠባቂው ስህተት የሰራ ይመስል ነበር ምክንያቱም ካሱ ከርቀት የመጣ ነበር ፣ ነገር ግን በእውነቱ የፒኤስቪው ግብ ጠባቂ ሃንስ ቫን ብሬክሌን ምንም ማድረግ ያልቻለው ቅጣት ምቱ በሃይል የተመታ እና የተጠመዘዘ እንከን የለሽ ምት ስለነበር ነው!

የምንጊዜም ምርጥ ቅጣት ምቶች ፅሁፋችን ስለሚቀጥል ፣ ክፍል 2 ን መመልከትዎን አይርሱ!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football