Connect with us
Express news


Football

በደቡብ አሜሪካ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ግጥሚያዎች ተጀምረዋል!

World Cup Qualifiers in South America Are On!
https://www.espn.com/

ሁለቱም የደቡብ አሜሪካ ግዙፍ ቡድኖች ነገ ምሽት ይጫወታሉ። ብራዚል በሜዳቸው ከ ቬኔዝዌላ ጋር ሲገናኙ ፣ አርጀንቲና ወደ ፓራጓይ ያቀናሉ። ነገር ግን ኮሎምቢያ ፣ ሁል ጊዜ ለማሸነፍ ከባዱ ቡድን ኡራጓይን የሚገጥምበት ጨዋታ አንርሳ።

አርጀንቲና በአሁኑ ሰአት በደቡብ አሜሪካ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ፣ በምድባቸው ውስጥ በ 18 ነጥብ 24 ነጥቦችን የሰበሰቡትን ብራዚልን በመከተል 2 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ምንም እንኳን በምድቡ ውስጥ ከሌሎቹ ቡድኖች አንድ ቀሪ ጨዋታ ቢኖራቸውም ሁለቱም ቡድኖች አናት ላይ ተቀምጠዋል (በብራዚል እና በአርጀንቲና መካከል ሊደረግ የነበረውን ጨዋታ በኮቪድ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ተላልፋፏል) ። ይህ ማለት በእውነቱ ምንም የሚያሳስባቸው ነገር የለም እና በሚቀጥለው የዓለም ዋንጫ ውድድር ውስጥ ቦታቸውን የተረጋገጠ ይመስላል።

መጨነቅ ያለበት ቡድን ፓራጓይ ነው። በ 6 ኛ ደረጃ ላይ ናቸው ፣ እና እዚያ የሚቆዩ ከሆነ ለውድድሩ ብቁ አይሆኑም። ነገር ግን አርጀንቲናን ማሸነፍ እና ሁሉንም አስፈላጊ 3 ነጥቦችን ማግኘት ቀላል አይሆንም። ትልቁ ተስፋቸው ፣ ቡድኑ ለሀገሩ እንዲሰለፍ ፈቃድ ማግኘት የቻለው የኒውካስትሉ አማካይ ሚጌል አልሚሮን ይሆናል ፣ እናም ተጫዋቹ ችሎታውን ለማሳየት ጓግታቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግጥሚያው ማን እንደሚያሸንፍ ግልፅ ነው። አርጀንቲና ከጥቂት ወራት በፊት የኮፓ አሜሪካን ዋንጫ አንስተዋል ፣ በምድብ ማጣሪያ ጨዋታም አንድም ሽንፈት አላስተናገዱም ፣ እናም ሜሲ ፣ ዲ ማሪያ እና ማርቲኔዝ በፊት መስመር የሚያሰልፉት አርጀንቲናዎች ግጥሚያዉን እንዲያሸንፉ እንጠብቃለን።

ወደ ብራዚል እንሂድ። ብራዚል የኮፓ አሜሪካን ዋንጫን በአርጀንቲና ተሸንፈው ሊሆን ይችላል ፣ ነገር ግን ከዚያ ውጭ በመሠረቱ ማንም ሊያቆማቸው አይችልም። ይህንን ሽንፈት ስንመለከት የ2018ቱ የዓለም ዋንጫ በሩብ ፍፃሜ በቤልጅየም የተሸነፉበት ጨዋታ ያስታውሰናል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አንዳንድ ጊዜ ብቻ አቻ በመለያየት አብዛኛዉን ጨዋታዎች አሸንፈዋል።

https://timesofindia.indiatimes.com/

በመካሄድ ላይ ባለው የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ብራዚል ከ 24ቱ ነጥቦች 24ቱን ሰብስበዋል! እናም በምድቡ የደረጃ ሰንጠረዥ በሌላኛው ጫፍ ላይ ማን ይቀመጣል? ቀጣይ ተጋጣሚያቸው ቬንዝዌላ። ቬንዝዌላ እስካሁን አንድ ድል እና አንድ አቻ ብቻ ማሳካት ችለዋል ፣ የቀሩትን ሁሉንም ግጥሚያቸው ተሸንፈዋል። ይህ ወቅታዊ አቋሟቸውን ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ነው። እኛ ኔይማር ፣ ጃሱስ እና ቪኒሺየስ ጁኒየር አስደናቂ አቋም አሳይተው ብራዚሎች በቀላሉ ያሸንፋሉ ብለን እናስባለን።

ለመጥቀስ የፈለግነው የመጨረሻ ጨዋታ በኡራጓይ እና በኮሎምቢያ መካከል የሚደረገው ፍልሚያ ነው። ኡራጓይ በምድቡ 3 ኛ ደረጃን በመያዛቸው ምክንያት በጥሩ ሁኔታ እየሄዱ ሲሆን ኮሎምቢያ ደግሞ በ 2 ነጥብ ብቻ ተበልጠው 5 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ለመጨረሻ ጊዜ እነዚህ ሁለት ቡድኖች የተገናኙት በሐምሌ ወር በኮፓ አሜሪካ ሩብ ፍፃሜ ነበር ፣ እናም ውጊያው ኮሎምቢያዎች በፍፁም ቅጣት ምት አሸንፈዋል። ነገር ግን ቡድኖቹ ተቀራራቢ አቋም ነው ያላቸው እናም በዚህ ጊዜ አቻ የሚለያዩ ይመስለናል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football