Connect with us
Express news


Football

ቅድመ -እይታ ፤ አርብ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ጀርመን ከ ሮማኒያ ጋር ይገናኛሉ!

Preview: Germany and Romania Clash on Friday in World Cup Qualifiers
goal.com

የሃንሲ ፍሊክ ጀርመን በመጨረሻው የ 2022 የአውሮፓ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ አርብ ምሽት ሮማኒያንን በ ሃምቡርግ ቮልስፓርክስታዲዮን ያስተናግዳሉ።

አስደሳች ግጥሚያ እንደሚሆን ተስፋ በተሰጠበት ጨዋታ ፣ ጀርመን እና ሮማኒያ ወደ አለም ዋንጫ ለማለፍ እየተፎካከሩ ነው! ጀርመን በምድብ አስር ላይ በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ፣ ተጋጣሚያቸው ቡድን ከባዱ አጀማመራቸውን ለመቀልበስ እየታገሉ ሲሆን አሁን ከአርሜኒያ እና ከሰሜን መቄዶኒያ ጋር ለሁለተኛ ደረጃ ይፎካከራሉ።

goal.com

አዲሱ አሰልጣኝ ሃንሲ ፍሊክ የጀርመን ብሔራዊ ቡድንን ከተቀላቀለ በኋላ በመጀመሪያዎቹ ሦስት ጨዋታዎች ሦስት ድሎችን አስመዝግበው ምንም ግብ ሳያስተናግዱ በጥሩ አቋም ላይ ናቸው። ሊችተንስታይንን 2-0 ፣ አርሜኒያ 6-0 ከዚያም አይስላንድን 4-0 በማሸነፍ በሳንት ውስጥ 12 ግቦችን አስቆጥረዋል።

ከሊችተንታይን ጋር ባደረጉት የመጀመርያ ጨዋታቸው 29 የግብ ሙከራ አስመዝግበው ነበር ነገር ግን ወደ ግብ መቀየር ተቸግረው ሊሆን ይችላል ፣ ነገር ግን በቀጣዮቹ ሁለት ጨዋታዎች ውስጥ ያሳዩት አቋም በጣም አስደናቂ ነበር እናም የአርቡን  ጨዋታ አሸንፈው በምድቡ አናት ላይ እንደሚቆዩ ያምናሉ።

ሮማኒያ ሁለተኛው ደረጃን ለመያዝ ከሌሎች ሁለት አገራት ጋር ለሚጠብቃቸው ፉክክር ጀርመንን ለማቆም የተቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ።

የሚሪል ራዶይ ቡድን በዓመቱ መጀመሪያ ላይ በአራት ተከታታይ ሽንፈቶች ደካማ ውጤት ካስመዘገበ በኋላ ልክ እንደ ጀርመን ባለፉት ሶስት ግጥሚያቸው ምንም ግብ አላስተናገዱም።

goal.com

አስቸጋሪ ጊዜ ካሳለፉ በኋላ በአዲሱ አሰልጣኝ ወደ ጥሩ አቋም የተመለሱ ይመስላል ፣ ትሪኮሎሪ ከ 1998 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ላይ ለመድረስ ይፈልጋሉ።

በጉዳት ዜና ፣ ሮቢን ጎሰንስ ከፊሊክስ ቡድን ውጪ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የፓሪስ ሴንት ጀርሜይን ቲሎ ኬኸር በግራ ተመላላሽ የሚተካው ይመስላል።

ኢልካይ ጉንዶጋን በመጎዳቱ የባየር ሙኒኩ ሊዮን ጎሬዝካ እና ጆሽዋ ኪሚች በአማካይ መስመር የመጀመር ዕድላቸው ሰፊ ይመስላል ፣ ነገር ግን የ 18 ዓመቱ ፍሎሪያን ዊርትዝ ከፊታቸው ሊሰለፍ ይችላል።

ግምት

ጀርመን 3 – 0 ሮማኒያ

ከሃቨርቴዝ እና ከቨርነር በሚገኘው የጀርመን የማጥቃት እንቅስቃሴ ዳይ ማንስቻፍት ብዙ ግብ ሲያስቆጥር ይመልከቱ። ሮማኒያ ለመገዳደር የሚሞክሩ ይሆናል ፣ ነገር ግን ያለመሸነፍ ጉዟቸውን ሲያበቃ ይመልከቱ።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football