Connect with us
Express news


Boxing

ታይሰን ፉሪ በምርጥ ፍልሚያ ዲዎንታይ ዊልደርን አሸነፈ!

Tyson Fury Knocks Out Deontay Wilder in Instant Classic!
MAAfighting.com

ብሮንዝ ቦምበር በጂፕሲ ኪንግ በ 11 ኛው ዙር ተሸነፈ!

ታይሰን ፉሪ በቅዳሜ እለት የ ደብሊው.ቢ.ሲ የከባድ ሚዛን ክብሩን ለመጠበቅ ፣ በ 11 ኛው ዙር ዴዎንታይ ዊልድን አሸንፏል።

ፍጥጫው እጅግ በጣም አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጥንካሬን የሚጠይቅ በጣም አስደሳች ውድድር ነበር ፣ እናም በዚህ ምክንያት ጠበብቶች ትግሉን ምርጥ ግጥሚያ ብለውታል።

DAZN.com

የጂፕሲው ኪንግ ዊልደርን በሦስተኛው ዙር ጥሎታል ፣ ከዚያም በአራተኛው ዙር ውስጥ ሁለት ጊዜ ከወደቀበት ከተነሳ በኋላ በ 10 ኛው እና በ 11 ኛው ዙር ላይ በዝረራ አሸንፎታል ፣ የእለቱ ዳኛ ራስል ሞራ ዊልደር አሁንም በእግሩ ለመቆም ቢሞክርም ጨዋታውን አጠናቅቆታል።

ፉሪ ጨዋታው ካለቀ በኋላ እንደተናገረው “ለምርጦቹ ሶስት አካላት ብቁ የሆነ ምርጥ ውጊያ ነበር” ብለዋል። “እኔ ምንም ሰበብ አልፈጥርም ፣ ዊልደር ምርጥ ተፋላሚ ነው ፣ በጣም ፈትኖኛል። እኔ ሁል ጊዜ የምለው የዓለማችን ምርጥ ተፋላሚ ነኝ ፣ እሱ ደግሞ ሁለተኛው ምርጥ ነው። እኔን አትጠራጠሩ። ሁልግዜም ከባድ ፈተናዎች መቋቋም እችላለው።”

ዊልደር (42-2-1 ፣ 41 ኬኦስ) ገላውን በማጥቃት እና በመክፈቻው ደወል መሃል ያለውን ቦታ ለመያዝ በመሞከር ፍልሚያውን ጀመረ ፣ ነገር ግን ሻምፒዮኑ የመጀመሪያው ዙር ከማለቁ በፊት ወደ ፊት መጫን ጀመረ እና በዙሩ መጨረሻ አካባቢ አሜሪካዊው ተፋላሚ ላይ ከባድ ቡጢ ሰንዝሯል።

ፉሪ (31-0-1 ፣ 22 ኬኦስ) በሁለተኛው ዙር ፍጥነቱን ጨመረ ፣ ፊት ለፊት እየመጣ በዊልደር ብዙ ቡጢዎችን በመሰንዘር ጉዳት አድርሷል። ሆኖም ዊልደር ተመልሶ እያገሳ መጣ ፣ እና ፉሪ ላይ አደገኛ ምት ሰንዝሯል ፣ ነገር ግን ሻምፒዮኑ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ አፀፋዉን መልሷል።

theguardian.com

በ 10 ኛው ዙር ውስጥ ፉሪ በቀኝ እጁ ፣ ወደ ዊልደር ኃይለኛ ቡጢ ወደ ጭንቅላቱ በመሰንዘር ተከታታይ ጉዳቶችን አድርሷል። ዊልደር እንደገና በሚያስደንቅ ሁኔታ ተምልሶ የፉሪን ጭንቅላት በማወዛወዝ ዙሩን አጠናቋል።

“ማን እንደሚያሸንፍ አይታወቅም ነበር” በማለት አምኗል ፤ እኔ ወደዚህ አስተሳሰብ ገባሁ ፣ ‹በሕይወትዎ ውስጥ የምትችለዉን ሁሉ ማድረግ ትችላለህ ፣ ነገር ግን በከዋክብት ውስጥ የተፃፈው ነገር ሁሉም ይሆናል›። በእሳት ብትጫወት ፣ ትቃጠላለህ። ሁለት ጊዜ ከባድ ጉዳት አድርሶብኛል ፣ ነገር ግን ፍልሚያው አልቋል ብዬ አላሰብኩም። ‘ምንም ማለት አደለም ፣ በአንድ ደቂቃ ውስጥ እመልስልሃለሁ’ ነበር ያልኩት። እናም አደረኩት” ብሏል።

“ይህ የቦክስ ውድድር ነው። ይህ ህይወት ነው። ወደ ፊት መቀጠል አለብህ። ከባድ ነገር ማሳካት ከፈለግክ ተስፋ መቁረጥ የለብህም።”

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Boxing