Connect with us
Express news


Football

የፕሪሚየር ሊጉ ድንቅ ግቦች! – ክፍል ሶስት

Premier League Wonder-Goals! – Part III
footballwhispoers.com

የምንጊዜም ምርጥ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ (ኢፒኤል) ግቦች ላይ የምናቀርበው ተከታታይ ፅሁፍ ፣ በእነዚህ 4 ምርጥ ግቦች እንጨርሳለን!

4. ሮቢን ቫንፐርሲ (አርሴናል ከ ቻርልተን አትሌቲክ ፣ 2005-06)

youtube.com

ይህ ያለ ጥርጥር በአርሴናል ማሊያ የሮቢን ቫን ፐርሲ ምርጥ ግቡ ነው። በቻርልተን የግብ ክልል ውስጥ የተሻማው ኳስ ምንም ጉዳት የማይፈጥር እና በጣም ከፍ ያለ ይመስል ነበር። ሆኖም የኔዘርላንዱ ተጫዋች ከየት መጣ ሳይባል ወደ ግብ ክልሉ ዘልቆ በመግባት ድጋሜ ማየት በማንችለው መልኩ ፣ አየር ላይ እያለ በመምታት አስደናቂ ግብ አስቆጥሯል!

3. ፓኦሎ ዲ ካንዮ (ዌስትሃም ከ ዊምብልዶን ፣ 1999-2000)

youtube.com

የፓኦሎ ዲ ካኒዮ የኢ.ፒ.ል. ድንቅ ግብ የተቆጠረበት አንግል ፣ ከሌሎች አስደናቂ የአየር ላይ ግቦች የተለየ ያደርገዋል። ፖል ስኮልስ እና ሮቢን ቫን ፐርሲ ኢላማውን የጠበቀ የአየር ኳስ ለማስቆጠር ሰፊ ክፍተት ነበራቸው ፣ ነገር ግን ዲ ካኒዮ ይህንን እድል አልነበረዉም። አብዛኛው ተጫዋች ይህንን ኳስ ለመቆጣጠር ይሞክር ነበር ፣ ነገር ኝ ጣሊያናዊው አጥቂ ዘሎ በመቀስ ምት ወደ ግቡ ጥግ በመምታት አስደናቂ ግብ አስቆጥሯል። በጣም የሚያስገርም ግብ!

2. ማቲው ለ ቲሲየር (ሳውዝሃምፕተን ከ ኒውካስል ዩናይትድ ፣ 1993-94)

youtube.com

ማቲው ‹ሊ ጋድ› ሌ ቲሲየር በዘመኑ ፍጹም ድንቅ ግቦችን አስቆጥሯል ፣ ነገር ግን ይህ የእሱ ምርጥ ግብ ሆኖ ተመዝግቧል። ግቡ ፖል ጋስኮይን በስኮትላንድ ላይ ያስቆጠረው ዝነኛ ግብ የሚያስታውስ ነው! ምንም እንኳን የመጀመሪያው ኳስ የተሻማለትን ከኋላው ቢሆንም ፣ ሊ ቲሲየር ኳሱን ከኋላ በእግሩ ጎትቶ ተቆጣጥሮታል። በሁለተኛ ንክኪው አንድ የኒውካስትል ተከላካይ ያልፋል እና በሶስተኛው ኳሱን በሌላኛው ተጫዋች ራስ ላይ በማሳለፍ ኳሱን ወደ ፊቱ ያእጣዋል። በስተመጨረሻ ፣ በቀኝ እግሩ ወደ ታችኛው ጥግ ኳሱን በመላክ የሚያስደንቅ ግብ አስቆጥሯል።

1. ዴኒስ ቤርክሃም (አርሴናል ከ ኒውካስል ፣ 2001-02)

ይህ ግብ የኛ የምጊዜም የ ኢፒኤል ምርጥ ግብ ብለን የመረጥነው ነው! ለአርሰናል በፊት መስመር የሚጫወተው ሌላኛው የኔዘርላንድ ተጫዋች ዴኒስ ቤርክሃም ኳሱን በኒውካስል ሳጥን ጠርዝ ላይ ይቀበላል። የእሱ የመጀመሪያ ንክኪ በማይታመን ሁኔታ ፈጣን ነበር እናም ተከላካዩን በማለፍ ኳሱን ወደ ቀኝ እግሩ ላይ በማምጣት ከግብ ጠባቂው ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቷል። ኔዘርላንዳዊው ምትሃተኛ ኳሱን በትክክለኛው መአዝን እና በ ኢፒኤል የታሪክ መጽሐፍት ውስጥ አስመዝግቧል!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football