Connect with us
Express news


Football

ለሃገራቸው ያልተጫወቱ ምርጥ የእግር ኳስ ተጫዋቾች – ክፍል ሁለት

The Best Footballers without an International Cap – Part II
thesportsman.com

በዚህ ተከታታይ ማጠቃለያ ክፍላችን ለሀገሮቻቸው በጭራሽ ያልጫወቱ ሁለት ተጨማሪ ድንቅ ተጫዋቾችን እንመለከታለን!

ፓኦሎ ዲ ካኒዮ

ፓኦሎ ዲ ካኒዮ የተጫዋችነት ዘመኑን በላዚዮ ጀመረ ከዚያም ለጁቬንቱስ ፣ ለናፖሊ እና ለኤሲ ሚላን ተጫውቷል። እነዚህ ሁሉ የሴሪአ ክለቦች የዲ ካኖን አቅም ተገንዝበዋል ፣ ግን ሁሉም የእሱን ቁጡ ባህሪም አይተዋል።

ጣሊያን ውስጥ ካሉ ብዙ ታላላቅ ክለቦች ጋር ካልተስማማ በኋላ ጥሩ ጊዜ ወዳሳለፈበት ወደ ሴልቲክ ተዛወረ። ሆኖም ከፍተኛ የደመወዝ ጭማሪ ከጠየቀ በኋላ ሴልቲክ እሱን ለመሸጥ ወሰነ ፣ እናም ጣሊያናዊው ወደ ሼፊልድ ዌንስዴይ ተዘዋወረ።

እሳታማው አጥቂ በመጀመሪያው የውድድር ዘመኑ የዌንስዴይ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነበር እና በፍጥነት በደጋፊዎች ተወዳጅ ሆነ። ሆኖም ከአርሰናል ጋር በተደረገው ጨዋታ ዲ ካኒዮ ቀይ ካርድ ከተሰጠው በኋላ ዳኛውን ገፍቶ የ 11 ጨዋታ እገዳ ተጥሎበታል።

በመጨረሻም እንደገና ለመጫወት ፍቃድ ሲሰጠው የዌስትሃም አሰልጣኝ ሃሪ ሬድናፕ ለሀመሮቹ አስፈረሙት። በምስራቅ ለንደን ውስጥ ያሳለፋቸው አምስት የውድድር ዘመናት ምናልባት በዲ ካኒዮ የተጫዋነት ዘመን ውስጥ ምርጦቹ ነበሩ።

አጥቂው የማይታመን ክህሎት ፣ ጽናት እና ብልህነት ቢኖረውም ፣ እሱ በጣም ከባድ ባህሪ ነበረው እና ምናልባትም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመጫወት ዕድል ያላገኘበት ብቸኛው ምክንያት ይህ ሊሆን ይችላል።

ስቲቭ ብሩስ

premierleague25years.wordpress.com

ስቲቭ ብሩስ በብዙ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ (ኢ.ፒ.ኤል) ክለቦች አሰልጣኝነት የሚታወቅ ቢሆንም አስደናቂ የተጫዋችነት ጊዜም ነበረው። ስኮትላንዳዊው አስልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በ ኢፒኤል መጀመሪያ አካባቢ ላይ የማንችስተር ዩናይትድን የበላይነትን ሲመሰርት ከቁልፍ ተከላካዮቹ አንዱ ነበር።

ብሩስ በተጫዋችነቱ መጀመሪያ ላይ ተግሣጽ በማጣት ብዙ ጊዜ ይተች ነበር ፣ ነገር ግን እያደገ ሲሄድ ወደ ተሟላ ተከላካይነት አድጓል። የፈርጉሰን የአሰልጣኝነት ዘዴ ከተገደበው የተፈጥሮ ችሎታው የላቀ ጥቅም እንዲያገኝ እና ወደ ታዋቂነት እንዲገባ እንደረዳው ምንም ጥርጥር የለውም።

ሆኖም ፣ ይህ እንኳን ወደ እንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን እንዲገባ አልረዳውም ፣ አንዳንድ የእንግሊዝ አሰልጣኞች በዚያ ጊዜ የነበረውን የማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ሪከርድን ሲመለከቱ እሱን ባለመጠቀማቸው ሊቆጩበት ይችላሉ!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football