Connect with us
Express news


Football

አስቂኝ የግብ ጠባቂ ስህተቶች! – ክፍል አንድ

Hilarious Goalkeeping Howlers! – Part I
dreamteamfc.com

ግብ ጠባቂነት ምስጋና የማይገኝለት ስራ ነው። ለግብ የቀረበ ሙከራ ካዳኑ አድናቆትን ያተርፋሉ። ነገር ግን አንድ ጊዜ ስህተት ከሠሩ ፣ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ይሳለቅባቸዋል!

ፒተር ሺልተን – እንግሊዝ (1990)

youtube.com

ፒተር ሺልተን እስካሁን ካሉት ታላላቅ ግብ ጠባቂዎች አንዱ ነበር። ሆኖም ፣ ይህ ከእሱ ምርጥ ጊዜያት መካከል አንዱ አልነበረም እና በሚያሳዝን ሁኔታ በመጨረሻው ዓለም አቀፋዊ ጨዋታው ላይ ነበር። ሺልተን ከእንግሊዝ ተከላካይ የኋላ ኳስ ይቀበላል ነገር ግን ሮቤርቶ ባጊዮ አጠገቡ ላይ መሆኑን አልተነዘብም። ጣሊያናዊው አጥቂ ከዚያ ኳስን ከሺልተን ነጥቆ ወደ ሳልቫቶሬ ሺላቺ አቀብሎታል። ከዚያ ባጊዮ የህይወት ዘመኑን በጣም ቀላል ግግ አስቆጠረ!

ማሲሞ ታቢ – ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ሳውዝሃምፕተን (ፕሪሚየር ሊግ 1999-2000)

youtube.com

ጣሊያናዊው ግብ ጠባቂ ማሲሞ ታቢ ማንችስተር ዩናይትድን ከሴሪአው ቡድን ቬኔዚያ በ 4.5 ሚሊዮን ፓውንድ ፈርሟል። ከመጣ ብዙም ሳይቆይ ይህንን አደረገ! የሳውዝአምፕተኑ ማቲው ሊ ቲሲየር ከግብ ክልል ውጪ ግምታዊ ኳስ ይመታል ፣ ይህም ማንኛውም ግብ ጠባቂ በቀላሉ ማዳን ይችላል። ሆኖም ግን ታቢ የተመታለትን ኳስ በእግሩ መካከል ወደ ዩናይትድ ግብ እንዲገባ አደረገ። በሚቀጥለው ጨዋታ ጣሊያናዊው ከቼልሲ ጋር ባደረገው ጨዋታ ሌላ ስህተት መስራቱን ይቀጥላል። ከዛ በኋላ እንደገና ለማንችስተር ዩናይትድ አልተሰለፈም!

ፒተር ኤንክልማን – በርሚንግሃም ከ አስቶን ቪላ (ፕሪሚየር ሊግ 2002-03)

youtube.com

ይህ በበርሚንግሃም ግብ ጠባቂ ፒተር ኤንክኬልማን የተሰራ የፕሪሚየር ሊጉ ትልቅ ስህተት ነው። ኤንክልማን ማን ኳሱን አረጋግቶ በእግሩ ይዞ ለቪላ ተጫዋቾች እንዲሰጥ የተወረወረለትን የእጅ ኳስ ፣ ምንም ጫና ሳይደርስበት ኳሱን ጠልዞ ለማውጣት በሚሞክርበት ሰዐት ፣ ኳሱ በእግሩ ስር አልፎ ከመረብ ጋር ተገናኝቷል። ይህም በሜዳው የነበሩ ደጋፊዎችን እንዲስቁ ያደረገ ስህተተ ነበር።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football