Connect with us
Express news


Football

ማንችስተር ዩናይትድ ሶስት ነጥቦችን ለማግኘት ከሌስተር ሲቲ ጋር ይፋለማል!

Manchester United Seek Three Points at Leicester city!
manunitedcore.com

ማንችስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል እና ከቸልሲ ጋር ለመራመድ ሶስት ነጥብ ይፈልጋል። ቅዳሜ በኪንግ ፓወር ስታዲየም ምን ይፈጠራል?

ማንችስተር ዩናይትድ በ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ (ኢፒኤል) ፣ የ ብሪንዳ ሮጀርስ ቡድን ሌስተር ሲቲን ለመጋፈጥ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ወደ ኪንግ ፓወር ስታዲየም ሲያመሩ ፣ ወደ አሸናፊነት መንገድ ለመመለስ ይፈልጋሉ። ቀያዮቹ ሰይጣኖች በወቅቱ የውድድር ዘመን ካደረጓቸው ሰባት ጨዋታዎች 14 ነጥቦችን በመያዝ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ሌስተሮች በዚህ የውድድር ዘመን ከሰባት ጨዋታዎች 8 ነጥቦችን ብቻ በመሰብሰብ በ 13 ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በቡድን ዜና ፤ ሌስተር የጄምስ ኦስቲን ፣ የዌስሊ ፎፋና እና የዊልፍሬድ ንዲዲ አገልግሎት በጉዳት ምክንያት አያገኙም ፣ ነገር ግን ጆኒ ኢቫንስ ከቀድሞው ቡድኑ ጋር በሚጫወትበት ሰአት በመሃል ተከላካይ መስመር ላይ ለምስራቅ ሚድላንድስን ቡድን ትልቅ መነቃቃት ሊፈጥር ይችላል።

fosseposse.sbnation.com

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጃሚ ቫርዲ እና ኬሌቺ ኢሄናቾ በፊት መስመር ሊሰለፉ ይችላሉ። ከዓለም አቀፉ ዕረፍት በፊት ሁለቱም ተጫዋቾች በክሪስታል ፓላስ ላይ ግብ ማስቆጠር ችለዋል።

ለቀይ ሰይጣኖች ማርከስ ራሽፎርድ ከትከሻ ቀዶ ጥገና በማገገም በመጨረሻ ወደ ቡድኑ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል ፣ የክንፍ አጥቂው አማድ ዲያሎ ከጭን ችግር ካገገመ በኋላ የመሳተፍ ዕድል አለው።

የ ኦሊ ጉናር ሶልሻየር ቡድን በጉዳት ምክንያት ያለ ተከላካይ ራፋኤል ቫራን ይገባል። ሃሪ ማጉየር እንዲሁ መሰለፍ የማይችል ሌላኛው ተጫዋች ነው ፣ ስለሆነም ቪክቶር ሊንዴሎፍ እና ኤሪክ ቤይሊ በዩናይትድ የተከላካይ መስመር ላይ ይሰለፋሉ።

ኤዲሰን ካቫኒ እና ፍሬድ እንዲሁ በአለም አቀፍ ግዴታዎች ምክንያት አይሰለፉም። ይህ ማለት ፖል ፖግባ ከስኮት ማክቶሜናይ ቀጥሎ ፣ ሜሰን ግሪንዉድ በስተቀኝ ፣ ጃዶን ሳንቾ በግራ ፣ እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ጀርባ ሊሰለፉ ይችላሉ።

ማንቸስተር ዩናይትድ በዚህ የውድድር ዘመን እስካሁን ጥሩ ጉዞ አሳይቷል። ቀያይ ሰይጣኖች 2-1 በሆነ ጠባብ ውጤት ያሸንፋሉ ብለን እናስባለን!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football