Connect with us
Express news


European Leagues

በእንግዳ ምክንያት ለሌላ ጊዜ የተላለፉ ግጥሚያዎች!

Strangely Postponed Games!
thesportsman.com

የእግር ኳስ ውድድሮች ለሌላ ጊዜ የተላለፉባቸው አስገራሚ ምክንያቶች ምንድናቸው? በጣም እንግዳ ከሆኑት አምስቱ እንይ!

ብላክበርን ሮቨርስ ከ ሚድልስቦሮ (1996) – የጉንፋን ወረርሽኝ

እ.ኤ.አ. በ 1996 ከገና በዓል በፊት የሚድልስቦሮ ተጫዋች ብራን ሮብሰን በጉንፋን ከተያዘ በኋላ ቡድኑ ከግጥሚያው አንድ ቀን በፊት ከብላክበርን ጋር የነበራቸውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ (ኢ.ፒ.ኤል.) ግጥሚያ ለመሰረዝ ወሰነ። ሚድልስቦሮ በበሽታ ፣ በጉዳት ወይም በእገዳ ምክንያት በአጠቃላይ 23 ተጫዋቾች አልተገኙም ብሏል።

በኋላ ፣ ለሚድልስቦሮ ከባድ መዘዞች ይዞላቸው መጣ። በተፈጠረው የ ኢፒኤል ጉዳት መሰረት ፣ ብላክበርን ነጥቦቹን መሰጠት አለብን ሲል ተከራከረ። በመጨረሻ ጨዋታው በኋላ ላይ እንዲደረግ ታዝዞ ፣ ሚድልስቦሮ የ 50 ሺህ ፓውንድ ተቀጥተው 3 ነጥብ ተቀንሶባቸዋል። ሁለቱ ቡድኖች በመጨረሻ ሲገናኙ ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል ፣ ነገር ግን በመጨረሻው ሚድልስቦሮ በመጨረሻው የውድድር ግጥሚያ መውረዱን ተከትሎ የሶስት ነጥብ ቅጣት ወሳኝ እንደነበር ያሳያል።

ኢስቶኒያ እና ስኮትላንድ (1996) – አንድ ቡድን በታሊን

balls.ie

እንዲሁም እ.ኤ.አ. በ 1996 ስኮትላንድ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢስቶኒያን በታሊን ለመግጠም እቅድ ተይዞ ነበር። በጨዋታው ዋዜማ ስኮትላንድ በካድሪሩ ስታዲየም ሥልጠና ያደረጉ ሲሆን የሜዳው መብራት በቂ እንዳልሆነ ወስነዋል። ስኮትላንዶች ለፊፋ ተቃውሟቸውን ገለፁ ፣ ፊፋም ተቋዉሞዉን በመቀበል ጨዋታው ከ 6:45 ወደ 3 ሰዓት እንዲተላለፍ አድርጓል።

ኢስቶኒያ የቴሌቪዥን ገቢ ሊያጣ ስለሚችል አልተደሰተም። ስለዚህ ጎን ለጎን የተቃውሞ ሰልፍ ይመጣል ተብሎ በሰፊው ተጠብቆ ነበር። ሆኖም ጨዋታው ከሦስት ሰከንዶች በኋላ ዳኛው እንዲቋረጥ አደረገ!

ፊፋ ስኮትላንዳውያንን የ 3-0 ድል ከመስጠት ይልቅ ጨዋታው ሞናኮ በሚገኘው ስታዲ ሉዊስ 2 እንዲደረግ ወሰነ። ስኮትላንዳዊው አማካይ ኢያን ፈርጉሰን ከሜዳው ሲወጣ በደጋፊዎቹ ላይ ሲሳደብ ፣ ግጥሚያው በአሰልቺ ጨዋታ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቀቀ።

ፍሮም ታውን ከ ቺፐንሃም ታውን (2015): ቺዝ ፌስቲቫል

የቴሌቪዥን ተመልካቾችን ለማስተናገድ የኤፍኤ ካፕ ግጥሚያ አንዳንድ ጊዜ ወደ አርብ ምሽት ሊዛወር ይችላል ፣ ነገር ግን ይህ በሁለቱ የእንግሊዝ ሊግ ባልሆኑ ቡድኖች መካከል የሚደረገው ግጢያ መርሐ ግብብ ለሚያወጡ ሰዎች ችግር ላይ የጣለ ነበር። ከፍሮም ቺዝ ሾው ጋር እንዳይጋጭ ጨዋታው ለሌላ ጊዜ ተላልፏል!

ቅዳሜና እሁድ ሲካሄድ የነበረው የፍሮም አግሪካልተራል እና ቺዝ ሾው በየጊዜው ከ 20 ሺህ በላይ ተመልካቾችን ይስባል። ስለዚህ የደቡብ ሊግ ፕሪሚየር ዲቪዥን ቡድን ኃላፊዎች ግጥሚያው ካልተዛወረ የተመልካች ቁጥር ይቀንሳል በሚል ስጋት እርምጃ ወስደዋል። ይህንን ጨዋታ ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ በተደረገው ውሳኔ በጣም ብዙ ሰዎች አልተደናገጡም ነበር ማለት ይቻላል!

ማንቸስተር ዩናይትድ ከበርንማውዝ (2016) – የውሸት ቦምብ

ማንችስተር ዩናይትድ እሁድ ግንቦት 15 2016 የውድድር ዘመኑ የመጨረሻውን የኤ.ፒ.ኤል ግጥሚያ እንዲያድረግ መርሃ ግብር ተይዞለት ነበር። ሆኖም 75,000 ደጋፊዎች በኦልትራፎርድ የተገኙ ቢሆንም በአንዱ መፀዳጃ ቤት ውስጥ “ምንነቱ ያልታወቀ እቃ” መገኘቱ የሚገልፅ ዜና በፍጥነት ወጣ ፣ ይህም በስታዴሙ ግራ መጋባትን እና ፍርሃትን ፈጥሯል።

ለመረዳት እንደሚቻለው ደጋፊዎቹ በፍጥነት ከስታዲየሙ መውጣት ነበረባቸው እና ገና ኳሱ ከመመታቱ በፊት ጨዋታው ተቋረጠ። ሆኖም ፣ የሽብርተኝነት ሥጋት የፈጠረው እቃ የጥበቃ ሰራተኞች በልምምድ ጊዜ ይጠቀሙበት የነበረ እቃ ብሽንትቤት ክፍል ውስጥ ጥለዉት የሄዱ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

ብራዚል ከ አርጀንቲና (2021) የኮቪድ -19 ፕሮቶኮሎች

sportsnet.ca

እነዚህ ሁለት የደቡብ አሜሪካ እግር ኳስ ተጫዋቾች ባለፈው መስከረም የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ላይ ሲገናኙ ፣ ጨዋታው ከተጀመረ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የኮቪድ -19 ፕሮቶኮሎች ተጥሷል በሚል ምክንያት ጨዋታው ተራዝሟል። የብራዚል የጤና ባለሥልጣናት ከዩናይትድ ኪንግደም የመጡ ተጫዋቾችን ራሳቸውን ባለማግለል የኳራንቲን ደንቦችን ተላልፈዋል ብለው ያመኑትን አራት ተጫዋቾችን ተሳትፎ ለማቆም በሚያስደንቅ ጣልቃ ገብነት ወደ ሜዳ ገብተዋል።

በ ኢፒኤል ቡድኖች የተሳተፉት ተጫዋቾች ፤ የአስቶኒያ ቪላ ኤሚሊያኖ ቡንዲያ እና ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ፣ እና ጆቫኒ ሎ ሴልሶ እና ክሪስቲያን ሮሜሮ የቶተንሃም ሆትስፐር ነበሩ። ሁሉም የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸው ከሀገር እንዲባረሩ ተደረገ። እስካሁን ይህ ጨዋታ የሚካሄድበት ቀን አልተገለጸም።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in European Leagues