Connect with us
Express news


Football

ኤቨርተኖች ከዌስትሃም ጋር በሜዳቸው ተሸንፈዋል!

Everton Lose at Home against West Ham!
standard.co.uk

ዴቪድ ሞይስ ወደ ጉዲሰን ፓርክ ተመልሶ የቀድሞ ቡድኑን አሸንፏል። የዌስትሃሙ ቶማስ ሱቼክ ፊቱ ደም ሆኖ ከሜዳ ወጥቷል!

ኤቨርተኖች በዌስትሃም 0-1 ከተሸነፉ በኋላ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ደረጃቸውን ይዘው መቆየት አልቻሉም። ዌስትሀም ባለፉት ጥቂት ጨዋታዎች ውስጥ ወጥ ያልሆነ አቋም እንደመያዛቸው እና እና ከሜዳቸው ውጪ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለዚህ ጨዋታ ተጠባቂ አልነበሩም። ነገር ግን የዌስትሃሙ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞየስ ከ 2002 እስከ 2013 ያሰለጠነውን የቀድሞ ቡድኑን ለማሸነፍ ተጨማሪ ተነሳሽነት ያገኘ ይመስላል።

ሁለቱም ቡድኖች በጥንቃቄ እየተከላከሉ ከተጋጣሚዎቻቸው ማንኛውንም ስህተት በመጠባበቅ ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ላይ አተኩረዋል። ዌስትሃም ከቶፊስ የበለጠ ኳሱን ተቆጣጥረው ነበር ነበር ፣ ነገር ግን ብዙ የማቀበል ስህተቶች በመሰራታቸው ምክንያት ምንም ዓይነት አደገኛ ዕድሎችን መፍጠር አልቻሉም።

ቶማስ ሱቼክ የጨዋታውን የመጀመሪያ ግብ በ 34 ኛው ደቂቃ ላይ ማስቆጠር ችሎ ነበር ግን እንደ አለመታደል ሆኖ ዳኞች ከጨዋታ ውጪ ብለው ሰርዘውታል። ከዚያ ፓብሎ ፎርናልስ ከ 6 ደቂቃዎች በኋላ ሌላ ጥሩ ዕድል አግኝቷል ነገር ግን እድሉን አምክኗል።

ኤቨርተኖች የተጎዱት ሪቻርሊሰን እና ዶሚኒክ ካልቨርት-ሌዊን ያስፈልጓቸው ነበር። አሌክስ ኢዎቢ በአጥቂ መስመሩ ላይ ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴ አላደረገም። ክፍት የግብ መረብ ፊት ለፊት ብቻውን ቆሞ በቀላሉ የማስቆጠር እድል ቢያገኝም ኳሱን ሙሉ በሙሉ ስቶታል። እንዲህ ዓይነቱ ተጫዋች 30 ሚሊዮን ፓውንድ እንዴት እንዳወጣ የሚገርም ነው። ዴማራይ ግሬይ ለኤቨርተን ጎልቶ የሚታይ ፣ ጠንካራ ሩጫዎችን በማድረግ ፣ ዕድሎችን በመፍጠር እና ጥሩ አቋርጦ በመግባት ሲጫወት ነበር ግን ዕድሉን ወደ ጎል ለመቀየር ከቡድን ጓደኞቹ ተጨማሪ እገዛን ይፈልግ ነበር።

goal.com

የጨዋታው ብቸኛ ግብ የመጣው በ 74 ኛው ደቂቃ ነበር። ዌስትሃሞች የማእዘን ምት አሸነፉ ፣ ጃሮድ ቦወን በቀጥታ ተከላካዩ አንጄሎ ኦግቦና አሻማው እሱም በቀላሉ አስቆጥሮ ቡድኑ እንዲያሸንፍ አደረገ። ሚካኤል አንቶኒዮ በጠንካራ የአጥቂ የእግርኳስ ዘይቤው በጨዋታው ሙሉ የኤቨርተንን ተከላካዮች ነቃ አርጎ አቆይቷል ፣ ቶማስ ሱቼክ እና ዴክላን ራይስ የመሃል ሜዳውን በሚገባ አደራጅተዋል። በአጠቃላይ ዌስትሃም ድሉ የሚገባው ነበር።

https://www.irozhlas.cz/

ቶማስ ሱቼክ በ 79 ኛው ደቂቃ ላይ ደም በደም ሆኖ ከሜዳ ወጥቷል ፣ ነገር ግን በሚቀጥለው ሳምንት ከቶተንሃም ጋር ለመጫወት ብቁ ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

መዶሻዎቹ በኤ.ፒ.ኤል. ሰንጠረዥ ላይ ኤቨርተንን አልፈው አሁን በ 14 ነጥብ 7 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ኤቨርተንም እንዲሁ በ 14 ነጥብ ከኋላቸው ይገኛሉ።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football