Connect with us
Express news


Football

ባርሴሎናዎች ፣ ዳናሞ ኬቮች በማሸነፍ የመጀመርያ የሻምፒዮንስ ሊግ ድላቸውን አስመዝግበዋል!

Barcelona finally have a Champions League breakthrough against Dynamo Kiev!
barcablaugranes.com

ብሉጉራናዎች 1-0 በማሸነፍ ፣ የመጀመሪያ የአውሮፓ ግብ እና ድል አግኝተዋል ፣ የመጀመርያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 10 ደቂቃ ሲቀረው ጄራርድ ፒከይ የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል።

ባርሴሎና ረቡዕ በቻምፒየንስ ሊግ ምድብ አምስት ዲናሞ ኬቭን 1 ለ 0 አሸንፏል ፣ ጄራርድ ፒኬይ የስፔኑ ቡድን ወደ ጥሎ ማለፍ የመድረስ ተስፋውን ለማስቀተል ወሳኝ ግብ አስቆጥሯል።

ጆርዲ አልባ በ36 ደቂቃ ያሻማዉን ኳስ ጀራርድ ፒከይ ወደ ግብ በመቀየር የባርሴሎና የመጀመርያ የቻምፒዮንስ ሊግ ግብ አስቆጥሯል። ይህም በሙኒክ እና በቤኔፊካ 3-0 ከተሸነፉ በኋላ ያስመዘገቡት የመጀመርያ ድላቸው ነው።

የዲናሞ ኬቭ ቡድን ትንሽ የማጥቃት ሙከራ ያደረገ ሲሆን አንድም ኢላማዉን የጠበቀ የግብ ሙከራ አላደረገም ፣ ባርሴሎና ግጥሚያዉን በአሳማኝ ሁኔታ ማሸነፉ ባለመቻሉ አሳሳቢ ሆኖ ሊታይ ይችላል።

marca.com

የባርሴሎናው አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን አንሱ ፋቲ ፣ ፊሊፕ ኩቲንሆ እና አጉዌሮን ተቀያሪ ወንበር ላይ ሲያስቀምጡ ፣ አብዛኛውን ጊዜ በግራ ተመላላሽ የሚጫወተው ሰርጊኖ ዴስት ፣ ከሉክ ዴ ጆንግ እና ሜምፊስ ዴፓይ ጋር በፊት መስመር አሰልፏል።

በዴስት እና ዴ ጆንግ ሁለት ለግብ የቀረቡ እድሎች ካባከኑ በኋላ ፣ አሰልጣኝ ኮማን ፋቲ እና ኩቲንሆ በ 31ኛው ደቂቃ እንዲያማሙቁ በመጠየቅ ብስጭቱን አሳይቷል።

ነገር ግን ተከላካዩ ፒኬ ፣ ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ተጫዋቾች ከመቀየሩ በፊት ፣ ከአልባ የተሻማለትን ኳስ በጥሩ አጨራረስ ውጥረቱ እንዲቀንስ አድርጓል።

marca.com

ይህ ማለት ደግሞ ባርሴሎና በሳምንቱ መጨረሻ ቫሌንሺያን 3 ለ 1 ያሸነፈበትን ግጥሚያ ጨምሮ ፣ ከሁለት ተከታታይ ድል በኋላ በኑ ካምፕ ሪያል ማድሪድን ያስተናግዳል ማለት ነው።

የባርሳው አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን ከጨዋታው በኋላ ደስታቸውን አልገለፁም እናም “ደግነቱ ተከላካይ መስመራችን ጥሩ ነበር። የበላይነቱን ተቆጣጥረን ነበርን ፣ ነገር ግን ጨዋታውን በጥሩ ውጤት ማጠናቀቅ አለብን። ከ60 ደቂቃ በኋላ ሶስት ወይም አራት ለባዶ መምራት ነበረብን” ብሏል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football