Connect with us
Express news


Football

ቼልሲዎች በጥሩ አቋም ማልሞዎችን አሸነፉ!

Chelsea Thrash Malmö with Dominant Performance
goal.com

ቼልሲዎች ፣ ማልሞዎችን 4-0 ባሸነፉበት ግጥሚያ አንድሬያስ ክሪስተንሰን ለቼልሲ የመጀመሪያ ግቡ ሲያስቆጥር ሮሜሉ ሉካኩ እና ቲሞ ወርነር በጉዳት ከሜዳ ወጥተዋል።

ለቼልሲ አስደሳች ምሽት ነበር። ሰማያዊዎቹ ወደ በላይነት መንገድ ሲመለሱ ማልሞዎችን በበላይነት አሸንፈዋል ፣ በግጥሚያዉም በጣም አስደናቂ አቋም አሳይተዋል።

ሮሜሉ ሉካኩ እና ቲሞ ቨርነር በቁርጭምጭሚት እና በጉልበት ጉዳት ከሜዳ ቢወጡም አሁንም ድሉ በቻምፒየንስ ሊግ ወደ ምርጥ 16 ለማለፍ ስለሚረዳቸው ውጤቱ ለሰማያዊዎቹ ግሩም ነበር።

skysports.com

አንድሪያስ ክሪሰተንሰን ፣ የጆርጊንሆ ሁለት አሪፍ ፍፁም ቅጣት ምቶች ከመቆጠራቸው በፊት ፣ ቲያጎ ሲልቫ ያሻማለትን ኳስ አስቆጥሯል። እናም ካይ ሃርቨትዝ በሁለተኛው አጋማሽ ያስቆጠረው ግብ ለቼልሲው አሰልጣኝ ቶማስ ቱቸል በራስ መተማመንን እና እርካታ ሰጥቶታል።

ሜሰን ማውንት ላለፉት አራት ጨዋታዎች በ ቱቼል ካልተሰለፈ በኋላ በትናንትናው ግጥሚያድንቅ አቋም አሳይቷል። የ 22 ዓመቱ ተጫዋች ከካንቴ ጋር በመጣመር በማልሞ ተከላካዮች ላይ ጫና ሲፈጥር ነበር።

marca.com

አሰልጣኝ ቶማስ ቱቸል ፣ ቼልሲ ከማልሞ ጋር ባደረጉት ግጥሚያ ላይ ባሳዩት አስደናቂ አቋም ደስተኛ ነው። በኳስ ብልጫ እና ቀልጣፋ የኳስ እንቅስቃሴቸው ግጥሚያዉን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥረው ነበር።

ሆኖም ድሉ በሉካኩ እና በቨርነር ጉዳት ደብዝዟል። ጆርጊንሆ የመጀመሪያ ፍፁም ቅጣት ምት ምት በኔልሰን ጥፋት ሲያገኝ ሉካኩ ተጎድቷል ፣ የማልሞው ተጫዋች ሙሉ በሙሉ ቁርጭምጭሚቱ ላይ ጉዳት ያደረሰ ይመስላል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football