Connect with us
Express news


Football

የዓለም ምርጡ ሊግ ታሪክ! – ክፍል 6

The History of the Best League in the World! – Part VI
manutd.com

በ 2007/08 እና በ 2008/09 የውድድር ዘመን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምን እንደተከሰተ ይዘን ቀርበናል! ማንችስተር ዩናይትድ የበላይነቱን ማስቀጠል ይችል ይሆን?

ማንቸስተር ዩናይትድ 9 ኛውን የኢ.ፒ.ኤል ዋንጫ በማንሳቱ ፣ በነሐሴ 2007 ወደ 16 ኛው የኢ.ፒ.ል. የውድድር ዘመን ሻፒዮንነታቸውን ለማስጠበቅ ተጫውተዋል። ግንቦት 11 2008 የውድድር ዘመኑ የመጨረሻ ቀን ማንችስተር ዩናይትድ ዊጋን አትሌቲክን 2 ለ 0 አሸንፏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ቼልሲ ከቦልተን ዋንደርስ ጋር 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል ፣ ይህም በሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧቸዋል። ስለዚህ የሰር አሌክስ ፉርጉሰን ተጫዋቾች አሥረኛውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ሲያነሱ በአጠቃላይ ደግሞ 17 ኛ ዋንጫቸው ነበር። ይህም በ 2008 በአጠቃላይ 18 ጊዜ ሻምፒዮን መሆን ከቻሉት ታልቅ ተፎካካሪዎቻቸው ሊቨርፑል በአንድ ብቻ ርቀው እንዲቀመጡ አስችሏቸዋል።

በሌላኛው የደረጃ ሰንጠረዡ ጫፍ ፣ በርሚንግሃም ሲቲ ብላክበርን ሮቨርስን 4-1 እንዲሁም ሬዲንግ ደርቢ ካውንቲን 4 ለ 0 ቢያሸንፍም ፉልሃም ፖርትስማውዝን 1 ለ 0 በማሸነፉ በርሚንግሃምም ሆነ ሬዲን ወደ ታችኛው ዲቪዝዮን ወርደዋል። ደርቢ ወደ ታችኛው ዲቪዝዮን የወረደ ሌላኛው ክለብ ነበር።

በ2007 -08 የውድድር ዘመን ፣ ከቻምፒዮንሺፑ በጥሎ ማለፍ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ያደጉት ደርቢ ካንትሪዎች 11 ነጥብ ብቻ ሰብስበዋል። ይህም የሊጉ የምንግዜም ዝቅተኛ ነጥብ ነው! የኢስት ሚድላንዶች 20 ግብ ብቻ ሲያስቆጥሩ ፣ 89 ግቦችን አስተናግደዋል። አንድ ግጥሚያ ብቻ አሸንፈዋል።

telegraph.co.uk

የ 2008/09 የኢ.ፒ.ኤል. የውድድር ዘመን ሻምፒዮን ማን እንደነር መገመት ምንም ሽልማት አያስገኝም። ልክ ናቹ ፣ ማንችስተር ዩናይትድ እንደገና ሻምፒዮን ነበር! በዚህ ጊዜ የሰሜን-ምዕራብ ክበብ በመጨረሻው የሳምንቱ ግጥሚያ ሻምፒዮን ሆነ። ሊቨርፑል በቅርብ ርቀት ይከተላቸው ነበር ፣ ነገር ግን እንደ አለመታደል ሆኖ የመርሲሳይዱ ክለብ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ በተከታታይ ግጥሚያዎች አቻ በመለያየቱ ፣ 90 ነጥብ የሰበሰበው ዩናይትድን የመድረስ እድላቸውን አጥተዋል።

manutd.com

የአቡዳቢ ዩናይትድ ግሩፕ መስከረም 2008 ማንችስተር ሲቲ ገዝቷል። ይህም ቡድኑ በዓለም ከሚገኙት ሀብታም የእግር ኳስ ክለቦች መካከል አንዱ እንዲሆን አስችሎታል! ከዚያ ሰማያዊው ግማሽ ማንችስተር ሮቢንሆ በ 2008 የክረምት የዝውውር መስኮት ከመዘጋቱ ጥቂት ሰከንዶች በፊት በእንግሊዝ ሪከርድ 32.5 ሚሊዮን ፓውንድ ማስፈረሙን አረጋገጠ!

በ 2009 የውድድር ዘመን የመውረድ አደጋ የደረሰባቸው ቡድኖች ኒውካስትል ዩናይትድ ፣ ሚድልስቦሮ እና ዌስት ብሮምዊች አልቢዮን ነበሩ።

ይቀጥላል…

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football