Connect with us
Express news


Football

የአውሮፓ ሊግ ማጠቃሊያ!

Europa League Round-up
scotsman.com

ትናንት ምሽት ከተደረጉ አስደናቂ የዩሮፓ ሊግ ግጥሚያዎች ሁሉንም ግቦች እና ክስተቶች እንመለከታለን!

ምድብ አንድ

ሬንጀርስ 2 – 0 ብሮንድቢ አይኤፍ

የሊዮኖን ባሌዶ የጭንቅላት ግብ እና የኬማር ሩፌ የቅርብ ርቀት ግብ ፣ ሬንጀርሶች በግላስጎው ውስጥ ሦስቱን ነጥቦች ንዲወስዱ አስችሏቸዋል። የስቴቨን ጄራርድ ቡድን በምድብ አንድ ውስጥ 3 ነጥቦችን በመያዝ 3 ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ብሮንድቢዎች በአንድ ነጥብ ብቻ መጨረሻ ላይ ተቀምጠዋል።

ስፓርታ ፕራግ 3 – 4 ሊዮን

የፕራግ ቡድን የመጀመሪያዎቹን ሁለት ግቦች በሉካዝ ሃራስሊን በኩል አስቆጥሯል። ሆኖም ሊዮኖች በሁለተኛው አጋማሽ ፤ ካርል ቶኮ ኤካምቢ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች እና ሆሴም አዋር እና ሉካስ ፓኬታ ባስቆጠሯቸው አንዳንድ ግቦች ፣ ከኋላ ተነስተው እንዲያሸንፉ አስችሏቸዋል። ላዲስላቭ ክሬጂ በጨዋታው መጨረሻ ለስፓታ የማስተዛዘኛ ግብ አስቆጥሯል። ውጤቱም ሊዮኖች በ 9 ነጥብ በምድቡ አናት ላይ አስቀምጧቸዋል። ስፓርታዎች በ 4 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ናቸው።

ምድብ ሁለት

ፒኤስቪ ኢንድሆቨን 1 – 2 ሞናኮ

nu.nl

የደች ቡድን ከኮዲ ጋክ አንድ ቢያገኝም ፣ ሞናኮዎች ሜሮን ቦዱ እና ሶፊያን ዲዮፕ ባስቆጠርዋቸው ግቦች ግጥሚያዉን ማሸነፍ ችለዋል። ሞናኮዎች ምድቡን በ 7 ነጥብ ይመራሉ። ፒኤስቪዎች በ 4 ሦስተኛ ደረጃ ላይ ናቸው።

ኤስኬ ስትሩም ግሬዝ 0 – 1 ሪያል ሶሲዳድ

ስፔኖቹ አሌክሳንደር ኢሳቅ በሁለተኛ አጋማሽ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ግጥሚያውን አሸንፈዋል። ስትሩዝ ግሬዞች ዜሮ ነጥብ በመያዝ መጨረሻ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ሪል ሶሲዳዶች በ 5 ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ምድብ ሶስት

ናፖሊ 3 – 0 ሌግያ ዋርሳው

ናፖሊዎች በሎሬንዞ ኢንሲግኔ ፣ በቪክቶር ኦሲሜን እና በማቲዮ ፖታኖ ግቦች በኔፕልስ ውስጥ ሌጊያ ዋርሶዎችን አሸንፈዋል። ሌጊያዎች ምንም እንኳን ሽንፈት ቢያስተናግዱም አሁንም በ 6 ነጥብ ምድቡን ይመሩታል። ናፖሊዎች በ 4 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ምድብ አራት

ፌነርባቼ 2 – 2 ሮያል አንትወርፕ

ፌነርባቼ እና ሮያል አንትወርፕ በኢስታንቡል አስደሳች ጨዋታ አሳይተው 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል። የአትወርፕ ታንዛኒያዊ አጥቂ ምብዋና ሳማታ እና ፒተር ጌርከንስ ያስቆተርዋቸው ግቦች ፣ በጨዋታ እና በፍፁም ቅጣት ምት ኤነር ቫሌንሺያ ያስቆተራቸውን ግብ ለመብለጥ በቂ ነበሩ። የቱርክ ቡድን አሁን በምድቡ በ 2 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ነው። አንትወርፕ በ 1 ነጥብ ብቻ የመጨረሻ ላይ ነው።

ኢንትራክት ፍራንክፈርት 3 – 1 ኦሊምፒያኮስ

ኢንትራክት ፍራንክፈርት በጀርመን በተደረገው ጨዋታ ኦሎምፒያኮስን አሸንፏል። ራፋኤል ሳንቶስ ቦሬ ፣ አልማሚ ቱሬ እና ዳኢቺ ካማዳ ለባለሜዳው ቡድን ግብ አስቆጥረዋል። የሱፍ ኤል-አረቢ በፍፁ ቅጣት ምት ለእንግዳው ቡድን አንድ ግብ ቢያስቆጥርም ጨዋታው 3-1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል። ኢንትራክት ፍራንክፈርት በ 7 ነጥብ ምድቡን በአንደኝነት ይመራል። ኦሊምፒያኮስ በ 6 ነትብ ሁለተኛ ነው።

ምድብ አምስት

ላዚዮ 0 – 0 ማርሴ

ላዚዮ እና ማርሴ በጣሊያን ዋና ከተማ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል። ላዚዮ በምድብ አራት በ 4 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ነው። ማርሴይ በ 3 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ነው።

ሎኮሞቲቭ ሞስኮ 0 – 1 ጋላታሳራይ

livik.net

ከቱርካዊው ተጫዋች ሞሐመድ ከሪም አክቲርኮል የተገኘው ብቸኛ ግብ ፣ ጋላታሳራይ በሞስኮ ሶስት ነጥብ እንዲያገኝ አስችሎታል። ጋላታሳራይ ምምድብ አምስትን በበላይነት ይመራል፣ ሎኮሞቲቭ ሞስኮ በ አንድ ነጥብ መጨረሻ ላይ ነው።

ምድብ ስድስት

ኤፍሲ ሚድትጅላንድ 1 – 1 ሬድ ስታር ቤልግሬድ

ትናንት በዴንማርክ በተደረገው ግጥሚያ ፣ ሬድ ስታር ሚርኮ ኢቫኒች ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ቢችልም በ 78 ደቂቃ ኒኮላስ ዳይር ባስቆጠራት ግብ አቻ መሆን ችለዋል። ሁለቱንም ግቦች ከእረፍት በኋላ ተገኝተዋል። ሬድ ስታር በ 7 ነጥብ አሁንም የምድቡ መሪ ሆኖ ይቆያል። ሚድትጅላንድ በ 2 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ነው።

ሉዶጎሬጽ ራዝግራድ 0 – 1 ስፖርቲንግ ብራጋ

በምሽቱ ግጥሚያ የብራጋ ተጫዋች ሪካርዶ ሆርታ በ 7ኛው ደቂቃ ብጨኛዉን ግብ አስቆጥሯል። የስፔኑ ክለብ አሁን በ 6 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ነው። ሉዶጎሬትስ በአንድ ነጥብ መጨረሻ ላይ ተቀጠዋል።

ምድብ ሰባት

ሪያል ቤቲስ 1 – 1 ባየር 04 ሌቨርኩሰን

በሴቪል በተደረገው ግጥሚያ ላይ የተቆጠሩ ሁለት ግቦች በጨዋታው የመጨረሻ ሩብ ላይ ተቆጥረዋል። ቦርጃ ኢግሌየስ በ 75 ደቂቃ ፍፁም ቅጣት ምት ቢያስቆጥርም ባየር ጨዋታው ከመገባደዱ ከስምንት ደቂቃ በፊት በሮበርት አንድሪሽ አማካይነት ምላሽ ሰጥቷል። ምንም እንኳን የጀርመን ቡድን የላቀ የግብ ልዩነት ቢኖረውም ሁለቱ ክለቦች አሁን በ 7 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ እመቀመጥ እየተፋለሙ ነው።

ምድብ ስምንት

ዌስትሃም ዩናይትድ 3 – 0 ኬአርሲ ጀንክ

thesun.co.uk

ዌስትሃም በክሬግ ዳውሰን ፣ በኢሳ ዲዮፕ እና በጃሮድ ቦወን ግቦች ጄንክን በቀላሉ አሸንፏል። ሀመሮች አሁን በ 9 ነጥብ እና በ 100% ሪከርድ ምድብ ስምንትን በበላይነት እየመሩ ነው። ጄንክ በ 0 ነጥብ መጨረሻ ላይ ተቀምጧል።

ራፒድ ቪየና 2 – 1 ዲናሞ ዛግሬብ

ራፒድ ፣ ማርኮ ግሩል እና ማክስሚሊያን ሆፍማን ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች ሶስቱን ነጥቦች ወስዷል። ዲናሞ ዛግሬብ በምስላቭ ኦርሺች በኩል አንድ ጊዜ ብቻ ኳስ ከመረብ ጋር ማገናኘት ችሏል። ከኦስትሪያ ዋና ከተማ የመጣው ቡድን በ 3 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ነው። ዲናሞ እንዲሁ 3 ነጥብ አለው ፣ ነገር ግን በግብ ልዩነት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Must See

More in Football