Connect with us
Express news


Football

ኤል ክላሲኮ – የስፔን ታላቁ ጨዋታ!

El Clasico: Spain’s Greatest Fixture!
footballtransfers.com

ባርሴሎና ሪያል ማድሪድን ነገ በካምፕ ኑ ይገጥማል። የኤል ክላሲኮ ታሪክ ምንድነው እና ይህንን ከሁሉም የላቀ የክለብ ጨዋታ ማን ያሸንፋል?

ኤል ክላሲኮ ትርጉም

ኤል ክላሲኮ ወይም ‘ዘ ክላሲክ’ በባርሴሎና እና በሪያል ማድሪድ መካከል ለሚደረግ ጨዋታ የተሰጠ ስም ነው። በመጀመሪያ በሁለቱ መካከል በሚደረጉ የስፔን ሻምፒዮና ጨዋታዎች ላይ ብቻ ነበር ጥቅም ላይ የሚውለው ፣ ግን በማንኛውም ውድድር ውስጥ ለሚደረጉ ጨዋታዎቻቸው ጥቅም ላይ ይውላል።

እስካሁን የተገኙ ውጤቶች

የመጀመሪያው ኤል ክላሲኮ በ 1902 በኮፓ ዴ ላ ኮሮናሲዮን የተደረገ ሲሆን ባርሴሎና 3-1 አሸንፏል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሪያል ብዙ ጨዋታዎችን ያሸንፋል ፣ ባርኮሎና 96 ሲያሸንፍ 52 አቻ እና ማድሪድ 97 ጊዜ አሸንፏል። የኤግዚቢሽን ጨዋታዎችን ጨምሮ በጠቅላላው 278 ኤል ክላሲኮዎች አሉ። ባርሴሎናዎች 115 ፣ ሪያል 101 አሸንፈዋል ፣ 62 ጊዜም አቻ ወጥተዋል።

የ ኤል ክላሲኮ ታሪክ

1920 ዎቹ – የመጀመሪያው የላሊጋ ኤል ክላሲኮ

በላሊጋ የመጀመሪያው ክላሲኮ የተካሄደው በየካቲት 1929 ሲሆን የመጀመሪያው የላሊጋ አመት በተጀመረ በሁለት ሳምንት ውስጥ ብቻ ነበር። የባርሴሎና ሌስ ኮርቶች ስታዲየም በዚያ ቀን በራስ መተማመን በተሞሉ የሜዳው ደጋፊዎች ተሞልቶ ነበር ፣ ነገር ግን ሪያል ማድሪድ በሁለቱም አጋማሾች አንድ አንድ ግብ በማስቆጠር 2-1 ድል ማግኘት ችለዋል። ባርሴሎና የመልሱን ጨዋታ 1 ለ 0 አሸንፏል እና የመጀመሪያውን የላሊጋ ዋንጫም አሸንፈዋል ፣ ግን የመጀመሪያው የኤል ክላሲኮ ድል ወደ ዋና ከተማው ሄደ!

በ 1930 ዎቹ – ሪያል ማድሪድ በላሊጋው ኤል ክላሲኮ ታሪክ ውስጥ ትልቁን ድል አስመዘገበ

የ 1934-35 የኤል ክላሲኮ ጨዋታዎች አስገራሚ ነበሩ ፣ ባርሴሎና በሎስ ኮርትስ 5-0 አሸንፏል ግን ሪያል ማድሪድ በቻማርቲን አስገራሚ 8-2 አግኝቷል።  በ30 ደቂቃዎች ውስጥ ባለሜዳው ቡድን 5-1 ከፍ ብሏል ፣ ይህም የባርሴሎናው ሃንጋሪ አሰልጣኝ ፌረንክ ፕላትኮ የተጭበረበረ መስሎት ኳሱ ከእረፍት መልስ እንዲለወጥ ጠይቋል! ያ ግን ምንም ለውጥ አላመጣም ባለሜዳው የላሊጋውን የኤል ክላሲኮ ትልቁን ድል አስመዝግቧል!

1950s – የስፔን የመጀመሪያው በቴሌቪዥን የተላለፈ የእግር ኳስ ግጥሚያ

ኤል ክላሲኮ በየካቲት 15 ቀን 1959 በስፔን ቴሌቭዥን የተላለፈ የመጀመሪያው የእግር ኳስ ጨዋታ መሆን ታሪክ ሠራ። ከጨዋታው በፊት ቴሌቪዥኖችን ለማግኘት ሽኩቻ ነበር። ሪያል ማድሪድ ታላቆቹን አልፍሬዶ ዲ ስቴፋኖ እና ፌረንክ ፑስካስን የያዘው ቡድን በዚያ ቀን በበርናባው 1-0 ቢያሸንፍም ባርሴሎና በሰባት ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያውን የላሊጋ ዋንጫ እንዳያነሳ ማድረግ አልቻለም!

1960 – ዲ ስቴፋኖ ባርሴሎናን መጉዳቱን ቀጥሏል

አርጀንቲናዊው የሪያል ማድሪድ ተጫዋች የኤል ክላሲኮ ኮከብ ግብ አግቢ ሲሆን አሁንም በ 1953 ሪያል ማድሪድን በልጠን አስፈርመነዋል ብለው በስህተት ካሰቡ በኋላ ባርሴሎናን ደጋግሞ አሰቃይቷል። በታህሳስ 1960 በቅርቡ በተከፈተው ካምፕ ኑ 5-3 ሲያሸንፉ ለሪያል ማድሪድ ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል።

በ 1970 ዎቹ – ክራዩፍ የበላይነትን ወደ ባርሴሎና ይመልሳል

grup14.com

ጆሃን ክራይፍ በ 1974 የባርሴሎና ተጫዋች መሆኑ የኤል ክላሲኮን ሚዛን ወደ ካታላን ዋና ከተማ እንዲመለስ ረድቶታል ፣ እና የደቹ ተጫዋች በዚያ ዓመት በላ ሊጋው በርናባው ውስጥ ኤል ክላሲኮን 5-0 ባሸነፈበት ጨዋታ ያደረገው እንቅስቃሴ አሁንም ድረስ ይነገራል። ኤል ሳልቫዶር ባርኮሎናን በዚያ ወቅት ላሊጋ ማዕረግ እንዲያሸንፍ አነሳስቷል ፣ ግን ከሁሉም በላይ ደግሞ እስከ ዛሬ ድረስ የክለቡን ማንነት የቀረፀ የእግር ኳስ ፍልስፍና አስገብቷል።

1980 ዎቹ – የኩንታ ዴል ቡትሬ ትውልድ አምስት አሸነፈ

ሪያል ማድሪድ መጋቢት 1986 በበርናባው ባርሴሎናን ሲጋፈጡ ሪያል ማድሪድ ለስድስት ዓመታት ላሊጋ ሻምፒዮን አልሆነም። የክለቡ ባለታሪኮች ኤሚሊዮ ቡትራጎኦ እና ጆርጅ ቫልዶኖ ከግብ አስቆጣሪዎች መካከል በሆኑበት ጨዋታ ፣ 3-1 አሸንፎ የላሊጋውን ዋንጫ ለሪያል አሳልፎ ሰጥቷል። ማድሪድ እና በቀሪዎቹ አስርት ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማያውቅ የበላይነት ነበረው። እንደ ቡትራጎኦ ፣ ሚካኤል እና ማኑዌል ሳንቺስ ያሉ ብቃት ያላቸው ተጫዋቾችን የያዘው የኩንታ ዴል ቡይት ትውልድ ተብሎ የሚጠራው ቡድን ከ 1986 እስከ 1990 ባለው ጊዜ ውስጥ እያንዳንዱን የላሊጋ ዋንጫ አሸንፏል!

በ 1990 ዎቹ – ክራይፍ አሰልጣኝ ሆኖ ተመለሰ

ክራዩፍ ወደ ባርሴሎና በአሰልጣኝነት መመለሱ ከ 1991 እስከ 1994 በተከታታይ አራት የላሊጋ ርዕሶችን ያሸነፈ የ “ድሪም ቡድን” አስገኘ። ሆኖም በ 1990 ዎቹ ውስጥ የኤል ክላሲኮ ታሪክ በሁለት አስደናቂ ውጤቶች ይታወሳል። ሪያል ማድሪድም ተመሳሳይ በሆነ ውጤት ከ 12 ወራት በኋላ አገኘ ከግብ አስቆጣሪዎቹም የወደፊቱ የባርሴሎና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ነበረበት!

2000 ዎቹ – ሮናልዲንሆ በርናባውን አስደመመ

fcbarcelona.com

እ.ኤ.አ ህዳር 2005 በሳንቲያጎ በርናባው የተደረገው ጨዋታ የዘመኑ ምርጥ ኤል ክላሲኮ ነበር። ባርሴሎና ቀደም ብሎ መሪነት ወስዷል ፣ ግን የሮናልዲንሆ ትርኢት ገና መጀመሩ ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ ላይ ብራዚላዊው ከራሱ ግማሽ ወደ ፊት በመሮጥ ፣ ሰርጂዮ ራሞስን ታክሎች በቀላሉ በማለፍ ፣ ኢቫን ሄልጌራን አልፎ ፣ ሮቤርቶ ካርሎስንም አጥፎ ኢኬር ካሲላስን አሳልፎ አስቆጥሯል። ከ 15 ደቂቃዎች በኋላ እንደገና ራሞስን አልፎ በቀላሉ ካሲላስ ላይ በማስቆጠር ውጤቱን 3-0 አደረገ። በበርናባው የተገኙ ደጋፊዎች ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አድናቆታቸውን አሳዩ ከተቀመጡበት በመነሳት አስገራሚ እንቅስቃሴውን አድንቀዋል!

የ 2010 ዎቹ – ሜሲ በበርናባው ላይ አሻራውን አሳርፏል

ሊዮኔል ሜሲ በላሊጋው የኤል ክላሲኮ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሲሆን በጨዋታው ላይ የነበረው ተፅዕኖ የማይታመን ነበር። አንድ ነጠላ እንቅስቃሴ ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆንም ፣ በ 2017 ባርሴሎና በበርናባው 3-2 ሲያሸንፍ በተጨማሪ ደቂቃ ያስቆጠረው ግብ ከሁሉም በኤል ክላሲኮ ታሪክ የበለጠ አስገራሚ እና ድራማዊ ነበር። ከግቡ በኋላ በበርናባው ደጋፊዎች ፊት ማልያውን አውልቆ የያዘበት ሁኔታ ከትውስታ የሚጠፋ አይደለም!

2021 – ባርሴሎና ከ ሪያል ማድሪድ

ባርሴሎና ከዚህ አስደናቂ ጨዋታ በፊት ከስምንት ግጥሚያዎች በኋላ በላሊጋው ሰንጠረዥ ውስጥ ሰባተኛ ላይ ይገኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የካርሎ አንቸሎቲ ሪያል ማድሪድ ካለፉት ሁለት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ በመውሰድ ከአንደኛ ደረጃ ላይ ወርዷል።

ካሪም ቤንዜማ ምርጥ አቋም ላይ እንደመሆኑ እና ቪኒሲየስ ጁኒየርም በመጨረሻ የተወራለትን ያህል እየተንቀሳቀሰ እንደመሆኑ ፣ ሪያል በውድድሩ ውስጥ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ መሆናቸው ብዙም አያስገርምም ፣ እና በኤል-ክላሲኮ ያላቸው የሶስት ጨዋታ ተከታታይ አሸናፊነት ቡድናቸው ውስጥ በእርግጠኝነት የራስ መተማመን ይፈጥራል።

ባርሴሎና በሜዳው ውስጥ ጥሩ አቋም እያሳየ ነው እና ለሎስ ብላንኮዎች ጥሩ ፈተና መሆን ይችላሉ ፣ ነገር ግን የሮናልድ ኮማን ቡድን በዚህ የውድድር ዘመን በየትኛውም ግጥሚያዎቻቸው አሳማኝ አይመስልም ፣ እናም በሜዳቸው ደጋፊዎች ይሸነፋሉ ብለን እንጠብቃለን። የእኛ ግምት ሪያል ማድሪድ 2-0 ያሸንፋል ነው።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football