Connect with us
Express news


Football

የዋና ከተማው ፍልሚያ፦ በጥሩ አቋም የሚገኘው ናፖሊ ወደ ሮማ ይጓዛል!

Clash in the Capital: High-Flying Napoli Travel to Roma!
upsportnews.com

ናፖሊ አስገራሚ 100% የማሸነፍ ሪከርድ ማስቀጠል ይችላል ወይስ ሮማ በኖርዌይ ውስጥ ከደረሰውን አሳፋሪ ሽንፈት ያገግማል ?

በዚህ የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ይ ዴል ሶሌ ድርቢ ፣ የሴሪኣው መሪ ናፖሊ ፍጹም የማሸነፍ ጉዞውን ለማስቀጠል ወደ ሮም ይቀናል። ሁለቱ የደቡባዊው የጣሊያን ግዙፍ የእግር ኳስ ቡድኖች በዋና ከተማው ውስጥ በዘጠኝ ነጥብ ተበላልጠው የሚፋለሙ ሲሆን ፣ ሮማውያን ሆሴ ሞሪንሆ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ከተሾሙ በኋላ የመጀመሪያ ፈታኝ ግጥሚያቸው ይሆናል።

ባለ ተሰጥኦው ተጫዋች በመጨረሻ የሳምንቱ ቀናት በጉልበቱ ላይ ጉዳት ከደረሰ በኋላ ፣ ሮማዎች ኒኮሎ ዛኒዮሎን በ እሁዱ ጨዋታ እንዲሚሰለፍ ተስፍ አድርገዋል። በኖርዌይ በቦዶ/ግሊምት 6-1 በተሸነፉበት የአውሮፓ ኮንፈረንስ ግጥሚያ ላይ ተጫዋቹ እንዳይሰለፍ አድርጎታል።

ጆርዳን ቬሬቱት ፣ ጂያንሉካ ማንቺኒ ፣ ታሚ አብርሃም እና የክለቡ ካፒቴን ሎሬንዞ ፔሌግሪኒ ወደ በምርጥ 11 ስለሚገቡ ፣ ጣሊያናዊው ተጫዋች የጆዜ ሞሪንሆ ከሚያደርግቸው በርካት የአሰልለፍ ለውጥ መካከል ይሆናል።

footballtransfertavern.com

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፣ ጊኒያዊው አማዱ ድያዋራ ፣ ቦርጃ ማዮራል እና ማራሽ ኩምቡላ በዚህ ጨዋታ የመሰለፍ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።

ክሪስ ስሞሊንግ አሁንም በጉዳት እየተሰቃየ ስለሆነ ለሳምንት ከሜዳ ውጭ ይሆናል ፣ እናም ምናልባት እንግሊዛዊው ተከላካይ በሮጀር ኢባኔዝ ሊተካ ይችላል።

የናፖሊው አሰልጣኝ ሉቺያኖ እስፓሌቲ እንደ የሮማው ፖርቹጋላዊ አሰልጣኝ ባይሆንም ወደ ስታዲዮ ኦሊምፒኮ ተመልሶ ቡድኑን ሊቀይር በሚችልበት ዝግጅት ላይ ነው።

ኮስታስ ማኖላስ  በተጠባባቂ ወንበር ላይ ይቀመጣል ፣ ማሪዮ ሩይ ደግሞ ከአውሮፓ እገዳ ተመልሶ የእንግዳው ቡድን አማራጮች የበለጠ ያሰፋል። የቡድኑ ተጫዋቾች ኬቨን ማልኮት እና አዳም ኦውናስ ፣ በዚህ ግጥሚያም የሚሰለፉ አይመስልም።

ከፊት መስመር ፣ ቪክቶር ኦስሚሄን እና ማቲዮ ፖታኖ ፣ ከ ሎሬንዞ ኢንስኜ ጋር ይሰለፋሉ ፣ እና በመሃል ሜዳ ፋቢያን ሩይዝ ወደ መሃለኛው ሶስትዮች የ ናፖሊ ክፍል ይመለሳል።

napolicalciolive.com

ሮማዎች በዚህ ዓመት ብዙ ዓይነት ችግሮች ቢገጥሟቸውም በሜዳቸው እስጥ ፈጽሞ የማይበገሩ ናቸው ፣ ስለሆነም ነጥቦችን ይዘው ለመውጣት እና ከአስቸጋሪው ሳምንት ማገገም መቻል አለባቸው። በዚህ ምክንያት የናፖሊ 100% ሪከርድ ይጨናገፋል። ግጥሚያው 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ይጠናቀቃል ብለን እናስባለን።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football