Connect with us
Express news


Football

ሊድስሶች ከዎልቭሶች ጋር ከመመራት ተነስተው አንድ ነጥብ ይዘው መውጣት ችለዋል!

Leeds Storm Back to Salvage a Point Against Wolves!
yorkshireeveningpost.com

በዚህ የፕሪሚየር ሊግ ፍልሚያ ሃዋንግ ሄ-ቻን ለዎልቭሶች በጨዋታው የመጀመርያዎቹ ደቂቃ ውስጥ ግብ አስቆጥሯል። ሮድሪጎ የአቻነት ግብ ከማስቂጠሩ በፊት ፣ ራፊንሃ በቁርጭምጭሚት ጉዳት ከሜዳ ለመውጣት ተገዷል።

ዎልቭሶች ቅዳሜ በተደረገው የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ ላይ ፣ ሃዋንግ ሄ-ቻን ባስቆጠራት ግብ መምራት ችለው የነበሩ ቢሆንም ፣ አጥቂው ሮድሪጎ በባከነ ሰአት ውስት ባስቆጠራት ፍፁም ቅጣት ምት ፣ ባለሜዳዎቹ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት እንዲለያዩ አድርጓል።

የማርሴሎ ቢኤልሳ ቡድን ደካማ አቋም አሳይቷል። ሆኖም ፣ በመጨረሻው ደቂቃ ውስጥ ግብ አስቆጥረው አንድ ነጥብ ማግኘት ችሏል።

ሃዋንግ በ 10 ኛው ደቂቃ ላይ ግብ አስቆጥሯል። ኔልሰን ሴሜዶ ተከላካዩን አታሎ አልፎ ኳሱን ለራውል ጂሜኔዝ ካሻገረ በኋላ ከቅርብ ርቀት ላይ በውጪኛው እግሩ አስቆጥሯል። ሜክሲካዊው አጥቂ ያደረገው ጥረት ተገጭቶ ወደ ደቡብ ኮሪያዊው አጥቂ ተመለሰ እናም በጥሩ አጨራረስ ኳስ ከመረብ አገናኝቷል።

thesun.co.uk

ሊድስ በመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለ ቡድን ነበር ነገር ግን በደንብ የተቆለፈው የዎልቭሶችን የተከላካይ መስመር ላይ ጫና መፍጠር አልቻለም። ጃክ ሃሪሰን ኢላማዉን ያልጠበቀ ሙከራ ከማድረጉ በፊት ፣ የእንግዳው ቡድን ግብ ጠባቂ ጆሴ ሳ ከርቀት የተሞከረው የራፊንሃ ጥረትን አድኗል።

የባለሜዳው ቡድን ግብ ጠባቂ ኢላን መስሊይ ፣ ከእረፍት መልስ ራያን አይት ኑሪ ያደረገው የመሬት ለመሬት ሙከራ አድኗል እና ሊድስ ጆ ጌልሃርትትን በ 79 ኛው ደቂቃ ድንቅ ሙከራ በ ሳ ከመጨናገፉ በፊት ብዙ እድሎችን ለመፍጠር ሲታገሉ ነበር።

የዎልቭስ ተከላካይ ሮማን ሳይስ አስቀያሚ ጥፋት ከሰራ በኋላ ራፊንሃ በ ክሪሴንስዮ ሳመርቫይል መተካት ነበረበት ፣ ይህም ሊድስ ላይ ተጨማሪ ችግር ፈጥሯል ፣ ነገር ግን ባለሜዳው ቡድን ጉዳቱ ጫና አልፈጠረበትም።

በሁለተኛ አጋማሽ ተቀይሮ የገባው ጌልሃርት ፣ ሴሜዶን ወደ ታች እንዲጎትተው ያስገደደው እና ፍፁም ቅጣት ምት እንዲያሸንፍ ያስቻለው ጥሩ የግል ብቃት አሳይቷል። ሮድሪጎ ሳን በተሳሳተ መንገድ በመላክ ፍፁም ቅጣት ምቱን አስቆጥሯል።

የሊጉ ያለመሸነፍ ጉዞን አራት ያደረሰው የብሩኖ ላጌ ዎልቭስ ከዘጠኝ ጨዋታዎች 13 ነጥብ በመሰብሰብ 10 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሊድስ በሰባት ነጥብ 17 ኛ ደረጃ ላይ ይቆያል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football