Connect with us
Express news


Football

ፊል ፎደን ሲቲ ብራይተን ባሸነፈበት ግጥሚያ ላይ አስደናቂ ብቃት አሳይቷል!

Stunning City Beat Brighton as Phil Foden Puts on Brilliant Display
fcbarcelona.com

ማንችስተር ሲቲ ብራይተንን በማሸነፍ በፕሪሚየር ሊጉ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ ባለበት ግጥሚያ ላይ የ 21 ዓመቱ ፊል ፎደን ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል።

ማንችስተር ሲቲ በመጀመሪያ አጋማሽ አስደናቂ አቋም አሳይቶ በአሜክስ ስታዲየም ብራይተንን 4-1 ለማሸነፍ ችሏል።

ብራይተን ግጥሚያውን በማሸነፍ በደረጃ ሰንጠረዙ ከሲቲ በላይ ሊቀመጥ ይችል ነበር ፣ ነገር ግን በ 31 ደቂቃ ውስጥ ሶስት ግቦችን ማስቆጠር የቻለውን የእንግዳው ቡድን የማጥቃት እንቅስቃሴ መቋቋም አልቻለም። ሁለገብነቱ የተመሰከረለት የ 21 ዓመቱ ፊል ፎደን የጨዋታው ኮከብ ነበር።

mancity.com

የሲቲ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከጨዋታው በኋላ “በፊት መስመር መጫወት ይችላል ፣ እያንዳንዱን ተጫዋች እያታለለ ከግድ ግብ መድረስ ይችላል። እንደ ሐሰተኛ ዘጠኝ ፣ በ ቀኝ እና በ ግራ ክንፍ መጫወት ይችላል” ብለዋል።

“ጥሩ ግብ የማስቆጠር ብቃት ያለው የመሃል መስመር ተጫዋች ነው። ገና ወጣት ከመሆኑ አንፃር አሁንም ማሻሻል ይችላል።”

ፊል ፎደን ከጃክግሪሊሽ የተሻማለትን ኳስ በማስቆጠር ውጤቱ 2-0 እንዲሆን አድርጓል ፣ ይህም በውድድር ዘመኑ ሶስተኛ ግቡ ሆኖ ተመዝግቧል።

ሳንቼዝ የግሬይሽስን ዝቅተኛ ጥረት ከተፋው በኋላ ፣ ፎደን ጃሱስ የመታውን ኳስ በመግጨት የውድድር ዘመኑ አራተኛ ግቡ አስቆጥሯል። እንግሊዛዊው ተጫዋች ከእረፍት በፊት ሃትሪክ ለመስራት የሚያስችለውን አስደናቂ ሙከራ ቢያደርም ፣ ሳንቼዝ እንደምንም ኳሱን በማዳን እድሉን አምክኖለታል።

goal.com

ከእረፍት በኋላ ብራይተን የተሻሉ ነበሩ ፣ እና ኤደርሰን የፓስካል ግሮስ እና የላንዶሮ ትሮሳርድ ጥረቶችን ለማስቆም ንቁ መሆን ነበረበት።

አሌክሲስ ማክ አሊስተር በመጨረሻ ደቂቃዎች ውስጥ በኢኖክ ምዌፑ ላይ በግብ ክልል ውስጥ በተሰራ ጥፋት የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት በማስቆጠር የኤደርሰንን ግድ ደፍሯል።

ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ብራይተን ከሁለት ጎሎች መመራት ተነስቶ የጋርዲዮላን ቡድን አሸንፎ ነበር ፣ ነገር ግን እንግዳው ቡድን ሪያድ ማህሬዝ በተጨማሪ ሰአት ባስቆጠራት ግብ ድላቸውን አረጋግጠዋል ፣ ይህም ከመሪው ቼልሲ በ2 ነጥብ ብቻ ርቆ እንዲቀመጥ አስችሎታል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football