Connect with us
Express news


Football

አስደናቂው ሊቨርፑል አምስት ግብ አስቆጥሮ ማንችስተር ዩናይትድን አሸነፈ!

Sensational Liverpool Thrash Manchester United in Five-Goal Thriller!
premierleague.cz

ማንቸስተር ዩናይትድ በሜዳው በሊቨርፑል አሰቃቂ ሽንፈት አስተናግዷል ፣ አሰልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻየርም ከፍተኛ ጫና ውስጥ ገብቷል።

እሁድ ፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ኦሌ ጉናር ሶልሻየር በሜዳቸው እና በደጋፊዎች ፊት አሳፋሪ በሆነ የ 5 ግብ ሽንፈት ደርሶባቸዋል።

የሊቨርፑል ዋና ተጫዋች መሐመድ ሳላህ ነበር። ግብፃዊው የፊት መስመር ተጫዋች አደናቂ ነበር እናም ሀትሪክ ሰርቷል ፣ ይህ ማለት አሁን በተከታታይ 10 ጨዋታዎች ላይ ጎል አስቆጥሯል ማለት ነው።

chinadaily.com

ሶልሻየር እና ተጫዋቾቹ ደካማ እና ያልተደራጀ አቋም አሳይተው በሜዳቸው ውስጥ በተለይም በመጀመርያው አጋማሽ ላይ በደጋፊዎቻቸው ኋይለኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።

ሊቨርፑል ናቢ ኬታ ፣ ሳላህ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ በማስቆጠር ገና በ 5 ደቂቃ ላይ በዩናይትዶች ላይ አስጨናቂ ጫና ፈጥረዋል። ከስምንት ደቂቃዎች በኋላ ዲዮጎ ጆታ ከትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ የተሻማልርትን ኳስ ተንሸራቶ በአስቆጠር ሁለተኛውን ግብ አክሏል።

በዚህ ሰአት ሊቨርፑል ዩናይትድን በበላይነት ተቆጣጥሮ ነበር ፣ እናም የወቅቱ ምርጥ ተጫዋች ሞሃመድ ሳላህ ፣ ኬታ ያሻማለትን ኳስ ከመረብ ጋር በማግርናኘት የመጀመሪያውን ግብ አግኝቷል ፣ ከዚያ በኋላ የዩናይትዱን ግብ ጠባቂ ዴቪድ ደ ሂያን በዝቅተኛ ምት አሸነፈ ይህም የርገን ክሎፕን ቡድን በመጀመርያው አጋማሽ በአራት ግብ ልዩነት እንዲመራ አስችሎታል።

football365.com

በሁለተኛው አጋማሽ ሶልሻየር ፣  ፖል ፖግባ በ ሜሰን ግሪንዉድ ቀይሮ አስገብቷል ፣ ነገር ግን በዚያን ሰአት ብዙ የዩናይትድ ደጋፊዎች ተጨማሪ ውርደት ለማየት ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት መቀመጫቸውን ለቀው ወጥተዋል።

ቀኑ ለቀዮቹ በጣም መጥፎ በነበረበት ሰአት ፣ ግሪንዉድን ተክቶ ወደ ሜዳ የገባው ፖግባ እንኳን በአሰቃቂ ሁኔታ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግዷል። ሳላ የጆርዳንን ሄንደርሰን ድንቅ ኳስ ወደ ግብ በመቀየር ሃትሪክ ከሰራ በኋላ ፣ ፖግባ ኬታ ላይ አሰቃቂ ጥፋት በመስራቱ ከሜዳ ተወግዷል ፣ ሃኪሞችም ናቢ ኬታን ተሸክመው ወጥተዋል።

ሊቨርፑል ቀሪዉን ደቂቃ በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች አቋርጠዉት የወጡትን ጨዋታ በበላይነት አሸንፎ መደበኛ ጨዋታው አጠናቋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football