Connect with us
Express news


EFL Cup

ሌስተር እና ብራይተን በካራባኦ ዋንጫ ይፋለማሉ!

Leicester Battle Brighton For the Carabao Cup!
https://foxesofleicester.com/

በነገው የካራባኦ ካፕ ጨዋታ ሌስተር ሲቲ ብራይተን ኤንድ ሆቭ አልቢዮንን በኪንግ ፓወር ስታዲየም ያስተናግዳል። ከሁለቱ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ (ኢፒኤል) ቡድኖች ወደ ኢኤፍኤል ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ማለፍ የሚችለው የትኛው ነው?

ሌስተር በሁሉም ውድድሮች አራት ጨዋታዎችን በማሸነፍ ላይ ይገኛል እና ይህንንም ለማስቀጠል ይፈልጋሉ። ብራይተን በበኩሉ በቅርቡ ከጥሩ አቋሙ የወረደ ሲሆን ከአራት ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በኋላ ባለፈው ቅዳሜ በማንቸስተር ሲቲ 4-1 ተሸንፏል። ይህ ሁሉ ሲሆን ሴጉልስ አሁንም በ ኢፒኤል ውስጥ አምስተኛ ደረጃን ሲይዝ ሌስተር ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ነው።

ብሬንዳን ሮጀርስ በዚህ የውድድር ዘመን መጀመሪያ ላይ ቀበሮዎቹ መጥፎ አቋም በማሳየታቸ ውተጨንቆ ነበር ነገር ግን በመጨረሻዎቹ ጥቂት ውጤቶች አማካኝነት ነገሮች ወደ ትክክለኛው መንገድ የሚመለሱ ይመስላል።

እና በእርግጥ ቡድኑ ታታሪ ቢሆንም፣ በአሁኑ ጊዜ አንድ ስም በየቦታው እየገነነ መጥቷል፣ የዛምቢያዊው አጥቂ ፓትሰን ዳካ። እንዴት? ምክንያቱም ለሌስተር ባደረጋቸው ያለፉት 3 ጨዋታዎች አምስት ጊዜ (አራቱን ከስፓርታክ ሞስኮ ጋር ባደረገው ግጥሚያ) አስቆጥሯል ፣ እንዲሁም አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ አቀብሏል። ዳካ በጥሩ አቋም ይገኛል። ጥያቄው ሮጀርስ ኮከብ አጥቂው ብምርት 11 ይሰለፋል ወይንስ ወንበር ላይ ይተወውና እንደ ሃርቪ ባርነስ ወይም አዮዜ ፔሬዝ ካሉ አዲስ ተጫዋቾችን ያሰልፋል?

https://www.theguardian.com/

ግሬሃም ፖተር በዘንድሮው የውድድር ዘመን በሁለቱ ቀደምት የኢኤፍኤል ዋንጫ ግጥሚያዎች ላይ እንዳደረገው ሁሉ አሁንም አዳዲስ ተጫዋቾች ይዞ ይገባል። በመጨረሻም ኢቭ ቢሱማ ለአንድ ወር ያህል ከጠፋ በኋላ ወደ አሰላለፍ ሲመለስ እና ላምፔቴም እንዲሁ እድል ያገኛል ብለን እንጠብቃለን።

ሁለቱ ቡድኖች አንዳቸው ለሌላው እንግዳ አይደሉም። ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት በኢፒኤል ከአንድ ወር በፊት ብቻ ሲሆን ብራይተን 2-1 አሸንፏል። ሌስተር ከዛ በፊት የነበሩት ሁለት ጨዋታዎች በአንድ ጎል ልዩነት ብቻ አሸንፏል። ቀበሮዎቹ አሁን ጥሩ አቋም ላይ ያሉ ቡድን በመሆናቸው በተቀራራቢ ውጤት እንደሚያሸንፉ ይጠብቁ።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in EFL Cup