Connect with us
Express news


Bundesliga

የምንግዜም ምርጥ የቡንደስሊጋ ግቦች! – ክፍል 1

Greatest Bundesliga Strikes of All-Time! -Part I
beinsports.com

በጀርመን ከፍተኛ ሊግ ታሪክ የምንጊዜም ምርጥ ግቦች የቶቹ ናቸው? በጣም ቆንጆ የሆኑትን ስድስት ግቦች እንመልከት!

6. ዲያጎ – ዌርደር ብሬመን ከ አለማኒያ አቸን – 2007

ብራዚላዊው ዲዬጎ ይህንን ድንቅ ጎል ያስቆጠረው በ2007 ነው። የአማንያ አቸኖች በረኛ ክርስቲያን ኒችትን የማዕዘን ምት ለመሻማት በመጣበት ነው ይህን የአመቱ ምርጥ ግብ ለወርደር ብሬመን ያስቆጠረው።

youtube.com

ኳሷ ዲያጎ እግር ላይ ቲወድቃለች ፣ የተጋጣሚው አማካዩ ማቲያስ ሌማን ምንም ቢጥርም ከ69 ያርድ ርቀት ላይ በማስቆጠር ውጤቱን 3-1 አደረገው።

“እግር ኳስ ሁል ጊዜ በስሜቶች ላይ የተመረኮዘ ነው ። በጥሩ ሁኔታ ለመጫወት ደስተኛ እና ነፃ መሆን አለብን እና በዚያን ጊዜ የተፈጠረው የዚያ ውጤት ነበር” ሲል ዲያጎ በኋላ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግሯል።

5. ጄይ-ጄይ ኦኮቻ – አይንትራክት ፍራንክፈርት ከ ካርልስሩሄ – 1993

ናይጄሪያዊው አማካኝ ጄይ-ጄይ ኦኮቻ በታዋቂው ግብ ጠባቂ ኦሊቨር ካን ላይ ያስቆጠረው ድንቅ ግብ አሁን ወደ 30 አመታት ሆነውታል። ሆኖም የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ ዩርገን ክሎፕ አሁንም ይህ ግብ በቡንደስሊጋ ታሪክ ውስጥ ምርጡ እንደሆነ ይናገራል።

“በጀርመን እግር ኳስ ታሪክ እጅግ አስደናቂውን ጎል አስቆጥሯል። ካን እና ተከላካዮቹ ኳሱን መረብ ላይ ከማስገባቱ በፊት አምስት ደቂቃ ያህል መሬት ለመሬት አንከራቷቸዋል!” ሲል ክሎፕ ተናግሯል።

youtube.com

የያኔው ወጣት ኦኮቻ በሁለተኛው አጋማሽ ለአይንትራት ፍራንክፈርት ከተጠባባቂ ወንበር ተነስቶ ጨዋታውን በማጣጠፍ ችሎታው ቀይሮታል። አንዴ ወደዚህ ከዚያ ወደዛ እያለ ሁሉንም የካርልስሩሄር ተከላካዮችን እና ካን ሙሉ በሙሉ ግራ በማጋባት ኳሱን ወደ መረቡ በማስገባት ሙሉ ስታዲየሙን አስደምሟል!

4. ግራፊት – ዎልፍስቡርግ ከ ባየር ሙኒክ – 2009

ብራዚላዊው አጥቂ ግራፊት በ2009 ይህንን አስማታዊ ግብ ለአለም ሰጠ። በቡንደስሊጋ ታሪክ በጀርመን ቴሌቪዥን የታየ ምርጥ ጎል ተብላለች።

youtube.com

ተአምሩ የተከሰተው በ16፡05 ሲሆን ከስምንት አመታት በፊት ኑሮውን የቆሻሻ ከረጢት በመሸጥ ይመራ የነበረው ብራዚላዊው የዎልፍስቡርግ አጥቂ ግራፊት በመጀመሪያ የባየርኑን ምስኪን አንድሪያስ ኦትልን በቀላሉ እጥፍጥፍ ያደርገዋል። ከዚያም ክርስቲያን ሌልን እና ግብ ጠባቂውን ሚካኤል ሬንሲንግ ያልፋል ከዚያ ብሬኖን እና ፊሊፕ ላህምን ጥሎ ይሄዳል። ከዚያም ግቡን ያስቆጠረው ቀስ ብሎ በተረከዙ ነው ፣ ነገር ግን የኳሱ ሃይል ሁለት የባየርን ተከላካዮችን እና መስመሩን አልፎ ለመግባት በቂ ነበር!

ይቀጥላል…

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Bundesliga