Connect with us
Express news


Bundesliga

የዓለማችን ምርጥ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋቾች፡ የ2021 ወርቃማ ታዳጊ ሽልማትን ማን ያሸንፋል?

The Best Young Footballer in the World: Who Will Win the 2021 Golden Boy?
goal.com

የጎልደን ቦይ ሽልማት በስፖርት ጋዜጠኞች እድሜው ከ21 አመት በታች ለሆነ እና ባለፈው አመት ምርጥ ነው ለተባለ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋች የሚሰጥ ሽልማት ነው። ዘንድሮ ማን ያሸንፋል? የማሸነፍ እድል ያላቸውን ወጣቶች እንመልከት።

ጁድ ቤሊንግሃም

skysports.com

18 አመቱ ብቻ ሊሆን ይችላል, ነገር ግን ጁድ ቤሊንግሃም ካሁኑ በእግር ኳስ አለም ላይ የራሱን አሻራ እየጣለ ነው። ለቦሩሲያ ዶርትሙንድ ቋሚ ተጨዋች የሆነ ሲሆን በመሀል ሜዳ ላይ አስጨናቂ ተጫዋች ሆኗል። ከአሁኑ 120 ሚሊዮን ዩሮ የተገመተ ነው ተብሏል። የእግር ኳሱ አለም ከእሱ ጋር በትክክል ፍቅር ይዞታል።

የእግር ኳስ ጋዜጠኛ ላርስ ሲቨርስተን “ሁሉንም ንጥረ ነገሮች የያዘ ሰው” ሲል ተናግሯል “[ዶርትመንድ] ተስተካክሎ ያላለቀ አልማዝ እና ወደ ምርጥ የመሃል ተጫዋች ሊቀይሩት የሚችሉት ተጫዋች አድርገው ያዩት ነበር” ሲል ተናግሯል።

“ግን ገና ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ዝግጁ ነበር ማለት ይቻላል።”

የቡንደስሊጋው ጋዜጠኛ አርቺ ራይንድ-ቱት “ከሜዳ ውጪም ውስጥም በጣም የሚጋባ ጥሩ ስሜት አለው” ብሏል።

በዶርትሙንድ የመልበሻ ክፍል ውስጥ ያሉ ከፍተኛ ባለ ሥልጣኖች ሲያመሰግኑት ቆይተዋል – ማትስ ሀምልስ 25 ጊዜ ፍቅሩን እንደገለፀለት ፣ ማርኮ ሬውስ ጨዋታውን የሚጫወትበት መንገድ እና ለመሮጥ ያለውን ፍላጎት ስቴቨን ጄራርድን ትንሽ እንደሚያስታውሰው ተናግረዋል።

ቡካዮ ሳካ

benchwarmers.com

ቡካዮ ሳካ 20 አመቱ ነው፣ ነገር ግን ከ2019/2020 የውድድር ዘመን በፊት ከሃሌ ኢንድ አካዳሚ ከተመረቀ በኋላ ምርጥ ተጫዋች ሆኗል።

ገና 20 አመቱ ሳይሞላው የክንፍ ተጫዋቹ 92 ጨዋታዎችን አድርጎ ለአርሰናል በወጣትነት ለክለቡ ከተጫወቱ ከምርጥ 5 ውስጥ አስቀምጦታል።

በዚህ ጊዜ ያሳየው ጥሩ ብቃት ለጋሬዝ ሳውዝጌት የዩሮ 2020 ቡድን እንዲጠራ ረድቶታል ቡድኑ ወደ ፍፃሜው እንዲደርስ ቁልፍ ሚናም ተጫውቷል። በግራ ኋላ ብዙ ጊዜ ቢጀመርም 12 ጎሎችን እና 21 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

የገበያ ዋጋው አሁን ከ70 እስከ 80 ሚሊዮን ዩሮ አካባቢ ነው ተብሏል።

ሜሰን ግሪንዉድ

pl.com

ሜሰን ግሪንዉድ ለማንችስተር ዩናይትድ ፍጹም ልዩ ተጫዋች ሆኗል። በአውሮፓ ውድድር ለቡድኑ ትንሹ ጎል አስቆጣሪ (17 አመት ከ 353 ቀናት) ሲሆን ፣ በ2000ዎቹ በኋላ ተወልዶ ለክለቡ ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች እና ከ20ኛ አመት ልደት በፊት 100 ጨዋታዎችን ያደረገ ፣ ከቤስት ፣ኋይትሳይድ ፣ዱንካን ኤድዋርድስ እና ራያን ጊግስ ቀጥሎ አምስተኛው የዩናይትድ ተጫዋች ነው።

በ18 አመቱ ከግሪንዉድ (17፣ ከቤስት ፣ዋይኒ ሩኒ እና ብሪያን ኪድ እኩል) በላይ በአንድ የውድድር አመት ብዙ ጎሎችን ያስቆጠረ ማንም የዩናይትድ ተጫዋች የለም እና 20 የፕሪምየር ሊግ ጎሎችን ካስቆጠሩ 4 ታዳጊዎች ውስጥ አንዱ ነው (ሩኒ ፣ ሮቢ ፉለር እና ማይክል ኦወን)

ኤድዋርዶ ካማቪንጋ

flashsport.com

ካማቪንጋ ለፈረንሣይ የክፍለ ዘመኑ ትንሹ ግብ አስቆጣሪ ነው ፣ ወደፊት ታላቅ ለመሆን ሁሉንም ባህሪያት ያለው አማካይ ሆኖ ታይቷል። የ18 አመቱ ወጣት ከበርካታ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ የቆየ ሲሆን በመጨረሻም በ40 ሚሊየን ዩሮ ለሪያል ማድሪድ ከሬኔስ በስድስት አመት ኮንትራት ፈርሟል።

ፔድሪ

fcbarcelona.cz

ፔድሪ ለማየት አስደሳች ተጫዋች ነው ፣ እናም በ2021 ወርቃማው ታዳጊ ሽልማትን ለማሸነፍ ከፍተኛ ተጠባቂ ሆኗል። በሚገርም እይታው ፣ኳስ በመያዝ ብቃቱ ፣ በትክክለኛ ኳስ ቅብብሉ እና ጎል በማስቆጠር ችሎታው በዚህ አመት ከተሻሻሉ ጥቂት የባርሴሎና ተጫዋቾች አንዱ ነው። በዚህ ወቅት አማካዩ በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው 52 ጨዋታዎች አራት ጎሎች እና 6 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አቀብሏል ፣ ይህም በዚህ ክረምት የስፔን ብሄራዊ ቡድንን በአውሮፓ ሻምፒዮና እንዲወክል አስችሎታል።

በውድድሩ ላ ሮሃዎች ባደረጓቸው 6 ጨዋታዎች በሙሉ ተሰልፏል ፣ በአጠቃላይ 629 ደቂቃዎችን በሜዳ ላይ ከተጫወተ በኋላ ወደ ቶኪዮ ኦሎምፒክም ሄዶ ከብራዚል ጋር እስከነበረው የፍፃሜ ጨዋታ ድረስ ሀገሩን ወክሎ ነበር።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Bundesliga