Connect with us
Express news


Football

መሪው ፓሪስ ሴንት ጄርሜን ሻምፒዮኑ ሊልን ይገጥማል!

Leading Paris Saint-Germain Take On Reigning Champions Lille!
ligue1.com

የበቀል ጊዜ! ፒኤስጂዎች ባለፈው የውድድር ዘመን የሊግ 1 ዋንጫ እና በዚህ የውድድር ዘመን መጀመሪያ ላይ ደግሞ የፈረንሳይ ሱፐር ካፕ የነጠቋቸው ሊሎችን የሚበቀሉበት እድል።

ፒኤስጂ ፣ ሁለተኛው ሌንስን በሰባት ነጥብ በልጦ ፣ በ28 ነጥብ በሊግ 1 አናት ላይ ተቀምጧል። ሊል በሚገርም ሁኔታ በ15 ነጥብ ብቻ አስረኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ባለፈው አመት ሶስት ጊዜ ብቻ ሽንፈት ያስተናገደው ሊል ፣ የሊግ 1 አሸናፊ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ይህ በጣም አስደንጋጭ ነው ። በዚህ የውድድር ዘመን ቀድሞውንም አራት ሽንፈቶች አስተናግዷል።

ፓሪሳውያኑ በመጨረሻው ጨዋታቸው ማርሴይን ከሜዳቸው ውጪ ገጥመው 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል ፣ በግጥሚያው የቀኝ መስመር ተከላካያቸው አክራፍ ሃኪሚ ቀይ ካርድ ከተመለከተ በኋላ ከ30 ደቂቃ በላይ በ10 ተጫዋቾች እንዲጫወቱ ተገደዋል። አሁን ካለፉት 4 ጨዋታዎች በሶስቱም ግብ ሊያስቆጥርቧቸው ያልቻሉትን ቡድን ሊልን ይገጥማሉ (1-1-2) ። እና ምንም እንኳን የማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ቡድን በውድድር ዘመኑ ፍጹም አጀማመር ቢኖረውም በሬንስ ጠንከር ያለ ውድቀት ገጥሟቸዋል እና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ብቃታቸው አሳማኝ አልነበረም።

https://www.sportingpedia.com/

ሊሎች የባሰ ነገር እያደረጉ ነው ፣ ይህም ለፒኤስጂዎች ጥሩ ዜና ነው። ካለፉት አምስት ግጥሚያዎች አንዱን ብቻ አሸንፈዋል ፣ ይህም ደጋፊዎቻቸው በዚህ የውድድር ዘእን መጀመሪያ ላይ በተሾመው የሊል አሰልጣኝ ጆሴሊን ጎርቬኔክ ላይ ጣቶቻቸውን በፍጥነት ለመቀሰር ተገደዋል። ከሊል በፊት ጊንጋምፕን ሲያሰለጥን ነበር ፣ ነገር ግን የአሰልጣኙ ቆይታ ፣ ቡድኑ ወደ ሊግ 2 በመውረዱ ምክንያት ፣ በጣም ለተወሰነ ጊዜ ነበር። የሊል ደጋፊዎች ፣ የፈረንሳይ ሻምፒዮን በመሆናቸው ትልቅ ተስፋ ነበራቸው ፣ ሆኖም ዝውውሩን ያልተሳካ ፊርማ አድርገው ይመለከቱታል።

ጆሴሊን ጎርቬኔክ በፍጥነት አንድ ነገር አድረግ ይኖርበታል ፣ አለበለዚያ ይህ የውድድር ዘመን በ ሊግ 1 ታሪክ ውስጥ በጣም መጥፎው ሪከርድ ሊሆን ይችላል።

https://news.in-24.com/

ወደ ቡድን ዜና ስንመለስ ፣ በመጨረሻው ጨዋታ ላይ ጉዳት አጋጥሞት ቢያንስ ለአንድ ወር ከጨዋታ ውጪ ለመሆን የተገደደውን ማርኮ ቬራቲቲን በጨዋታው አይሰለፍም። ዋኛልደም በቦታው ሳይሰለፍ አይቀርም። ራሞስ አሁንም ከሜዳው ውጪ ነው። ለ ፒኤስጂ ትልቅ ችግር ሊሆን የሚችለው የ ክሊያን ምባፔ የጆሮ ኢንፌክሽን ነው። በዚህ የውድድር ዘመን የቡድኑ ምርጥ አጥቂ ተጫዋች በመሆኑ እስከ ነገ ወደ ሙሉ ጤንነቱ ተመልሶ ለመጫወት ዝግጁ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን።

ፒኤስጂዎች 3-1 እንደሚያሸንፉ እንገምታለን። ምናልባት በከፍተኛ ደረጃ ላይ ላይሆኑ ይችላሉ ፣ ነገር ግን ሊል በትንሹም ቢሆን በጣም ወጥነት የጎደለው ነበር ፣ እና በ ሊግ 1 ውስጥ ካሉት ምርጥ ቡድን ጋር በሚያደርጉት ፍልሚያ ላይ ወደ አቋማቸው አይመለሱም።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football