Connect with us
Express news


Football

በኢፒኤል ፣ ሮናልዶ እና ቀያይ ሰይጣኖች ስፐርሶችን አዋረዱ!

Ronaldo and Red Devils Savage Spurs in the EPL!
skysports.com

ሮናልዶ፣ ካቫኒ እና ራሽፎርድ ለማንቸስተር ዩናይትድ ግብ አስቆጥረዋል። ቶተንሃም ሆትስፐር በደረአ ሰንጠረዙ መካከለኛ ላይ ናቸው እና ግፊቱ በኑኖ ላይ ጨምሯል!

ኦሊ ጉናር ሶልሻየር ማንቸስተር ዩናይትዶች ፣ በቶተንሃም አቻው ኑኖ ኢስፔሪቶ ሳንቶ ላይ ጫናውን ከፍ ካደረገ በኋላ ሙሉ ለሙሉ የሚገባቸውን እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ (ኢ.ፒ.ኤል.) ድልን ካሳኩ በኋላ ከ”አስቸጋሪ ሳምንት” ማገገማቸው ተናግሯል።

ዩናይትድ ምርጥ ጨዋታ ባሳየበት ግጥሚያ ላይ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የመክፈቻ ግብ አስቆጥሯል። ድሉ ባለፈው ሳምንት በኦልድ ትራፎርድ በሊቨርፑል ፣ የሶልሻየር ቆይታ ጥያቄ ውስጥ ያስገባ የ 5-0 ውጤት ምላሽ የሰጠ ነበር።

ሶልሻየር በቡድኑ የመቆየቱ ጉዳይ እስካሁን 100% እርግጠኛ አይደለም ፣ ነገር ግን ሮናልዶ ፣ ከእረፍት 6 ደቂቃዎች በፊት ፣ ከብሩኖ ፈርናንዴዝ የተሻማለትን ኳስ አየር ላይ እያለ በማስቆጠር ፣ የአለቃው ህይወት የበለጠ ምቹ አድርጓል።

thesun.co.uk

ከዚያም በ64 ደቂቃ ግብ አስቆጣሪው ተጫዋች ፣ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ የሚያቀብል ተጫዋች ሆኗል። የፖርቹጋላዊው ኮከብ ተጫዋች ለኤዲሰን ካቫኒ ፍጹም የሆነ ኳስ ለማቀበል ጥሩ እንቅስቃሴ አሳይቷል ፣ አጥቂዉም በቶተንሃም ግብ ጠባቂ ሁጎ ሎሪስ ላይ በቀላሉ አስቆጥሯል።

ማርከስ ራሽፎርድ ፣ ኔማንጃ ማቲች በተከላካዮች መሃል ያቀበለውን ኳስ በጥሩ ሁኔታ ያጠናቀቀው ግጥሚያው ሊጠናቀቅ አራት ደቂቃ ሲቀረው ነበር።

skysports.com

የስፐርስ ደጋፊዎች በሊቀመንበራቸው ዳንኤል ሌቪ ላይ ንዴታቸውን አሳይተዋል። በሰፊው የቶተንሃም ሆትስፐር ስታዲየም ዙሪያ ” ሌቪ እንዲወጣ እንፈልጋለን ” የሚሉ ዝማሬዎች ጮክ ብለው አስተጋብተዋል።

ቶተንሃም ከእረፍት በኋላ በጣም ደካማ ነበሩ። ሃሪ ኬን በግጥሚያው ደካማ እንቅስቃሴ ያሳየ ሲሆን በደጋፊዎቻቸው መካከል የተፈጠረው አለመረጋጋት ቀጠለ። አሰልጣኝ ኑኖ ፣ በሁለተኛው አጋማሽ ላይ ሉካስ ሞራን በስቲቨን በርግዊን ቀይሮ በሚያስወጣበት ሰአት ፣ ደጋፊዎቹ “የምትሰራውን አታውቅም!” ሲሉ ተደምጠዋል።

ከዚህ ውጤት በኋላ ማንቸስተር ዩናይትድ በኢ.ፒ.ኤል የደረጃ ሰንጠረዥ ውስጥ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቀያይ ሰይጣኖቹ አደረጓቸውው አስር ግጥሚያዎች 17 ነጥብ ያገኙ ሲሆን ይህ ድል በሶልሻየር ላይ ያለውን ጫና ይቀንሰዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ኑኖ በስፐርስ ያለው ቆይታ ስጋት ላይ ወድቋል። የእሱ ቡድን አሁን በ15 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ነው።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football