Connect with us
Express news


Football

ክሪስታል ፓላስ በኢትሃድ 2-0 በማሸነፍ ማንቸስተር ሲቲን አስደነገጠ።

Crystal Palace Shock Manchester City with a 2-goal Win at the Etihad!
sportsskeeda.com

በውድድር ዘመኑ ከተከሰቱት ያልተጠበቁ ውጤቶች አንዱ ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው በክሪስታል ፓላስ ተሸንፏል። ይህም ዊልፍሬድ ዛሃ እና ኮኖር ጋላገር ለ ንስሮቹ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ክሪስታል ፓላስ ቅዳሜ ማንቸስተር ሲቲን በማሸነፍ እስካሁን የውድድር ዘመኑን አስደንጋጭ ውጤት አስመዝግቧል። ፓላስ ወደዚህ ጨዋታ የገባው ከአራት ተከታታይ አቻ ውጤት ቢሆንም በዚህ የውድድር ዘመን ሻምፒዮን ለመሆን ትልቅ ግምት ከተሰጠው ቡድን ጋር ያሳዩት ብቃት አስገራሚ ነበር።

ፓላስ እንደ ቡድን በራስ መተማመን የጀመረ ሲሆን በግጥሚያው መጀመርያ ደቂቃ በሲቲ ተከላካዮች ላይ ጫና ሲፈጥሩ ነበር ፣ እና በአይሜሪክ ላፖርቴ በጋሊገር እና በዛሃ በተፈጠረበት ጫና ኳሱን ማንም ተጫዋች ወደሌለበት ቦታ ይመታዋል ፣ ዛሃ በግራ እግሩ በኤደርሰን ላይ አስገራሚ የመክፈቻ ግብ አስቆጥሯል።

goal.com

በሁለተኛው አጋማሽ የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን ጨዋታውን ለመቆጣጠር ሞክሯል ፣ ጋብርኤል ጃሱስ ከኋላ የመታውን ኳስ ተጠቅሞ አቻ መሆን ቢችሉም ፣ ፊል ፎደን በግንባታው ላይ ከሜዳ ውጪ ስለነበር ግቡ በ ቫር ተሽሯል።

ከዚህም ባለፈ ዳኛው አንድሬ ማርሪነር ፣ በመጀመሪያው አጋማሽ የባከነ ሰአት ላይ ላፖርቴ ከሲቲ ግብ በ35 ያርድ ርቀት ላይ በዛሃ ላይ በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ አሰናብቶታል።

ያ ውሳኔ ሲቲን ያደናቀፈ ይመስላል እና ጋሊገር በመጨረሻው ደቂቃ ፓላሶች ባደረጉት አሪፍ መልሶ ማጥቃት ሁለተኛውን እና የማሸነፍያውን ግብ አስቆጥሯል። ጋሊገር ጎል ማስቆጠር ብቻ ሳይሆን በመሀል ሜዳ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴም አድርጓል።

newsdeal.com

ጋርዲዮላ ከጨዋታው በኋላ “ብዙ እድሎች ፈጥረናል ማለት ባንችልም በመጀመሪያው አጋማሽ ግን በቂ የግብ እድሎች አግኝተናል” ሲል ተናግሯል።

“10 ለ11 ከባድ በነበረበት ሰአት ጎል አስቆጥረናል ፣ ነገር ግን ቫር ሻረብን እናም ሮድሪ አንድ ወይም ሁለት የጎል እድሎችን አግኝቶ ነበር። በመጨረሻም በመልሶ ማጥቃት ማንኛውም ነገር ሊከሰት ይችላል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football