Connect with us
Express news


Football

በቻምፒየንስ ሊግ አትላንታ ቢሲ ማንቸስተር ዩናይትድን ይፋለማል!

Atalanta BC Take on Manchester United in Champions League Clash!
goal.com

ማንቸስተር ዩናይትድ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ የጣልያኑ አታላንታ ቢሲን ለመግጠም ወደ ጌዊስ ስታዲየም ያቀናሉ። ቀያይ ሰይጣኖቹ በቻምፒየንስ ሊጉ ሶስተኛ ተከታታይ ድላቸውን ማስመዝገብ ይፈልጋሉ!

ማንቸስተር ዩናይትድ በቻምፒየንስ ሊግ ማክሰኞ ምሸት ላይ አትላንታ ቢሲን ሲገጥሙ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ አቅዷል። ዩናይትድ ቅዳሜ ምሽት በፕሪሚየር ሊጉ ቶተንሃም ሆትስፐርን 3-0 ካሸነፈ በኋላ ወደ ፍልሚያው ያቀናል ፣ በዋናው አሰልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻየር ላይ ከፍተኛ ጫና በርትቶ ነበር ነገር ግን ቀያይ ሰይጣኖቹ በአስደናቂ ሁኔታ ሶስቱን ነጥቦች ማግኘት ችለዋል።

የ 3-5-2 አሰላለፍ በቶተንሃም ላይ ጥሩ ውጤት ያስመዘገበ ሲሆን ፤ ሮናልዶ ፣ ኤዲሰን ካቫኒ እና ራሽፎርድ ጎል አስቆጥረዋል እና ድሉ የ20 ጊዜ የእንግሊዝ ሻምፒዮን ፣ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው የደርቢ ተቀናቃኙ ማንሸስተር ሲቲ በሶስት ነጥብ ዝቅ ብሎ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

manunitednews.com

የሶልሻየር ቡድን በመስከረም 14 በምድብ ስድስት መክፈቻ ግጥሚያ ላይ በያንግ ቦይስ 2-1 ከተሸነፈ በኋላ ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ከፍተኛውን ነጥብ መሰብሰብ ችሏል። ከቪላሪያል እና ከአታላንታ ከመመራት በመነሳት እና ሮናልዶ በሁለቱም ጨዋታዎች የማሸነፍያ ግብ በማስቆጠር ፣ አሸንፏል።

ማን ዩናይትድ በ6 ነጥብ የቻምፒየንስ ሊግ ምድቡን በበላይነት ቢይዝም እራሱን እንደ ብቁ አድርጎ ሊቆጥር አይችልም ምክንያቱም ቀያይ ሰይጣኖቹ በአራተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ያንግ ቦይስ ጋር ያላቸው ልዩነት ሶስት ነጥብ ብቻ ነው እና ማክሰኞ በሚደረገእው ግጥሚያ ላይ ከተሸነፉ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ።

አትላንታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጥሩ አቋም ላይ ይገኛል ከኡዲኔሴ እና ከላዚዮ ጋር አቻ ቢለያይም ሳምፕዶሪያን 3-1 በማሸነፍ በአጠቃላይ በ11 ጨዋታዎች 19 ነጥቦችን በመሰብሰብ እና አምስት ግጥሚያዎችን አሸንፎ በአራት አቻ በመለያየት አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በጉዳት ረገድ አትላንታ ቤራት ድጂምሲቲ፣ ሮቢን ጎሴንስ፣ ራፋኤል ቶሎይ፣ ማትዮ ፔሲና እና ሃንስ ሃተቦየር የማይሰለፉ ሲሆን ዩናይትድ ለዚህ ጨዋታ ሙሉ ለሙሉ ብቁ የሆነ ቡድን ሊኖረው ይችላል። ሮናልዶ ጎል በማስቆጠር ቀያይ ሰይጣኖቹን 3-1 እንደሚያሸንፉ ይጠብቁ!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football