Connect with us
Express news


Football

በቻምፒዮንስ ሊጉ በአስደናቂ ሁኔታ ከኋላ ተነስተው ያሸነፉ ቡድኖች! – ክፍል 2

Greatest Champions League Comebacks Ever! – Part II
skysports.com

በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እጅግ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ ቡድኖች ከኋላ ተነስተው ያሸነፉባቸውን ጨዋታዎች ላይ የጀመርነው ተከታታይ ትንተናችን ሁለተኛ ክፍል ቀጥሏል። እስከ ቁጥር 5 እንመለከታለን!

7. ኤኤስ ሞናኮ 3-1 ሪያል ማድሪድ (በድምሩ 5-5፣ ሞናኮ ከሜዳው ውጪ ባስቆጠረው ጎል አሸንፏል) – 2004

ሞናኮ ከኋላ ተነስቶ በመምጣት ሪያል ማድሪድን በ 2003/04 ዩሲኤል ከውድድሩ ውጪ ማድረግ ችሏል።

የሊግአው ክለብ በመጀመሪያው ጨዋታ በቂ ተፎካካሪ ነበር። በሴባስቲን ስኩላቺ እና በፈርናንዶ ሞሪየንቴስ በኩል መረቡን አገኙ ፣ ነገር ግን የማድሪድ የማጥቃት ሃይል እንዲያሸንፉ አድርጓቸዋል እና በእርግጠኝነት እንደገናም እንደዛ እንደሚሆን ሲጠበቅ ነበር።

ኢቫን ሄልጌራ ፣ ዚነዲን ዚዳን ፣ ሉዊስ ፊጎ እና ሮናልዶ በሳንቲያጎ በርናባው ያስቆጠሩ ሲሆን በሞናኮ የሁለተኛው ጨዋታ ተጨማሪ ጎሎች ተጠብቀው ነበር። ራውል በመጀመሪያው አጋማሽ በግራ እግሩ ምርጥ ጎል ሲያስቆጥር ሪያል 5-2 በሆነ ውጤት መምራት ጀመረ ጨዋታውም የተጠናቀቀ ይመስል ነበር።

youtube.com

እስካይሆን ድረስ ማለት ነው። ሉዶቪች ጂዩሊ ከመጀመሪያው አጋማሽ በፊት አንድግብ አስቆጠረ ከዛም ከሪያል ማድሪድ በውሰት የመጣው ሞሪየንቴስ ሞናኮ ከእረፍት በኋላ አንድ ጎል አስቆጥሮ መሪ አድርጓል።

ምርጥ የነበረው ጂዩሊ በድምር ውጤት አቻ እንዲሆኑ እና ከሜዳው ውጪ በተቆጠረ ጎል የበላይ አድርጓቸዋል ፣ ይህም በአስደናቂ ሁኔታ በዩሲኤል ከኋላ ተነስተው ለማለፍ በቂ ነበር!

6. ቼልሲ 4-1 ናፖሊ – 2012

ቼልሲ በ2012 የዩሲኤል የመጀመሪያ ጨዋታ በናፖሊ 3-1 ከተሸነፈ በኋላ ችግር ውስጥ ገብቷል። በአለም ላይ ካሉ ምርጥ ወጣት አሰልጣኞች አንዱ ሆኖ ወደ ቼልሲ የመጣው አንድሬ ቪላስ ቦአስ እየተቸገረ ነበር።

ከዩሲኤል የወጡ የሚመስሉት ሰማያዊዎቹ እሱን አሰናብተው የደጋፊውን ተወዳጁ ሮቤርቶ ዲ ማቴኦን ሾሙ። ቀድሞ የማሰልጠን ልምድ የነበረው በብዙ ትናንሽ ክለቦች ኤምኬ ዶንስ እና ዌስት ብሮሚች አልቢዮን ነበር። ጣሊያናዊው ቼልሲን ለውጦ ይህን ጨዋታ ሙሉ በሙሉ ገለበጠ!

ጎካን ኢንለር ለናፖሊ ጎል ካስቆጠረ በኋላ ጨዋታውን ወደ ተጨማሪ ሰአት ለመውሰድ የሰማያዊዎቹ አንጋፋ ሶስት ተጫዋቾች ዲዲየር ድሮግባ፣ ጆን ቴሪ እና ፍራንክ ላምፓርድ ሶስት ግቦችን አስቆጥረዋል። ከዚያም ብራኒስላቭ ኢቫኖቪች ከድሮግባ የተሻገረለትን ኳስ መትቶ በጭማሪ ሰአት በአስደናቂ ሁኔታ አስቆጥሮ እንዲያልፉ አድርጓል።

ቼልሲ በሩብ ፍፃሜው ቤኔፊካን አሸንፎ ከዛም በግማሽ ፍፃሜው ባርሴሎናን በጥሩ ሁኔታ አሸንፏል። በመጨረሻም በሙኒክ ከባየርን ጋር ተጫውተው ዋንጫውን አንስተዋል!

ዲ ማትዮ በህዳር ወር ከስራው ተባረረ ፣ ነገር ግን ጥቂት አሰልጣኞች ናቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህን ያህል ትልቅ ተፅእኖ እንዳላቸው መናገር የሚችሉት!

5. ሊቨርፑል 4-0 ባርሴሎና (በድምሩ 4-3) – 2019

ባርሴሎና በሜዳው 3-0 በሆነ ውጤት በጭማሪ ሰአት እየመራ ኦስማን ዴምቤሌ ማስቆጠር የሚችለውን ኳስ ደካማ በሆነ ሁኔታ ወደ አሊሰን እጅ ሲያስገባ ሊዮኔል ሜሲ በንዴት ወድቋል። አርጀንቲናዊው የፊት አጥቂ ስራው እንዳልተጠናቀቀ እና ይህ የባርሴሎና ቡድን ደካማ እንደነበረ የሚያውቅ ይመስላል።

እስካሁን ከተቆጠሩት ምርጥ ቅጣት ምቶች መካከል አንዱን ያካተተ ድንቅ ግላዊ ብቃትን ካሳየ በኋላም ሜሲ በ2018/19 የግማሽ ፍፃሜ የሁለተኛ ዙር ጨዋታ ወደ አንፊልድ ሜዳ በመጣበት ወቅት በእርግጠኝነት ጥርጣሬ አድሮበት መሆን አለበት።

youtube.com

በትልቅ ጨዋታዎች ምርጥ የሚሆነው የሊቨርፑል እንቆቅልሽ ሰው የሆነው ዲቮክ ኦሪጊ በእረፍት ጊዜ የየርገን ክሎፕን ቡድን መሪ ለማድረግ ቀደም ብሎ ጎል አስቆጥሯል ነገርግን ሁለት ተጨማሪ ግቦች ያስፈልጉ ነበር።

“[ጎል ካስቆጠርን] ሊቨርፑል አምስት (አምስት) ያስፈልጋቸዋል – እና ቢያንስ አንድ እናስቆጥራለን… ተስማማን?” ከባርሴሎና ኦፊሻል የትዊተር አካውንት የድጋፍ ጥሪ ነበር።

ተሳስተዋል። ጆርጂኒዮ ዊጃናልዱም ከተቀያሪ ወንበር ላይ ሲወጣ ማየት ለሊቨርፑል ደጋፊዎች ታሪካዊ ምስል ይሆናል ምክንያቱም በሶስት ደቂቃ ውስጥ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሮ አቻ አድርጓል!

ባርሴሎና እየፈራረሰ ነበር ፣ ሜሲ ታስሮ ነበር ፣ እና የቡድን አጋሮቹ በዙሪያው ይንቀጠቀጡ ነበር። ከዚያም ሊቨርፑል የማእዘን ምት አገኘ። ትሬንት አሌክሳንደር-አርኖልድ በፍጥነት አሻማው እና ኦሪጊ አስደናቂ የሆነውን ከኋላ ተነስቶ ማሸነፍ ለማጠናቀቅ ወደ መረቡ ጣሪያ ቀረቀረው!

ይቀጥላል…

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football