Connect with us
Express news


Football

ዌስትሃም በ10 ተጫዋቾች ለመጨረስ የተገደደው ቪላን 4-1 አሸነፈ!

West Ham Trash 10-man Villa 4-1!
standard.co.uk

ዌስትሃም ዩናይትድ በቪላ ፓርክ አስቶንቪላ መረብ ላይ አራት ግቦችን በማስቆጠር በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ (ኢ.ፒ.ኤል.) ከፍተኛ አራት ደረጃ ላይ መቀመጡን አጠናክሮታል።

ዌስትሃም ከሜዳው ውጪ ባደረገው ጨዋታ እስካሁን ያልተሸነፉ ሲሆን አስቶንቪላ በተከታታይ አራተኛውን የኢ.ፒ.ኤል. ሽንፈት አስተናግዷል። በትናንቱ ጨዋታ ልዩ የሆነው የዌስትሃም ካፒቴን ዴላን ራይስ የማሸነፊያውን ጎል ያስቆጠረው እና እንዲሁም ለግብ የሚሆን ኳስ አቀብሎ ነበር።

መዶሻዎች ጨዋታው ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ተቆጣጥረዋል እና የመክፈቻውን ግብ ለማስቆጠር ብዙ ጊዜ አልፈጀባቸውም። ቤንጃሚን ጆንሰን በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ በግራ እግሩ ላይ በመምታት ወደ ታች ግራ ጥግ ላይ አስቆጥሯል። ዴቪድ ሞየስ በቀኝ መስመር ተከላካይነት መጫወት የሚችልባቸው በርካታ አማራጮች እንዳሉት ግልፅ ነው ፣ ኩፋል ከጉዳት ሲመለስ ጆንሰን ደግሞ በጥሩ አቋም ላይ ይገኛል።

አስቶንቪላ በደጋፊዎቻቸው ፊት በቀላሉ እጅ ለመስጠት ፈቃደኛ አልነበሩም እና ኦሊ ዋትኪንስ በ34ኛው ደቂቃ ላይ ጨዋታውን አቻ አድርጓል። ኤሚሊያኖ ቡኤንዲያ ፎርናልስን በማታለል ኳሱን በቀላሉ ወደ ግብ መቀየር ወደሚችለው እና ፣ማንም ሰው አጠገቡ ወዳልነበረው ዋትኪንስ ልኮታል።

የ 1-1 ውጤቱ ግን ለአራት ደቂቃዎች ያህል ብቻ ነበር የቆየው ፣ ዲላን ራይስ በሚያስደንቅ የረጅም ርቀት ምት የቪላ ግብ ጠባቂ ላይ ሲያስቆጥር ጆንሰን የመጀመሪያ ግብ እንዳደረገው ወደ ግርጌ ግራ ጥግ ላይ ኳሱን ልኮታል።

standard.co.uk

በሁለተኛው አጋማሽ በቪላ በኩል ነገሮች የተባባሱ ሲሆን ፣ ኤዝሪ ኮንሳ በ50ኛው ደቂቃ የዌስትሃም አጥቂ ላይ በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግዷል።

በመቀጠል ፓብሎ ፎርናልስ እና ጃሮድ ቦወን በሀይሉ ብልጫ ተጠቅመው በሁለት ፈጣን መልሶ ማጥቃት በ80ኛው እና 84ኛው ደቂቃ ላይ ጎል አስቆጥረዋል።

የዲን ስሚዝ አንበሳዎች የሽንፈት ጉዟቸውን መቋጨት አልቻሉም እና አሁን በኢፒኤል በአስር ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ዌስትሃም በ20 ነጥብ ወደ ከፍተኛ አራት እየገባ ነው። ጥያቄው በህዳር 7 ከሊቨርፑል ጋር እንዴት ይጫወታል የሚለውን ነው?

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football