Connect with us
Express news


Football

አስቂኝ በራስ ላይ የተቆጠሩ ግቦች – ክፍል ሶስት

Funniest Own-Goals Ever – Part III
https://www.theguardian.com/

በምንግዜም አስቂኝ በራስ ላይ የተቆጠሩ ግቦች ላይ የነበረን ተከታታይ ፅሁፍ ፣ የምንጊዜም ምርጥ ሦስቱን በመመልከት ይጠናቀቃል!

3. አድርያን ገልፍ – ፑሊ ፎትቦል ከ ኤፍሲ ሬንስ (2017)

አድሪያን ገፊፎ በስዊዘርላንድ ስድስተኛ ዲቪዝዮን የእግር ኳስ ተጫዋች ሆኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነትን ለማትረፍ አስቦ አያውቅም ነበር። አማካዩ ይህንን አስደናቂ የመቀስ ምት በራሱ ግብ ያስቆጠረው በቫዱዳይዝ ካፕ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በፑሊ ፉትቦል እና በኤፍሲ ሬኔንስ መካከል በተደረገ ግጥሚያ ላይ ሲሆን ፣ የሚያሳዝነው ነገር ቡድኑ 2-1 እየተሸነፈ ነበር።

youtube.com

ኳሱን በመጀመሪያ ንክኪ መቆጣጠር ከባድ ነበር። ሆኖም ግን ፣ ከሁለተኛው ይልቅ የመጀመርያው ንክኪ እጅግ በጣም የተሻለ ነበር ፣ ይህም የማይቻል ከሚመስለው አንግል ወደ ራሱ መረብ ላይ በአክሮባት አስቆጥሯል። እንዴት ያለ አስደናቂ ግብ ነው!

2. መሐመድ ሻትናዊ – አል-ፋይሳሊ ከ አል-ወህዳት (2015)

ለአል-ፋይሳሊ ግብ ጠባቂ መሀመድ ሻትዋኒ ፍትሃዊ ለመሆን በዚህ የጆርዳን ደርቢ አል-ወህዳት ያስተናገዳት ሁለተኛ ግብ ላይ የተከላካይ መስመሩ ጭምር ጥፋተኛ ነበር።

youtube.com

ከኋላ መስመር ወደ ግብ ክልሉ የገባ ኳስ በአግባቡ ማውጣት አልቻሉም እና የተቀናቃኙ ቡድን አጥቂ በጣም በቀላሉ ሁኔታ ተከላካዩን ያልፈዋ። ሻትዋኒ የመጀመሪያውን ምት ካዳነ በኋላ አደጋውን የመቀነስ እድል ነበረው። ነገር ግን ግብ ጠባቂው እግሩን አውጥቶ በሚያስደንቅ ሁኔታ ኳሱን በራሱ መረብ ላይ አስቆትሯል!

1. ፌስቱስ ቤይሴ – ሲትዝን ኤኤ ከ ሰን ሄይ ኤስሲ (2011)

ደጋግመን ምስሉን ብንመለከተው እንኳን ፣ የፌስቱስ ቤይስ አላማ ምን እንደሆነ ለመረዳት አስቸጋሪ ነው። ይህንን አስደናቂ ግብ በሆንግ ኮንግ አንደኛ ዲቪዚዮን ላይ የምንግዜም አስደናቂ በራስ ላይ የተቆጠረ ግብ ብለነዋል።

youtube.com

የሲትዝን ኤኤ ተጫዋች ጃክ ሴሊ ያሻማው ዝቅተኛ ኳስ የቡድን አጋሩ የማግኘት እድሉ አነስተኛ ነበር ፣ ነገር ግን ቤይሴ ኳሱን በጭንቅላት ማውጣት እንደማይችል አውቋል። የ ሰን ሄይ የመሀል ተከላካይ በምትኩ ለየት ያለ የመቀስ ምት መርጧል እና ኳሱን ወደ የላይኛው ጥግ በመላክ በራሱ መረብ ላይ አስቆጥሯል!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football