Connect with us
Express news


Football

ላይፕዚግ በቻምፒየንስ ሊግ በመጨረሻ ደቂቃ ላይ የአቻነት ግብ በማስቆጠር ፒኤስጂን አስደነገጠ!

Leipzig Shock PSG with Last-Second Draw in Champions League!
marca.com

ዶሚኒክ ሶቦስላይ በሽርፍራፊ ሰከንድ ላይ ለላይፕዚግ ፍፁም ቅጣት ምት በማስቆጠር ፣ ሜሲ ሳይዝ የገባው ፓሪስ ሴንት ጄርሜንን አበሳጭቷል።

ረቡዕ እለት በቻምፒየንስ ሊግ ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ሲለያይ ፣ ላይፕዚግ ዘግይቶ ባስቆጠረው ግብ ጨዋታውን 2-2 እንዲጠናቀቅ አድርጓል።

ፒኤስጂ ከሜዳው ውጪ ለማሸነፍ ጥሩ እንቅስቃሴ ያሳየ ሲሆን ግጥምያው ሊጠናቀቅ 30 ደቂቃ ሲቀረውም 2-1 እየመራ ነበር።

በመጨረሻዎቹ ሴኮንዶች ውስጥ ግን የፒኤስጂው ተከላካይ ፕሪስኔል ኪምፔምቤ በክርስቶፈር ንኩንኩ ላይ ጥፋት በመስራቱ ላይፕዚግ ፍፁም ቅጣት ምት አግኝቷል ፣ ዶሚኒክ ሶቦስላይም ኳሱን በቀላሉ ከመረብ ጋር አገናኝቷል።

marca.com

የ ፒኤስጂ የመሃል መስመር ተጫዋች ጆርጂኒዮ ዊጅናልደም ለ ዳዝን በሰጠው መግለጫ ፣ “እንደ ላይፕዚጎች በጥሩ ሁኔታ አልጀመርንም ፣ ነገር ግን ጨዋታውን መልሰን መቆጣጠር ነበረብን” ብሏል። “በሁለተኛው አጋማሽ የጎል እድሎችን ፈጠረናል ፣ ነገር ግን በተቀራኒው ለነሱም ብዙ እድል እንዲያገኙ አድርገናል።

“ከዚያ ተምረን ጨዋታውን በተሻለ ሁኔታ መቆጣጠር አለብን ምክንያቱም 2-1 እየመራን እና የጎል እድሎቻችንን መጠቀም ነበረብን። ብዙ መስተካከል ያለባቸው ነገሮች አሉ።”

ፒኤስጂ ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀሮ ጫና ውስጥ ነበር ፣ ሲልቫ ተከላካዮችን በማለፍ የመኮረዉን ኳስ ጂያንሉጂ ዶናርማ ካዳነው በኋላ ፣ ካፒቴኑ ማርኩዊንሆስ ኳሱን ከመስመር ላይ አውጥቶታል።

ባለሜዶቹ ግፊቱን አጠናክረው በማስቀጠል ክሪስቶፈር ንኩንኩ መሪ የሚያደርጋቸውን ግብ ሲልቫ ካሻገረለት ኳስ በግንባሩ ገጭቶ አስቆጥሯል። ነገር ግን ዋንያልደም ፣ ለፒኤስጂ በ 21 ደቂቃ የመጀመርያውን ግብ ሲያስቆጥር ሁለተኛውን ግብ ደግሞ ማርኩዊንሆስ በግንባሩ የገጨውን ኳስ ከቫር ክርክር በኋላ አስቆጥሯል ፣ ውጤቱንም 2-1 በማድረግ መሪነቱን እንዲይዙ አድርጓል።

france24.com

ምባፔ በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ ላይ የላይፕዚግ ግብ ጠባቂ ፒተር ጉላሲ ላይ በቀጥታ በመምታት ሁለት ግልፅ እድሎችን አባክኗል።

ውጤቱ ፒኤስጂ ሜሲ ከሜዳ በራቀበት ጊዜ ፣ በአንድ ነጥብ ዝቅ ብለው መሪነቱን ለማንቸስተር ሲቲ አስረክቧል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football