Connect with us
Express news


Football

መዶሻዎቹ በእሁድ ምርጥ የኢፒኤል ፍጥጫ ቀዮቹን ያስተናግዳሉ!

Hammers Host the Reds in Epic EPL Sunday Showdown!
thisisanfield.com

ሊቨርፑል እሁድ ወደ ዌስትሃም ይጓዛል። በዚህ ታላቅ የፕሪምየር ሊግ ግጥሚያ ማን የበላይ ሆኖ ይወጣል?

ሊቨርፑል በእሁድ ምሽት ከዌስትሀም ዩናይትድ ጋር ለመገናኘት ወደ ለንደን ሲጓዝ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መሪ ቼልሲ ላይ ጫናውን ለመጠበቅ ይፈልጋል።

የዴቪድ ሞይስ ቡድን በቅርብ ጊዜ በኢፒኤል ፍልሚያ አስቶንቪላን 4-1 ሲያሸንፍ የየርገን ክሎፕ ቀዮች ከብራይተን ኤንድ ሆቭ አልቢዮን ጋር 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የመርሲሳይዱ ክለብ ወደ እሁዱ ጨዋታ ፣ ከዌስትሀም ጋር የአራት ተከታታይ ጨዋታዎች ድል ይዞ የሚገባ ይሆናል። በዚህ ጨዋታ ሁሌም ብዙ ጎሎች ሲቆጠሩ ሊቨርፑል ከዋና ከተማው ክለብ ጋር ባደረገው ያለፉት 10 የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች 29 ጎሎችን አስቆጥሯል።

ኒኮላ ቭላሲች እና አንድሪይ ያርሞሌንኮ ሁለቱም ዌስትሃም በሳምንቱ አጋማሽ ከጌንክ ጋር አቻ የወጡበት ጨዋታ በጉዳት ያመለጣቸው ሲሆን በዚህ ጨዋታ ላይም አጠራጣሪ ናቸው።

ሞዬስ ከዩሮፓ ሊግ ጨዋታው በኋላ ምንም አይነት አዲስ ስጋቶችን አላሳወቁም እናም በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ከርት ዙማ እና ቤን ጆንሰንን ወደ ሀመርስ የተከላካይ መስመር እንደሚመልሳቸው ይጠበቃል።

hammers.news

ፓብሎ ፎርናልስ ፣ ቶማስ ሶውቼክ እና ጃሮድ ቦወን በዋና 11 ውስጥ ቦታቸውን መልሰው እንደሚያገኙ ይጠበቃል ፣ ማኑዌል ላንዚኒ እና የኮንጎው ተከላካይ አርተር ማሱዋኩ በተጠባባቂ ወንበር ላይ የሚጀምሩ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ሊቨርፑልን በተመለከተ የርገን ክሎፕ ሮቤርቶ ፊርሚኖ በሳምንቱ አጋማሽ ላይ “ከባድ” የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው አረጋግጠዋል ፣ ኩርቲስ ጆንስ እና ጆ ጎሜዝም በአይን ጉዳት እና የእግር ጉዳት ከሜዳ እንደሚርቁ አረጋግጠዋል።

የጆንስ አለመገኘት ከጄምስ ሚልነር ፣ ናቢ ኬይታ እና ሃርቪ ኢሊዮት ጋር ወደ ጉዳት ዝርዝር በመጨመር የሊቨርፑልን የመሀል ሜዳ ቀውስ አባብሶታል። ሆኖም ቲያጎ አልካንትራ ፣ ፋቢንሆ እና አሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሊን ለመጀመር ብቁ ናቸው።

premierleague.com

አንዲ ሮበርትሰን እና ኢብራሂማ ኮናቴ በዚህ ቅዳሜና እሁድ ወደ ኋላ መስመር እንደሚመለሱ ይጠበቃል ፣ ሞሃመድ ሳላህ በኢ.ፒ.ኤል. ሲዝን ከሜዳው ውጪ ባደረጋቸው የመጀመርያዎቹ 6 የሊግ ጨዋታዎች ጎል ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች ለመሆን ይፈልጋል ፣ አሁን ከቲዬሪ ሄነሪ ጋር እኩል 5 ላይ ይገኛል።

ይህ የሁለት አጥቂ ቡድኖች ግጥሚያ ሲሆን ምርጥ ጨዋታ እንደሚሆን ይጠበቃል። ሆኖም ሊቨርፑል በመጨረሻ 3-1 እንደሚያሸንፍ እንገምታለን!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football