Connect with us
Express news


Football

የሻምፒዮንስ ሊግ አንጋፋዎች ፣ ክፍል ሶስት!

Legends of the Champions League – Part III
goal.com

የ ዩኢኤፍኤ ቻፒዮንስ ሊግ (ዩሲኤል) የፍፃሜ ጨዋታዎችን ታሪክ የምንመለከትበት ተከታታይ ፅሁፋችን ፣ በዚህ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የተከሰተውን ሁኔታ በመመልከት ይቀጥላል!

ሪያል ማድሪድ 3-0 ቫሌንሺያ (2000)

ይህ በዝነኛው ቡድን የበላይነት የተጠናቀቅ ግጥሚያ ነበር። ፍልሚያው ሪያል ማድሪድ በላሊጋእ የደረጃ ሰንጠርዥ በመካከለኛ ላይ የተቀመጠ ቡድንን በቀላሉ የማሸነፍ ስሜት ነበረው።

ቫሌንሺያ ለዚህ የፍጻሜ ጨዋታ በፍጹም የኢመጥን አልነበረም እና ማድሪድ ሎስ ሙርሲዬላጎስን በቀላሉ በማሸነፍ ይህንን አረጋግጠዋል።

የፌርናንዶ ሞሪነቴስ አስደናቂ የጭንቅላት ግብ ፣ የስቲቭ ማክማንማን ድንቅ የአየር ላይ ግብ እና የራውል አሪፍ ግብ የማድሪድስታስ ምሽትን አድቀዋል ፣ ይህም የቪሴንቴ ዴል ቦስክ ቡድን ስምንተኛ የአውሮፓ ዋንጫ ነበር።

ባየር ሙኒክ 1-1 ቫሌንሺያ ፣ ባየር ሙኒክ በፍጹም ቅጣት ምት 5-4 አሸንፏል (2001)

እ.ኤ.አ. በ 2001 የፍጻሜ ጨዋታ ብቸኛ የተቆጠሩ ግቦች በፍፁም ቅጣት ምት ነበር ፣ ሻምፒዮናው ደግሞ በፍፁም ቅጣት ምት ተለይቷል!

ጋዝካ ሜንደታ ገና በሶስተኛው ደቂቃ ላይ የመጀመርያውን ግብ አስቆጥሯል ፣ ባየርን ከደቂቃዎች በኋላ ፍፁም ቅጣት ምት ቢያገኝም ፣ ሳንቲያጎ ካኒዛሬዝ የማህመት ሾልን ጥረት በማዳን የምሽቱ ጀግና መሆን ችሏል።

ነገር ግን ስቴፋን ኤፈንበርግ በሁለተኛ አጋማሽ ፍፁም ቅጣት ምት ካስቆጠረ በኋላ ኦሊቨር ካህን በፍጻሜ ጨዋታው ተረኛ ጀግና መሆን ችሏል ፣ ግጥሚያው ለሁለት ሰአታት የተደረገ ቢሆንም አንድም ተጨማሪ ግብ መገኘት አልቻለም።

አንጋፋው የባየርን ግብ ጠባቂ በጨዋታው ሁለት ፍፁም ቅጣት ምቶችን በማዳን ስሙን በ ዩሲኤል እና ባየር ሙኒክ ታሪክ ውስጥ አስፍሯል!

ባየር ሙይንሽን 1-2 ሪያል ማድሪድ (2002)

ሪያል ማድሪድ እ.ኤ.አ. በ 2000 ተጠባቂ በነበሩበት ጊዜ ድል አስመዝግበዋል ፣ ነገር ግን ከሁለት ዓመታት በኋላ ከባየር ሊቨርኩሰን ጋር በነበራቸው የፍፃሜ ግጥሚያ ላይ ተጠባቂ ቡድን አልንበሩም ፣ ምክንያቱም የጀርመኑ ቡድን በፍፃሜ ግጥሚያ ላይ አስደሳች ግጥሚያ አሳይተው ነበር።

ራውል እና ሉሲዮ ከ13 ደቂቃ ውስጥ ግብ በማስቆጠር ግጥሚያዉን 1-1 አድርገዋል። ይሁን እንጂ ይህ የፍፃሜ ግጥሚያ በአንድ ነገር ብቻ ይታወሳል ፣ የዚንዲን ዚዳን ከእረፍት በፊት ያስቆጠራት የማሸነፊያ ግብ።

ምንም እንኳን በኢከር ካሲላስ ቢታገዝም ፣ የፈረንሣዊው የማይታመን የአየር ላይ ግብ የዚህ አስደናቂ ፍጥጫ ልዩነት ፈጣሪ ግብ ነበር። ወጣቱ ግብ ጠባቂ በሁለተኛው አጋማሽ ተጎድቶ የነበረውን ሴሳር ሳንቼዝን በመተካት ፣ 20 አመት ሊሞላው አምስት ቀናት ብቻ ሲቀረው ብዙ የግብ እድሎችን በማዳን ሁለተኛ የዩሲኤል ድሉን አስመዝግቧል!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football