Connect with us
Express news


Football

በስታምፎርድ ብሪጅ የሊጉ መሪዎች ከበርንሌይ ጋር አቻ ወጥተዋል!

Stamford Bridge Stalemate as League Leaders Held by Plucky Burnley!
malaymail.com

በርንሌይ ምርጥ አቋም ላይ ከሚገኘው ቼልሲ ጋር ነጥብ ለመጋራት የተፋለመ ሲሆን የመጀመሪያው አጋማሽ የሀቨርትዝ ግብ በቪድራ ተሰርዟል።

በስታምፎርድ ብሪጅ 79ኛው ደቂቃ ላይ የበርንሌው ቼክ አጥቂ ማትዬ ቪድራ በጭንቅላቱ ያስቆጠረው ኳስ በስታምፎርድ ብሪጅ መሪውን ቼልሲን አስደንግጧል ፣ ጨዋታውም 1-1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

የቪድራ ጎል በዚህ ሲዝን ቼልሲዎች በክፍት ጨዋታ የተቋጠረባቸው የመጀመሪያው ግብ ነው። ከጨዋታው በኋላ የብሉዝ ማናጀር ቶማስ ቱቸል ስሜቱን ለጋዜጠኞች ተናግሯል፡- “በእርግጥ በጣም አዝኛለሁ፣ ይህንን ጨዋታ 100 ጊዜ ብንጫወት 99 ጊዜ እናሸንፋለን፣ ዛሬ ግን አላሸነፍንም። ሁለተኛው ጎል ወሳኝ ነበር። ሁሌም አንድ ኳስ አንድ ሽሚያ ሲያመልጥህ ይህ ሊሆን ይችላል የኛ ጥፋት ነው ተጨማሪ ጎል ማስቆጠር ነበረብን ፣ ብዙ የጎል እድሎችን ፈጥረናል” ሲል የቼልሲው አሰልጣኝ ተናግሯል።

“እነሱን የምንፈልግበት ቦታ ላይ ይዘናቸው ነበር። ብዙ እድሎችን ትፈጥራለህ። በንፁህ እድል ነጥብ ለመስረቅ እንደሚቻል እንዲያምኑ ፈቀድንላቸዋል እና ያ ነው የሆነው። ይህ እንዲህ አይነቱ የመጀመሪያ ጨዋታ አይደለም እና የመጨረሻውም አይሆንም። በአፈፃፀም ፣ በአቋም እና በነበረው ጥራት ተደስቻለሁ። እግር ኳስ ነው ፣ ዛሬ ከእኛ ጋር አልነበረም”

https://www.burnleyexpress.net/

በጨዋታው ቼልሲዎች የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢወስዱም ሊጠቀሙበት አልቻሉም ምክንያቱም በርንሌይ ጎል ላይ ኒክ ፖፕ ያለማቋረጥ አስደናቂ ኳሶችን ሲያድን ነበር።

ሆኖም ካይ ሀቨርትዝ በመጀመሪያው አጋማሽ ያስቆጠረው ኳስ ነበር እስከ እረፍት ድረስ ሁለቱን ቡድኖች የለያቸው ፣ በ33ኛው ደቂቃ ላይ ከሪስ ጀምስ የተሻገረለትን ኳስ ጀርመናዊው አጥቂ በግንባሩ በመግጨት አስቆጥሮ ወደ እረፍት ወጥተዋል።

በርንሌይ ለማጥቃት ጥቂት እድሎች ቢያገኙም አቻነታቸውን ለማግኘት ግን አንድ ብቻ ነበር ያስፈለጋቸው።

ጄይ ሮድሪጌዝ የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ ወደ ቪድራ አቀበለ እሱም በ79ኛው ደቂቃ ከፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን መሀል ላይ መቶ አስቆጥሯል።

1-1 መለያየት ማለት ቼልሲ በ26 ነጥብ የኢ.ፒ.ኤል. የደረጃ ሰንጠረዡን መሪ ሆኖ ይቀጥላል ማለት ነው። በርንሌይ በ8 ነጥብ በወራጅ ቀጠናው 18ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Must See

More in Football